Tuesday, February 4, 2014

ሰሞኑን የተለቀቀው የዘንድሮው የሂውማን ራይትስ ወች ሪፖርት የወያኔን አፈና በድጋሚ አጋለጠ


ወያኔ በሆድ አደር በለስልጣናቱ አማካኝነት እስኪሰለቸን በመደጋገም የተቃዋሚ
ፓርቲዎች ራእይ የለሽነትና ደካማነት እንጅ ሀገሪቱ ለፖለቲካ ጨዋታ ምቹ ናት፤
የሀገራችንን  ብርቅ  ነጻ  ጋዜጠኞች  ራሱ  ሽብርተኛ  እያለ  ለሚጠራቸው  ፖለቲካ
ድርጅቶች ይወግናሉ፤  ወይም ደግሞ የሽብርተኛ ድርጅቶች ጉዳይ አስፈጻሚዎች
ናቸውና የመሳሰሉትን እየደረደረ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲዋሽና ዓለምን ሲያታልል
ቢከርምም  እንሆ  ዓለማቀፍ  እውቅና  ባላቸው  ድርጅቶች  ሪፖርት  በተደጋጋሚ
እየተጋለጠ መሆኑ እየታየ ነው።
ሰሞኑን  የወጣው  የ2013ን  እንቅስቃሴ  የሚገመግመው  የሂውማን  ራይትስ  ወች
ሪፖርት  እንደሚያመለክተው  ግን  ፋሽስት  ወያኔ  ለራሱ  ህልውና  ይጠቅመው
ዘንድ  የፖለቲካ  ምህዳሩን  በማትበብ  ማንም  ግለሰብም  ሆነ  ፖለቲካ  ፓርቲ
ሊነቀሳቀስ  ከማይችልበት  ደረጃ  ላይ  እንዳደረሰው  አጋልጧል።  ይህ  የድርጅቱ
ሪፖርት  የነጻ  ሚዲያ  ህልውና  በኢትዮጵያ  ከፍተኛ  አደጋ  ውስጥ  እንደወደቀ
ጨምሮ አጋልጧል።

ከጥቂት አመታት በፊት ፋሽስት ወያኔ ባጸደቀው የጸረ ሽብርተኝነት አዋጅ የተነሳ
ፖለቲከኞችና  ጋዜጠኞች  ሽብርተኛ  ተብለው  እንደታሠሩና  እንደተፈረደባቸው
የጠቀሰው  የተቋሙ  ሪፖርት  በህጋዊና  ሰላማዊ  መንገድ  የሚንቀሳቀሱ  የፖለቲካ
ፓርቲዎች  በፍርሃት  ቆፈን  ውስጥ  እንዲቀመጡ  ተደርገዋል  ብሏል።  ከዚህ
በተጨማሪም  ሌሎች  የሰብዓዊ  መብት  ጥሰቶችም  ከልክ  በላይ  እየተባባሱ
መምጣታቸውን  የጠቀሰው  ሪፖርት  ህጋዊ  ታራሚዎች  በተለይም  ጋዜተኞችና
ፖለቲካ  እስረኞች  በገለልተና  አካላት  እንዴይጎበኙ  እገዳ  ይታልባቸዋል  ሲል
አጋልጧል።      

No comments:

Post a Comment