Sunday, February 23, 2014

ህዝቡ ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል ሲል ለብአዴን/ኢህአዴግ ተቃውሞን አሰማ።

አማራው ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አለምነው መኮንን የሚመሩትን የአማራ ሕዝብ በጸያፍ ቃላት መሳደባቸውን ተከትሎ አንድነት እና መኢአድ ፓርቲዎች በጋራ ዛሬ በባህርዳር የጠሩት ሰላማዊ ሰልፍ ከፍተኛ የሆነ ሕዝብ በተገኘበት በሰላም ተጠናቀቀ።
ህዝቡ ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል ሲል ለብአዴን/ኢህአዴግ ተቃውሞን አሰማ።
ሺህዎች የሚቆጠሩ የባህርዳር ነዋሪዎች ቁጣቸውን ለመግለጽ በወጡበት በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ሕዝቡ በአቶ አለምነው የተሰደበውን ለማስታወስና ቁጣውንም ለመግለጽ ሰልፈኛው ጫማውን አንገቱ ላይ በማንጠልጠል በሰላማዊ ሁኔታ በባዶ እግሩ በመሄድ በአዲስ የተቃውሞ ስልት ድምጹን አሰምቷል ያሉት በስፍራው የነበሩ የሰልፉ ታዳሚዎች እንዲህ ያለው የትግል አገላለጽ የሚደነቅና ወደፊትም ሊበረታታ የሚገባው ነው ብለዋል።
በባህር ዳር በተደረገው በዚህ ትልቅ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ አቶ አለምነው በአማራ ህዝብ ላይ የተናገሩት የጥላቻ ንግግር በትላልቅ ስፒከሮች ለሰልፈኛው በድጋሚ የተሰማ ሲሆን ሰልፈኛውም በቁጭት በብአዴን ላይ ተቃውሞውን በአንድ ድምጽ አሰምቷል።

No comments:

Post a Comment