Thursday, December 11, 2014

አሳዛኙ ብሔራዊ ውርደታችን

ኢትዮጵያ መንግስት አላት ወይ? የአሜሪካ አምባሳደር ለኢትዮጵያ መንግስት በቀይ ባህር ለሞቱት ኢትዮጵያውያን የሃዘን መግለጫ ላኩ።ኢህአዲግ/ወያኔ እስካሁን አንዳች አልተነፈሰም።Statement by Patricia Haslach, U.S. Ambassador to Ethiopia

Patricia Haslach, U.S. Ambassador to Ethiopia
Patricia Haslach, U.S. Ambassador to Ethiopia
በያዝነው ሳምንት መጀመርያ ላይ ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች በየመን የባህር ዳርቻ፣ በቀይ ባህር ውስጥ ከሰባ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መስመጣቸው መሰማቱ ይታወቃል።ጉዳዩ በሀገር ቤት እና በመላው ዓለም በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ሃዘን አስከትሏል።
ከእዚህ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያውያንን ልብ ያደማው ጉዳይ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን ቢቢሲን ጨምሮ በርካታ የዜና አውታሮች የተቀባበሉትን ጉዳይ ላይ አንዳች የሃዘን መግለጫ አለማሰማቱ ነው።በትናንሽ አደጋ ለሞቱ ለሌላ ሀገር ዜጎች የሃዘን መግለጫ በማውጣት እና በመላክ የሚታወቀው ኢህአዲግ/ወያኔ ለኢትዮጵያውያን ሞት አንዳች አልመተንፈሱ ሌላው የብሔራዊ ውርደታችን መገለጫ ነው።በሳውዲ ጉዳይ መንግስት እንደሌለን አውቀን ነበር።ዘንድሮም በቀይ ባህሩ አደጋ አረጋገጥን።በፌስቡክ ገፃቸው የእየእለቱን ውሎ የሚለጥፉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ሰሞኑን ከ 300 ሚልዮን ብር በላይ ወጣበት ስለተባለው በአሶሳ ስለነበረው ብሔር ብሄርሰቦች በዓል ማውሳታቸው ኢትዮጵያ መንግስት አላት ወይ? ብለው ብዙዎች እንዲጠይቁ ማስገደዱ አልቀረም።
ከእዚህ በታች በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ ከሰባ በላይ ለሚሆኑት በቀይ ባህር ሕይወታቸው ላለፈው ኢትዮጵያውያን የሃዘን መግለጫ አወጣ።የኢትዮጵያ መንግስት ስለጉዳዩ እስካሁን ድረስ ምንም አላለም።
”ትናንት በየመን የባህር ዳርቻ ቀይ ባህር ውስጥ በሰጠመችው ጀልባ ሕይወታቸው ባለፈው ኢትዮጵያውያን የተሰማኝን ትልቅ ሃዘን ለኢትዮጵያ መንግስት እና ለሟቾች ቤተሰብ እገልፃለሁ።ልባችን ከሟቾች ቤተሰቦች እና ወዳጆች ጋር ሁሉ ነው” በኢትዮያ የአሜሪካ አምባሳደር ወ/ሮ ፓትሪሽያ ሃስላች

No comments:

Post a Comment