Wednesday, August 20, 2014

A Note on Modern Slavery

Gezahegne Bekele (PhD)
August 13, 2014
Recently a publication called “The Global Slavery Index” was released that documents and identifies issues related to modern day slavery. The publication first defines modern slavery as the possession and control of a person in such a way as to significantly deprive that person of his or her individual liberty, with the intent of exploiting that person through their use, management, profit, transfer or disposal. Usually this exercise will be achieved through means such as violence or threats of violence, deception and/or coercion. In essence modern slavery goes beyond the age old slavery by including slavery-like practices (such as debtbondage, forced marriage, and sale or exploitation of children), human trafficking and forced labor.
The Global Slavery Index compiles slavery related information and presents them in an easily understandable manner. Specifically the index, 1. Provides a ranking of 162 countries around the world, based on a combined measure of three factors: estimated prevalence of modern slavery by population, a measure of child marriage, and a measure of human trafficking in and out of a country. 2. Identifies factors relevant to risk of slavery and provides a standardized measure of these factors that allows comparison country by country. 3. Examines the strength of government responses to modern slavery for the 20 countries at the top and bottom of the Index ranking.
Concepts
Trafficking is one of the main components of Modern Slavery. Using the United Nations’ Trafficking protocol of 2000, Trafficking is identified as 1- Recruitment, transportation, transfer, harboring or receipt of persons. 2- By means of threat or use of force or other forms of coercion, of abduction, of fraud, of deception, of theabuse of power or of a position of vulnerability or of the giving or receiving of payments or benefits to achieve the consent of a person having control over another person. 3- With the intent of exploiting that person through: Prostitution of others; Sexual exploitation; Forced labor; Slavery (or similar practices); Servitude; and Removal of organs.
Slavery is in turn addressed as the status or condition of a person over whom any or all of the powers attaching to the right of ownership are exercised. According to The Slavery Convention (1926) and Supplementary Slavery Convention (1956), slavery includes slavery-like practices: debt bondage, forced or servile marriage, sale or exploitation of children and descent-based slavery.
The third important component of Modern Slavery is forced Labor in which, according to International Labor Organization (ILO) Forced Labor Convention, 1930 (No. 29), all work or service which is exacted from any person under the menace of any penalty and for which the said person has not offered himself voluntarily.
Analysis
The analysis of Modern Slavery shows that there are 29.8 million people in the world today that are slaves. The highest Modern Slavery prevalence or slaves as percentages of the population occurs in the West African nation of Mauritania which has a deeply entrenched hereditary slavery, and is ranked number 1 in the Index. Mauritania has a deeply entrenched hereditary slavery. It is estimated that there are between 140,000 – 160,000 people enslaved in a country with a population of just 3.8 million. Haiti -a country plagued by conflict, natural disaster, and with deeply entrenched practices of child slavery- is second on the Index. Pakistan, India, Nepal, Moldova, Benin, Ivory Coast, The Gambia, and Gabon complete the top 10 in prevalence.
However, when actual numbers of enslaved people are considered instead of prevalence rates a very different picture of Modern Slavery can be observed. Nearly 78-percent of all modern day slavery takes place in India, China, Pakistan, Nigeria, Ethiopia, Russia, Thailand, Democratic Republic of Congo, and Myanmar. India for example is estimated to have between 13,300,000 and 14,700,000 people enslaved. The India country study suggests that while this involves the exploitation of some foreign nationals, by far the largest proportion of this problem is the exploitation of Indians citizens within India itself, particularly through debt bondage and bonded labor. The China country study on the other hand suggests 2,800,000 to 3,100,000 in modern slavery which includes the forced labor of men, women and children in many parts of the economy, including domestic servitude and forced begging, the sexual exploitation of women and children, and forced marriage.
Regionally, it is noteworthy that 16.36% of the estimated total 29.8 million people in Modern Slavery are in Sub-Saharan Africa. Sub-Saharan Africa is the largest of the regions measured for the Global Slavery Index. The high prevalence measured for such countries as the Democratic Republic of Congo and Mauritania reflect centuries-old patterns of enslavement, often based on colonial conflicts and injustice exacerbated by contemporary armed conflict. The index asserts “Ongoing conflicts, extremes of poverty, high levels of corruption, and the impact of resource exploitation to feed global markets all increase the risk of enslavement in many African countries”. Child and forced marriages–practices the index considers as a form of slavery– and still tolerated in the context of informal or ‘traditional’ legal systems in many countries further contribute to Sub-Saharan African Modern Slavery.
The Case of Ethiopia1
Ethiopia is among the most enslaving (ranked fifth in absolute numbers) nation responsible for 620,000 – 680,000 modern day slaves. Ethiopia is also the twelfth most slavery prone country in terms of modern day slavery prevalence.
The country study on Ethiopia states that in recent years Ethiopia has seen a rapid increase in outward migration, with millions of Ethiopians travelling throughout Africa and overseas, mostly to Gulf States and the Middle East, to find work. The Ethiopian Ministry of Labor and Social Affairs, which is largely responsible for migration issues, reported that it reviewed and approved 198, 000 contracts for overseas employment, predominately for domestic workers in 2012; a 50% increase from 2011. This, however, only represents part of the huge numbers of those migrating overseas – with well-placed sources claiming this is only 30 – 40 % of the overall figure. Irregular migration, including migration facilitated by illegal brokers, makes up the remaining 60 – 70%. According to UNHCR, many of these migrants use Yemen and Djibouti as transit points between Ethiopia and the Middle East. Between 1 January and 30 November 2012, a total of 107, 500 migrants arrived in Yemen; 84,000 of which were Ethiopians.
The country study further explains that the increased migration of Ethiopians abroad has led to increased reports of abuse and exploitation of workers. The majority of regular outward migrants are young women, with limited education, seeking domestic work in the Middle East. There are documented cases of women being stranded and exploited during transit or being exploited upon reaching their destination during their search for work. In the absence of regular employment channels for men, young males turn to irregular migration routes, predominately through the horn of Africa and Yemen. Reports suggest that these Ethiopian males are subjected to forced labor in low skilled jobs including waste disposal, camel and goat herding and construction in Yemen, Djibouti and the Middle East.
In addition to the exploitation of Ethiopian migrant workers abroad, modern slavery is also an issue within Ethiopia, particularly for children. According to UNICEF, Ethiopia has one of the highest rates of child labor in the world. When child labor is taken as a form of modern day slavery, UNICEF estimates that at least 1.2 million children are enslaved in Ethiopia every year. Girls from rural areas are exploited in domestic and commercial sex work, while boys are subjected to forced labor in traditional weaving, herding, guarding and street vending.
Furthermore, the movement of Ethiopian domestic workers has increased in numbers in a few short years, which has led to an increase in the number of recruitment agencies. Illegal private employment agencies have rapidly expanded, with the Ethiopian Ministry of Foreign Affairs indicating that more than 1000 illegal brokers are operating in Addis Ababa alone.
Domestic workers travelling under these illegal private employment agencies are particularly vulnerable to exploitation. Some of these workers have no supporting legal contract, and are sometimes bound to a debt-bondage style agreement with brokers in their destination country. The situation is particularly difficult along the Red Sea coast, with reports of traffickers targeting Ethiopians looking to travel onwards to Gulf countries. The migration process itself can be particularly dangerous when undertaken through migrant smugglers, with reports of migrants being held in “torture camps” in Yemen and the Sinai. In a recent BBC report, it was suggested many Ethiopian migrants are held for ransom in these “torture camps”, where the women are routinely raped and men are subject to burns. The report also suggests that those held captive have had their bones broken and eyes removed.
Certain traditional practices make girls particularly vulnerable to slavery-like practices, such as child marriage. Women tend to be around seven years younger than men when they marry in Ethiopia, with around 63% of women aged 25-49 married by age 18; only 13% of men aged 25-49 were married by this age. Some reports indicate that girls can be abducted from their homes and forced to marry. Of the 50,000 estimated women and children involved in the sex industry, it is suggested that a quarter are victims of sexual exploitation and trafficking.
This article is primarily an attempt to present excerpts from the original publication. In order to emphasize the controversial issues and concepts associated with modern slavery in general and in particular the case of Ethiopia, I have taken the liberty of incorporating points in the country studies nearly word for word.
Details of the index can be obtained here:http://www.globalslaveryindex.org/report/?download

Wednesday, August 13, 2014

Ethiopian gov’t to bring criminal charges against six weeklies

Reporters Without Borders
Ethiopia’s justice ministry has announced that it is bringing criminal charges ranging from “dissemination of false rumours with the intent of overthrowing the government” to “undermining public trust in the government and attempts at fostering ethnic and religious divisions” against six news weeklies.
ethiopia pressIn a communiqué released on 5 August, the ministry accused the six weeklies – Lomi, Enqu, Fact, Jano, Addis Guday and Afro-Times – of “encouraging terrorism, endangering national security, repeated incitement of ethnic and religious hate, and smears against officials and public institutions.”
Two of the weeklies, Addis Guday and Fact, are among Ethiopia’s leading privately-owned newspapers and have often covered events or published stories that have generated political controversy. One of Addis Guday’s journalists, Asmamaw Hailegiorgis, has been held on a terrorism charge since 25 April.
The ministry said it had been “patient” with the six weeklies but had finally decided to bring charges in response to public pressure for corrective action. It also warned that it was ready to bring charges against other publications engaging in similar “subversive” activity.
Prime Minister Hailemariam Desalegn’s government must end the harassment of independent media that it has been orchestrating for the past few months,” said Reporters Without Borders secretary-general Christophe Deloire.
“With the 10 journalists and bloggers already accused of terrorism and now this prosecution threat, the government is sending a much tougher message to news providers. Prosecuting journalists for ‘undermining public trust in the government’ is totally illegitimate.”
Ethiopia is ranked 143rd out of 180 countries in the 2014 Reporters Without Borders press freedom index
Ze-Habesha

Wednesday, August 6, 2014

“ስለእኔ አታልቅሱ!” (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ)


“ዋይ ዋይ ከሚሉና ሙሾ ከሚያወጡ ሴቶችና ከሕዝቡ እጅግ ብዙዎች ተከተሉት፡፡ ኢየሱስ ግን ወደ እነርሱ ዘወር ብሎ እንዲህ አለ፡- እናንተ የኢየሩሳሌም ልጆች ለእኔስ አታልቅሱልኝ፤ ዳሩ ግን፡- መካኖችና ያልወለዱ ማኀፀኖች፣ ያላጠቡ ጡቶችም ብፁአን ናቸው የሚሉበት ጊዜ እነሆ ይመጣልና ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ፡፡

ከቅዱስ መጽሐፉ ይህን የመሲሁ የመጨረሻ ምክር የመረጥኩት (ምንም እንኳ ረቢው የተናገረው ስለመለኮታዊው ትምህርት ቢሆንም) ዓለማዊው ፍች የኢትዮጵያችንን የወቅቱን መንፈስ ለመረዳት ከማስቻሉም በዘለለ፤ በየጊዜው እያየን፣ እየሰማን ያለነውን የፖለቲካ ተቃውሞው የጥምዝምዞሽ መንገድ በአርምሞ ለመመርመር መልካም ምሳሌ ይሆናል በሚል እሳቤም ነው፡፡

የሠላማዊ ትግሉ መቀልበሻ ስልቶች 



እፍኝ በማይሞሉ ፋኖዎች ከአርባ ዓመታት በፊት “ደደቢት” በተሰኘ የሰሜን በርሃ የተመሰረተው ህወሓት ከተራዘመ የትግል ጉዙ በኋላ፤ ታጋይ ሕላዊ ዮሴፍ “እልፍ ሆነናል” እንዲል፤ ራሱን አጠናክሮ “እልፍ” በመሆን ሥልጣን ይዞ፣ የሀገሪቷን አንጡራ-ሀብት አመራሩ መምነሽነሺያው ካደረገ፣ እነሆ ሃያ ሶስት ዓመታት እንደዘበት ነጎዱ፡፡ ርግጥ ነው ይህች የዳንኪራ እና ፌሽታ ዘመን እውን ትሆን ዘንድ፣ የቡድኑ ዋና ዋና መሪዎችም ሆኑ መላው ታጋይ (የበረከቱ ተቋዳሽ ባይሆንም) በቃላት ሊገለፅ የማይችል የመከራ ዓመታትን በቆራጥነት ማሳለፋቸው የሚስተባበል ታሪክ አይደለም፡፡ ሥልጣን እጃቸው ከገባ በኋላም የአገር ጥቅም መገበርን ጨምሮ እየገደሉ፣ እያሰሩና እያሰደዱ… በሕዝብ ላይ ወደር የለሽ ጭካኔን በመፈፀም ዘላቂነቱን እንዲህ ስለማስረገጣቸውም ተወርቶ የተዘጋ አጀንዳ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ ይሁንና ከዕለት ዕለት እየመረረና እየከፋ የመጣው ይህ ኩነት፣ ምድሪቷ የአንድ እውነት መዝጊያና የአዲስ ዓመት ምዕራፍ መክፈቻ ላይ መድረሷን ስለማመላከቱ ለመመስከር ጠቢብነትን አይጠይቅም፤ የዘመኑ መንፈስ እያሰማን ያለው “ፋኖ ተሰማራ”ም የሶስተኛው አብዮት ደውል ስለመሆኑ ለመረዳት የቀደሙ ነብያቶችን ትንበያ መጠበቅ አያሻም፡፡ ገዥዎቻችን፣ መግደልና ማሰርን ሱፍ ለብሶ፣ ከረባት አስሮ፤ ጠዋት ወደ ቢሮ ተገብቶ፣ ማታ የሚወጣበት መደበኛ ሥራ ከማድረጋቸውም ባለፈ፣ የሥልጣን ግዛታቸውን እንዲህ ነቅተው (ታጥበውና ታጥነው) ባይጠብቁት ኖሮ፣ ለሃያ ሶስት ዓመት ቀርቶ፣ ለሃያ ሶስት ሰዓት እንኳን በቤተ-መንግስቱ መቆየት እንደማይችሉ አብጠርጥረው ያውቁታል፡፡ የዚህ ጽሑፍ ፍሬ-ሃሳብም በዚህ መልኩ የሥልጣን ዕድሜውን ገና የማቱሳላን ያህል ማራዘም የሚፈልገው ኢህአዴግ፣ ተቃዋሚ ድርጅቶች የሚያቀነቅኑት የሠላማዊ ትግል አቅጣጫን የሚቀይስበትን እና የሚወስንበትን የሴራ ፖለቲካ፣ ለውጥ ፈላጊው ኢትዮጵያዊ ነቅቶ እንዲያከሽፈው መቀስቀስ ነው፡፡ ዛሬ በርካቶች በቁጭት እንደሚብሰለሰሉት ኢህአዴግ በመንበሩ ላይ ከሁለት አስርታት በላይ ተደላድሎ የመቆየቱ ምስጢር በውስጣዊ ጥንካሬው፣ አሊያም ሲቪል ጀግኖች በመጥፋታቸው ሳቢያ አይደለም (ወላድ በድባብ ትሂድና፤ ሀገሪቱ የሚሞትላት ጀግና ትውልድ ከመፍጠር መክና አታውቅም)፡፡ የግንባሩ ዋነኛ የጥንካሬ ምንጭ የተቃዋሚውንም ወገን የቤት ሥራ ጠቅልሎ እየሰራ በመሆኑ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ወደኋላ ሄደን በአደረጃጀትም ሆነ በድጋፍ መሰረታቸው ‹‹የተሻሉ›› ሊባሉ የሚችሉ ተቀናቃኝ ፓርቲዎችን ሂደት ብንመረምር፣ መራራውን እውነታ እየጎመዘዘንም ቢሆን መጋታችን አያጠራጥርም፡፡ ለማሳያ ያህልም በአገዛዙ የማስቀየሻ እርምጃ ተጠልፈው ከከሸፉ ሕዝባዊ ንቅናቄዎች መካከል ጥቂቶቹን በአዲስ መስመር እንመልከት፡፡

ኦነግ

የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር፣መለስ ዜናዊና ጓዶቹ ቆንጥረው ከሰጡት የሽግግር መንግስት ሥልጣኑ ተገፍቶ ከወጣ በኋላ ወደለመደው በርሃ በገባበት ወቅት፣ በአንፃራዊነት ቀድሞ መገንባት ከቻለው ጥንካሬ ባሻገር፣ በኦሮምኛ ተናጋሪው ማሕበረሰብ ዘንድ የሚሊዮኖችን ልብ ይበልጥ ማማለል ችሎ እንደነበረ የአደባባይ ሐቅ ነው፡፡ ወቅታዊውን የኃይል አሰላለፍ ጠንቅቆ የተረዳው “አባ መላ”ው ኢህአዴግም የጠብ-መንጃ ግብግቡ ከመጀመሩ አስቀድሞ፣ ከተማውን ለቆ ያልወጣውን የአመራር አባሉን ኢብሳ ጉተማን ወደ እስር ቤት ወረወረ፤ ይህንን ተከትሎም ኦነግ ከመቼውም ጊዜ በላይ በእልህና በቁጭት ተነሳስቶ አርሲና ሐረርን አስተባብሮ፣ ወለጋን በታንክ አቋርጦ፣ ባቱ ተራራን በመድፍ ጩኸት አንቀጥቅጦ፣ በባሌ ተሻግሮ ፊንፊኔ ላይ በድል ሊንጎማለል ነው ተብሎ ሲጠበቅ፤ በግልባጩ ዋና ፀሀፊው ሌንጮ ለታ እና የተወሰኑ መሪዎቹ በቦሌ በኩል በመመለስ “ወይ እኛንም አብራችሁ እሰሩን፤ አሊያም ጓደኛችንን መልሱልን?” በማለት ከመረጡት የኃይል ትግል ጋር የማይጣጣም ስልት ተግብረው አረፉት፤ በዚህም የልብ ልብ የተሰማው ኢህአዴግ፣ የድርጅቱን አባላትም ሆነ ኦሮምኛ ተናጋሪውን በጅምላ በ “ስመ-ኦነግ” እየወነጀለ ለአስከፊ እስር መዳረጉ፣ በክልሉ ላይ ከባድ ፍርሃት አነበረ፡፡ ይህ ፖለቲካዊ ስህተትም ለዛሬው ሽንፈቱ ዋነኛ ተጠቃሽ ሲሆን፤ የተቃውሞ ጎራ ትግሉንም ከሥርዓት ለውጥ ወደ እስረኛ ማስፈታት ያወረደ ቀዳሚ ኩነት ሆኖ በታሪክ ተከትቧል፡፡ 

መአሕድ

የፕ/ር አስራት ወልደየስ የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት (መአሕድ) ውድቀትም ከኦነግ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ መአሕድ በምስረታው ማግስት ያገኘው መጠነ-ሰፊ የሕዝብ ድጋፍ፣ ህወሓት/ኢህአዴግ በ17 ዓመታት ከሰበሰበው ሁሉ ይልቅ እንደነበረ አይዘነጋም፡፡ ይህ አይነቱ ፈጣን ግስጋሴም ሊያስከትለው የሚችለውን የቁጣ ናዳ አስቀድሞ የተረዳው ‹‹ብልጣ-ብልጡ›› ኢህአዴግ፣ ሊቀ-መንበሩን ጉምቱ የሕክምና ሊቅ ጨምሮ ጥቂት የአመራር አባላቱን እስር ቤት ወረወረ፡፡ ከዚያማ ድርጅቱ ‹‹እታገልለታለሁ›› የሚለውን የፖለቲካ ሥልጣን የመቆጣጠር ዓላማውን ‹‹መሪዎቻችን ይፈቱ!›› ወደሚል አኮስሶ ባለበት ሲረግጥና ሲዳክር ለ13 ዓመታት ከቆየ በኋላ፣ በስተመጨረሻ ህላዊነቱ አክትሞ ወደ ሕብረ-ብሔር (መኢአድ) ድርጅትነት መሸጋገሩ ታወጀ፡፡ ክስተቱም አብዮታዊው ግንባሩ የተቃውሞ ጎራውን እንቅስቃሴ ወደፈለገው አቅጣጫ መዘወሩን በሚገባ እንደተካነበት ያስረገጠ ሆኖ አልፏል፡፡ 

ቅንጅት

ዛሬ ዛሬ እንደ ንግስት ሳባ ዘመን የሩቅ ጊዜ ታሪክ ያህል ይሰማኝ የጀመረው ምርጫ 97ም ሌላኛው የነገረ-አውዱ አስረጂ ነው፡፡ በጥቂት ወራት ውስጥ ከጫፍ ጫፍ ሀገራዊ ንቅናቄ መፍጠር የቻለው ግዙፉ ቅንጅት በአብዛኞቹ የምርጫ ጣቢያዎች በይበልጥ ደግሞ በገጠር አካባቢዎች አሸናፊ መሆኑ በተለያዩ አጣሪ አካላት በመረጋገጡ፤ የኢህአዴግን ‹‹መንግስት ለመመስረት የሚያስችለኝ ድምፅ አግኝቻለሁ›› ጨዋታን ከውስጥም ከውጭም አምኖ የተቀበለ አንድም እንኳ አልነበረም፡፡ በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች ይህንን ዓይን ያወጣ ስርቆት በሠላማዊ መንገድ ለመቃወም በሞከሩ ዜጎች ላይ በተወሰደው ርህራሄ አልባ የኃይል እርምጃ በርካታ ንፁሀን ለህልፈት እና ለአካል ጉዳት ሲዳረጉ፣ በተወሰኑ የክልል ከተሞች ደግሞ ከፍተኛ ሕዝባዊ ማጉረምረም ተፈጥሮ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ግና፣ ‹‹ብልሆቹ›› የኢህአዴግ ኤጲስ ቆጶሳት በተካኑት ስልት የቅንጅቱን መሪዎች ከያሉበት ሰብስበው እስር ቤት ከተቱ፤ ትግሉም ከተነሳበት ‹‹የገጠሩ ወገኖቻችን ድምፅ ይመለስ!›› ወደ ‹‹መሪዎቻችን ይፈቱ!›› ቀኝ ኋላ ዞሮ፣ የሥርዓቱ ዕድሜ እንዲቀጥል ስለመፍቀዱ የእኔ ትውልድ የአይን ምስክር መሆኑ ርግጥ ነው፡፡ 

ሕዝበ-ሙስሊ

ለሶስት ዓመት ተመንፈቅ (ከ‹‹እፎይታ ጊዜ››ው በቀር) ካለማቋረጥ በተቀጣጠለው የሙስሊሙ ኃይማኖታዊ ነፃነትን የማስከበር ትግልም፣ የንቅናቄው አስተባባሪዎች ‹ቃሊቲ የታጎሩትን መሪዎች የማስፈታት ዓላማ በአራተኛነት የተያዘ ነው› ቢሉም (‹‹አህባሽን በግዴታ ማጥመቅ ይቁም››፣ ‹‹መጅሊሱ ወደ ሕዝቡ ይመለስ›› እና ‹‹ነፃ ሕዝባዊ ምርጫ ይካሄድ›› የሚሉት ሶስቱ መሪ ጥያቄዎች የተቃውሞ መነሾ እንደሆኑ ልብ ይሏል)፤ የሕዝበ-ሙስሊሙ በተለይም የቅርብ ጊዜዎቹ የመስጂዶቹ እምቢ-ባይነቶች፣ ሥርዓቱ ለማደነቃቀፍ (ዓላማውን ለማስቀየስ) ባዘጋጀው የ‹‹ይፈቱ›› ማዕቀፍ ስር የተገደበ የመምሰል አዝማሚያው ነው በዚህ አውድ እንድጠቅሰው ያስገደደኝ፡፡ በርግጥ የሁለት አስርታቱን የተቃውሞ ልምድ በቅጡ የመረመሩ የሚመስሉት የ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› ወጣቶች፣ በዚህ የተለመደ የትግል ቅልበሳ ላለመጠለፍ የሚያደርጉት ብርቱ ሙከራ እንዳለ ብገነዘብም፣ ከቀደመው ‹‹ጥቁር ሽብር›› ወዲህ በቀጣይ በሚኖሩት የትግል ወቅቶች ዋነኛ የትግል ጥያቄያቸውን ነፃነታቸውን በማስከበር ማዕቀፍ ስር እንደሚያደራጁት አምናለሁ፡፡ 

ማልቀስስ ለማን?

በ1983ቱ የመንግስት ለውጥ ዓለም አቀፋዊው አውድ፣ ለሽፍቶቹ ስብስብ እርግማንም በረከትም ይዞ ነበር፡፡ እርግማኑ፣ በቀደመ-ፖለቲካዊ ዝማሜያቸው ዝግ ሶሻሊስት ሥርዓት መመስረት አለመቻላቸው ሲሆን፤ በረከቱ ደግሞ በረዥሙ የእርስ በእርስ ጦርነት ክፉኛ የተመታችውን አገር በተለይም ተቋሞቿን ለመገንባት ከሚያስፈልገው ጊዜ አኳያ የምዕራባውያኑን ‹‹ዕድል እንስጣቸው›› የድጋፍ ልብ ማግኘታቸው ነው፡፡ በእነ ሳሙኤል ሀንቲንግተን ‹‹መድበለ-ፓርቲ ሥርዓትን እርሱት፤ አውራ ፓርቲነት ያዋጣችኋል›› ምክረ-ሐሳብ አማካኝነት የወቅቱ ምዕራባውያን አለቆቻቸውን መንፈስ መረዳታቸውን ወደኋላ ስንገነዘብ፤ ቢያንስ እስከ 97 ድህረ-ምርጫ ውጥንቅጥ ድረስ በተጓዙበት የአምባ-ገነንነት መንገድ በጥብቅ አለመወገዛቸውን እንረዳለን፡፡ በአናቱም በህወሓትና መሰል ነፍጥ አንጋቢ የድህረ-ቀዝቃዛው ጦርነት ቡድኖች ላይ ተስፋ የነበራቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት እና ምሁራንም ዘግይተውም ቢሆን ቡድኖቹ ወደ ቋሚ ሽፍትነት መቀየራቸውን ከመመልከት አልዳኑም፡፡ የዚህ አይነት ስብስብ ቋሚ መለዮ፣ በመሰረተ ልማት ግንባታዎች ላይ ሙሉ ሀገራዊ ሀብት ማፍሰስ ነው፤ መግፍኤውም ግልፅ ነው፤ የሕብረተሰቡ የአምራችነት ማሕበረ-ኢኮኖሚያዊ አቅም ሲጎለብት፣ እነርሱም የሚያግበሰብሱት ሀብት እየሰፋና እየበዛ እንዲሄድ የማስቻሉ ሀቅ ነው፤ እንደ ህወሓት ያሉ የነፃ-አውጪነት የኋላ ታሪክ ያላቸው ገዢ ቡድኖች፣ በምርጫ ፖለቲካ የማይነቀነቁባቸው ምክንያቶችም ከዚሁ ጋር ይተሳሰራል፤ ከሰላማዊ ሕዝባዊ ዓመፅ ውጪ ይህን ነውረኛ ቡድን ማስቆም እንደማይቻል በ‹‹ሕዳሴ አብዮት›› ርዕሰ-ጉዳይ ለመከራከር የሞከርኩትም ለዚሁ ነው፡፡ እንግዲህ ከእስክንድር ነጋ እስከ ርዕዮት አለሙ፤ ከውብሸት ታዬ እስከ የሱፍ ጌታቸው፤ ከአንዱአለም አራጌ እስከ በቀለ ገርባ፤ ከጦማሪያኑ እስከ እነ ሐብታሙ አያሌው… ድረስ ዘርዝረን የማንጨርሳቸው የእልፍ አእላፍ ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን መታሰር አሳዛኝ ቢሆንም፤ ለእነርሱም ሆነ ለሀገር የሚበጀው ‹‹ታጋይ እንጂ ትግል አይሞትም!›› የሚለውን የጊዜውን አስገዳጅ ሕዝባዊ ጥሪ በመቀበል አደባባዩን በቁጣ ማጥለቅለቅ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ዛሬ እያየነው እንዳለው የግፉአኑን መፈክር አንግቦ መነሳትን ገሸሽ አድርጎ፣ የ‹‹ይፈቱ›› ጥያቄ የትግሉን መንፈስ ይመራው ዘንድ መፍቀድ ሂደቱን ለሥርዓቱ ሴራ አሳልፎ እንደመስጠት የሚቆጠር ይመስለኛል፡፡ መግቢያዬ ላይ የጠቀስኩት የመምህሩ ቃል የሚነግረንም ለእነሱ ከማልቀስ ይልቅ፣ የአምባ-ገነኑን ሥርዓት ቀንበር ተሸክመን በአሳረ-ፍዳ ኑሮአችንን ስለምንገፋው ስለራሳችን ብናለቅስ የተሻለ መሆኑን ነው፡፡ ከዚህ ጎን ለጎንም አብዝተን ነፃነታቸውን የምንሻላቸው ጀግኖቻችን እንደምኞታችን ቢፈቱና መፃኢ ዕድላቸው ምን ሊሆን እንደሚችል ራሳችንን ብንጠይቅ፣ የምንፋጠጠው ‹ተመልሰው በኢህአዴግ የብረት ጫማ ስር ለጥ-ሰጥ ብሎ ማደር› ከሚል እውነታ ጋር ብቻ ነው፡፡ የተለመደውን ‹‹የይቅርታ ቃጭል›› አጥልቀው፣ በተሰበረ መንፈስ ከትግሉ ርቀው አንደበታቸውን ሸብበው አሊያም ከሀገር ወጥተው ቀሪውን ህይወታቸውን በስደት እንዲያሳልፉ ከማድረግ ያለፈ የምንፈጥርላቸው ወይም የምናመቻችላቸው ምንም ነገር አለመኖሩ ርግጥ ነውና፡፡ ያውም ብርቱካን ሜደቅሳን ለቅቆ፤ ርእዮት ዓለሙን የሚያስርበትን የቆየ የፖለቲካ ጨዋታውን ሳንዘነጋ፡፡ ይህም ነው ሕዝብን የማዳመጥ አንዳችም ልምድ ለሌለው ሥርዓት ‹‹ይፈቱ!››፣ ‹‹ይለቀቁ!›› እያልን ከመጮኽ በመቆጠብ፣ ታሳሪዎቹ ስለተዋደቁባቸው የነፃነት እሴቶች መተግበር መታገልን ግድ ያደርገው፡፡ በጥቅሉ በመከራው ዳገት ላይ ያሉት ወገኖቻችን የገጠማቸውን ሁነት ያስነሳው፣ ማናችንም በነፃነትና በእኩልነት ልንኖርባት የምትገባዋን አገር የመናፈቅ እንደሆነ ከተስማማን ዘንዳ፣ በየእስር እርምጃው የተፈጠሩትን ክፍተቶች እየደፈንን፣ የነፃነቱን ቀን ለማቅረብ መታተር የወቅቱ አስገዳጅ ጉዳይ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ በቀድሞው የቅንጅት አመራሮች የገፍ እስር ማግስት፣ የከተሞቹን ንቅናቄዎች ከ‹‹ይፈቱልን›› ይልቅ፣ ‹‹ድምፃችን ይመለስልን!›› በሚለው መሠረታዊ ጥያቄ አጥብቀን ይዘን ትግላችንን ብናራዝመው ኖሮ፣ ፖለቲካዊ ለውጦችን መጨበጥ እንችል እንደነበር ማናችንም ብንሆን የምንጠራጠር አይመስለኝም፡፡ ከዚህ አኳያም የሚያስማማን ዋነኛ ጭብጥ፣ ቢያንስ የ2002ቱ ምርጫ በተካሄደበት አስቂኝ ድራማ ልክ ተከናውኖ እና ተቀልዶብን የማለፉ ዕድል እጅጉን ያነሰ የመሆኑ ጉዳይ ነበር፡፡ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ ያየናቸው የጦማሪያኑና የሶስቱ ፓርቲዎች ወጣት አመራሮች እስር፣ በተለመደው የ‹‹ይፈቱ›› ደካማ የትግል ስልት የመሄድ ዳርዳርታውን ገርተን፣ ከአደባባዩ መራቃቸውን ተከትሎ እየተፈጠረ ያለ የሚመስለውን (ከማሕበራዊ ድረ-ገፆች እስከ የዕለት ተዕለት የፓርቲዎቹ እንቅስቃሴ ድረስ) ክፍተት መሻገሩ፣ የተሻለ ብቻም ሳይሆን ገዢዎቻችን እንድንሰምጥበት ከሚሹት የሽንፈት ማጥ ውስጥ ከመነከርም የሚገታ አማራጭ ነው፡፡ እነሆም ለማንስ ማልቀስ ይገባል? የሚለውን ጥያቄ መመለስ የሚያስፈልገን እንግዲህ በዚህ ከባድ ወቅት ላይ ነው፡፡ …እንደየተነሱበት አውድ ለሚያምኑባቸው ክቡድ ዕሴቶች ዘብጥያ 
ለተጣሉት ዜጎች መብሰልሰልን በመምረጥ ከጎናቸው መሰለፍን ላንገራገርነው ለኛ ማዘን የበለጠ የተገባ ነውና፣ እነርሱ ድርሻቸውን ስለመወጣታቸው እያመሰገንን፣ ፍትሃዊ አቋሞቻቸውን በገዘፈ ጉልበት ወደፊት መውሰድ ብቸኛው ምርጫችን መሆን ይኖርበታል፡፡ የ‹‹ሕዳሴው አብዮት›› ተግባሮትም አስፈላጊው ሥነ-ልቦና ይኸው ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ 
ድል ለግፉአን ኢትዮጵያውያን!

Saturday, August 2, 2014

ኦሮሞ እና እስልምና በ «ሕዳሴ አብዮት» መስመር (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ)


በወርሃ-ግንቦት ላይ ለዘመናት የተንሰራፋውን ሀገራዊ ደዌ ይፈውሳል ብዬ ተስፋ ስለማደርግበት «የሕዳሴ አብዮት» በሶስት ተከታታይ ክፍሎች ለመዳሰስ መሞከሬ ይታወሳል። በወቅቱ መጪው የ «ሕዳሴ አብዮታችን» መፍትሔ ሊሰጥባቸው ከሚገቡ ጉዳዮች መሀል በዋነኝነት የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪው ማሕበረሰብ እና የእስልምና እምነት ተከታዮች የመብት ጥያቄን በተመለከተ በጥቅሉ ጠቃቅሼው አልፌ ነበር። ሆኖም «ሰፋ ብሎ ቢዳሰስ» የሚሉ በተለያየ መንገድ የሚቀርቡ ጎትጓች ድምፆች መበራከታቸው የመነሻ ሃሳቡን ፈታ አድርጌ እንዳቀርብ አስገድዶኛል፤ እንግዲህ ይህ ጭብጥም የዛው ተከታይ መሆኑ ይሰመርልኝ።
የኦሮሞ ጥያቄ፥
በኢትዮጵያችን ከሚገኙ በርካታ ብሔሮች መካከል አብላጫውን ቁጥር የሚይዘው ኦሮምኛ ተናጋሪው ቢሆንም፣ ለዘመናት ይደርሱበት ከነበሩ ሥርዓታዊ በደሎች እና የባሕል ጭፍለቃዎች ዛሬም በምልአት ነፃ እንዳልወጣ በቂ ማሳያዎች አሉ። በ1960ዎቹ አጋማሽ የአገሪቷ አደባባዮች የዘመኑን መንፈስ በተረዱ ቁጡ ወጣቶች መጥለቅለቁን ተከትሎ፣ «በንጉሣዊው አገዛዝ ግብዓተ-መሬት ላይ የመጨረሻዋን ድንጋይ ለማስቀመጥ» በሚል ሰበብ ቤተ-መንግስቱን መቆጣጠር የቻለው ወታደራዊው ደርግ፣ ህልቆ መሳፍርት በሌለው መስዋዕትነት የተገኘውን ወርቃማ ዕድል ከጅማሮው አጨናፍጎታል። በግልባጩ አብዮቱን ካጋሙት ገፊ-ምክንያቶች ዋንኞቹ ለሆኑት የብሔርና የሕዝባዊ መንግስት ምስረታ ጥያቄዎች፣ መፍትሄ ይስጥ አይስጥ እስኪረጋገጥ ድረስ መታገስ ያልፈለገው ህወሓት፣ ጉዳዩ በደም መፋሰስ ብቻ እንደሚፈታ አውጆ ጫካ ሲገባ አዲሱ መንግስት ገና የ6 ወር ጨቅላ እንደነበረ አይዘነጋም። ይሁንና ታሪክ በአስከፊ መልኩ ራሱን ሲደግም ያስተዋልነው ወታደራዊውን መንግስት መንፈቅ-ዓመት ያህል እንኳ መታገስ ያልፈቀደው ይህ ቡድን፣ ለጥያቄዎቹ መልስ ሳይሰጥ ከሁለት አስርታት በላይ ያለመንግራገጭ በሥልጣን ለመቆየት ባለመቸገሩ ነው፤ ርግጥ የእኔ ትውልድም የእድሜውን እኩሌታ በትግስት መጠበቁ የአደባባይ እውነታ ቢሆንም፣ ተጨማሪ የቻይነት ዓመታት ይኖራሉ ብዬ ግን አላስብም፤ አብዮቱን ምኩንያዊ የሚያደርገውም ይህ ነው። …እነሆም ከአራት አስርታት በላይ ሲንከባለሉ የቆዩት የኦሮሞ ጥያቄዎች በ «ሕዳሴ አብዮት» ይፈቱ ዘንዳ፣ ሊተኩርባቸው የሚገቡ አንኳር አጀንዳዎችን በሁለት አውድ ከፍለን እንመለከታለን።
፩—ኢህአዴግ-መራሹ መንግስት ጥያቄዎቹን ከወረቀት ድንጋጌ (ከአፋዊነት) እና ከፕሮፓጋንዳ ሽንገላ ባለፈ፣ እውነተኛ መፍትሔ በሚያስገኝ መልኩ እልባት ሊያበጅላቸው አልፈቀደም፤ ባለፉት ሃያ ሶስት ዓመታት «አነበርኩት» የሚለው ቋንቋ ተኮር ፌዴራሊዝም የይስሙላ ስለመሆኑ ለመገንዘብ፣ ዛሬም ከደርዝን በላይ የፖለቲካ ድርጅቶች የራስ አስተዳደር ጥያቄን አንግበው በትግል መድረክ መገኘታቸውን ማየቱ በቂ ነው። የክልሉ ‹‹ገዥ›› እንደሆነ የሚነገርለት ኦህዴድም ቢሆን፣ የህወሓቱ የአማርኛ ክንፍ እንደሆነው ብአዴን ሁሉ፣ የኦሮምኛ ክንፍ ከመሆን አለማለፉን፣ የብሔሩ ልሂቃንን ጨምሮ የፌደራል ሥርዓቱን አወቃቀር ያጠኑ በርካታ ምሁራን ማስረጃ እያጣቀሱ ያጋለጡት እውነታ ነው። ሕዝቡም በየጊዜውና በየአጋጣሚው የሚያነሳው ጥያቄ አሁንም ተግ አለማለቱ የልሂቃኑ ማስረጃ መሬት መርገጡን ያስረዳል። በቅርቡ አፈ-ጉባኤ አባዱላ ገመዳ ስለሕጋዊነቱ በድፍረት የደሰኮረለት የማስተር ፕላኑ ጥያቄ በኃይል መጨፍለቅም በገዥው በኩል ሕገ-መንግስቱ አፈር ለብሶ እንዳበቃለት ተናግሮ አልፏል። በተጓዳኝ የክልሉ ነዋሪ በተፈጥሮ ሀብቱ ተጠቃሚ እንዳይሆንና ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዳይኖር ከመደረጉ ባሻገር፤ ከሕዝቡ ቁጥር ብዛት አኳያ ኦሮምኛ በሁለተኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋነት እንዲያገለግል ኦህዴድ ተፅእኖ የሚፈጥር አልሆነም፤ ሌላው ቀርቶ ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ ያነሱ ፖለቲከኞች ‹‹ኦነግ›› ተብለው የምድር ፍዳቸውን ሲቀበሉ የታደጋቸው የለም። የዚህ እኩይ ድርጊት ተጠያቂም ጉልበተኛው ህወሓት ብቻ ነው ማለት ገራገርነት ይመስለኛል፤ የገዛ ወገኑን አሳልፎ የሰጠው ኦህዴድም ጭምር የድርሻውን መውሰዱ አይቀሬ ነውና። ይህም ሆኖ ከአንዳንድ ምልክቶች በመነሳት ጥያቄዎቹ መልስ እስካላገኙ ድረስ፣ የቱንም ያህል የእስር ቤት ደጃፎች ከዚህም በላይ ቢጨናነቁ፣ የቱንም ያህል የእስረኞቹ ሰቆቃ እያደር ቢበረታ ከእንግዲህ በኦሮሚያ ምድር በፍርሃት ዝም-ጭጭ ብሎ የሚተኛ ሊኖር እንደማይችል ዛሬ ላይ ቆሞ መናገሩ ‹‹ሟርተኛ›› አያስብልም።
፪—የኦሮምኛ ተናጋሪውን ያደረ ቅራኔ በመፍታት የአንድነት ዘብ ለማድረግ፣ የሀገሪቱ ታሪክ እና ባሕል በዳግም ብያኔ መታደሱ ግድ ነው ብዬ አምናለሁ። የክልሉ ማሕበረሰብ በዘመናዊው መንግስት ምስረታም ሆነ ከባእድ ወረራ መታደጉ ላይ ታላቅ አበርክቶ ቢኖረውም፣ በሀገሪቷ ታሪክ ውስጥ ሚናው ደብዝዞ መገለፁ ጎምዛዛ እውነት ነው፤ የቋንቋው ተናጋሪ ያልሆነው አብዛኛው ኢትዮጵያዊም ይህንን አምኖ ሊያርመው ቀርቶ፣ እውቅና ሊሰጠው እንኳ አለመፍቀዱ፣ ጉዳዩን ወደሰሞነኛው «ውጡ ከሀገራችን» አይነቱ አስደንጋጭ ኩነት ገፍቶታል። ከዚህ በተቃራኒው በጥቂት የብሔሩ ልሂቃን የሚንፀባረቀው (ሀገርን ለፍርሰት ሊያጋልጥ የሚችለው) ሸውራራ የታሪክ አረዳድን እና የቅኝ አገዛዝ ትርክትን ማጥራት ሌላው ወሳኝ የቤት ሥራ ሆኗል፤ ምክንያቱም ከጥያቄው ጋር ተያይዘው የሚነሱ የተቃውሞ ድምፆች ማጠንጠኛ «ባሳለፍነው መቶ ዓመት ለቅኝ አገዛዝ ተዳርገናል፣ ሥርዓታዊ በሆነ መዋቅር የሥልጣን ባይተዋር ሆነን ቆይተናል፣ ከሌላው ሕዝብም በተለየ መልኩ ከሰብአዊ ፍጡር በታች ተቆጠረን ተረግጠናል…» የሚል መንፈስ እንዲይዝ እየተለጠጠ ነው። ይህ የታሪክ ትንተና ስሁት መሆኑን የምንረዳው በየትኛውም መንግስታዊ ሥልጣን ጊዜ (ሀገሪቱ በጦር መሪዎችም ሆነ በነገሥታቱ ጠንካራ መዳፍ ስር በተያዘችበት ዘመን) በግንባር ቀደምትነት በመንበሩ ላይ ይፈራረቁ ከነበሩት አማርኛና ትግርኛ ተናጋሪዎች የማይተናነስ እኩል ሚና እንደነበራቸው የቋንቋው ተናጋሪ ምሁራን በማስረጃ አስደግፈው ባዘጋጇቸው ድርሳኖቻቸው ያተቱትን ስናስተውል ነው።
ለማሳያም ‹‹የጎንደር ዘመን›› ተብሎ ከሚጠቀሰው (እ.ኤ.አ ከ1636-1769ዓ.ም ድረስ የዘለቀው) ማዕከላዊ መንግስት ውድቀት በኋላ የተተካውና ‹‹ዘመነ መሳፍንት›› እየተባለ የሚጠራው አገራዊ የአስተዳደር ዘይቤ ጠንሳሽና ተግባሪ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች እንደነበሩ ማስታወሱ በቂ ነው። በወቅቱ የመንግስቱ መቀመጫ ከሰሜን ጎንደር ወደ ደብረታቦር የተዘዋወረ ሲሆን፣ የግዛት ወሰኑ ደግሞ ጎንደርን፣ ወሎን፣ ጎጃምን፣ ከፊል ሸዋንና ትግራይን የሚያካትት እንደነበር መዛግብቱ ያወሳሉ። በዘመኑ ሥልጣኑን የጠቀለሉትና ‹‹የጁ (ወራ-ሼክ) ስርወ- መንግስት›› በሚል ስም የሚጠሩት የአሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች እንደነበሩ የብሔሩ ምሁራን ነግረውhናል። እያገባደድነው ባለው በዚህ ዓመት ‹‹የውገና ድርሰቶችና የታሪክ እውነቶች›› በሚል ርዕስ ዳጎስ ያለ ጥራዝ ያሳተሙት ታቦር ዋሚ ‹‹በኢትዮጵያ ታሪክ ዘገባዎች አላግባብ ዘመነ መሳፍንት ሲባል የቆየው የየጁ ዘመንና ታሪካዊ ሚና›› በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር በርካታ መጽሐፍትና የጥናት ጽሑፎችን በመጥቀስ ሥልጣኑ በኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች እጅ እንደነበረ በስፋት አብራርተዋል። ታቦር በትርክታቸው ‹‹የጁ ከሰሜን ኢትዮጵያ የኦሮሞ ነገዶች አንዱ እንደሆነና ቀስ በቀስም ይህ ስም የጎሳው ብቻ ሳይሆን ሕዝቡ የሰፈረበት አካባቢ ጭምር መጠሪያ እንደሆነ በርካታ ጸሐፍት ይመሰክራሉ›› (ገፅ 287) ሲሉ በአባሪ ማስረጃዎች አስደግፈው አቅርበዋል። ሥርወ-መንግስቱ በሥልጣን ላይ የቆየበት ጊዜያትንም ‹‹ከጎንደር ዘመነ-መንግስት ማብቂያ እስከ አፄ ቴዎድሮስ መነሳት ድረስ የነበሩትን ዓመታት ሁሉ ያካትታል›› (ገፅ 293) በማለት ገልፀውታል፤ ይህንን በአሃዝ እናስቀምጠው ብንል ደግሞ ወደ 86 ዓመት ገደማ ልንቆጥር እንገደዳለን።
በተመሳሳይ መልኩ ‹‹የኦሮሞ ታሪክ›› የተሰኘው መጽሐፍ ጸሐፊ እሸቱ ኢረና ዲባባም መከራከሪያውን እንዲህ ሲሉ ያጠናክሩታል፡- ‹‹ጎንደር የሃበሻ መንግስት (አቢሲኒያ)ማዕከል በነበረችበት ወቅት የኦሮሞ ህዝብ በአካባቢው ሰፍሮ ይኖር እንደነበረና ወሳኝ ሚና ለረጅም ጊዜ ነበረው፤ እ.ኤ.አ. ከ1853-1854 በጎንደር በእስር ላይ የነበረው ጀርመናዊ ሰዓሊ በሰራቸው ምስሎች ኦሮሞ በወቅቱ በአካባቢው ገዢ እንደነበር እርሱም ከአካባቢው ኦሮሞ ሴት እንዳገባ፤ ምስልዋንም ሰርቶ እነዚህ የስዕል ስራዎቹ እ.ኤ.አ. በ1868 ዓ.ም በለንደን ከተማ በመጽሐፍ መልክ ታትሞ ወጥቶ ይገኛል። በአካባቢው ሰፍረው ይኖሩ ከነበሩት የኦሮሞ ጎሳዎች ውስጥ የቦረና ኦሮሞ አንዱ መሆኑን ኤች ሙሬይ በ1830ዎቹ ባሳተመው ጽሑፍ ውስጥ ከጠቀሰ በኋላ ኦሮሞ እንደ ሕዝብ በደንቢያ በጎጃም፣ በዳሞትና በአንጎት አካባቢዎች ሰፍሮ እንደሚገኝ ተጠቅሷል።›› (ገፅ 83-84) ራሱ የክልሉ መንግስትም፣ በባሕልና ቱሪዝም ቢሮው በኩል ‹‹የኦሮሞ ታሪክ እስከ አስራ ስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን›› በሚል ርዕስ ባሳተመው መጽሐፍ ‹‹…ወራ- ሼክ» የሚለው የቤተሰቡ መጠሪያ በየጁ ኦሮሞዎች ዘንድ ታላቅ ዝና ከማግኘቱም በላይ በአጠቃላይ የየጁ ኦሮሞዎች ቀደምት መንግስት መነሻ ወይም አባት ተደርጎ እስከመቆጠር ደረሰ ይባላል›› (ገፅ 281) ሲል ገልጿል።
በግልባጩ የአፄ ምኒሊክ ፈረስ ሐረርና አርሲ መርገጡን ‹‹የቅኝ-ግዛት ወረራ›› አድርገው የሚያቀርቡ ዘመነኛ ‹‹ፖለቲከኞች››፣ ይህ አይነቱን ጥሬ ሀቅ ለመቀበል ቀርቶ ለመስማት አይፈቅዱም። የጠቀስኳቸው ድርሳናትም የሚነግሩን ኦሮሞ ከሌላው ብሔር ጋር ትንቅንቅ ገጥሞ በለስ ቀንቶት ድል ባደረገ ቁጥር መንግስታዊ ሥልጣን መጠቅለሉን ብቻ አይደለም፤ በሀገሪቱ ታሪክ ጭቆና እንጂ ቅኝ አገዛዝ የሚባል ነገር አለመኖሩንም ጭምር ነው። ከኤርትራ እስከ ሞያሌ፤ ከጋምቤላ እስከ ሶማሌ በተዘረጋው ሰፊ የኢትዮጵያ ግዛት ላይ በተደጋጋሚ ከተቃጡ የባዕዳን ወረራዎች በቀር፣ ቅኝ-ገዢም ሆነ ቅኝ-ተገዢዎች ስለመኖራቸው የሚያትት አንድም የታሪክ መረጃ ተፈልጎ ታጥቷል። መቼም ‹‹ድሮ ነፃ ሀገር ነበረን›› በሚል ዛሬ ላይ የመገንጠልን ጥያቄ ሲያነሱ፤ አሊያም አንድ ብሔርን በነፍጠኛነትና በወራሪነት ሲኮንኑ የምናደምጣቸው ጠርዘኛ ልሂቃን ‹የኦሮሚያ የግዛት ወሰን ጎንደርን እና ትግራይን ያጠቃልል ነበር› ስለማለታቸው ሰምተን አናውቅም። መቀመጫውን ደብረታቦር ላይ አድርጎ ከትግራይ እስከ ሸዋ ያስተዳድር የነበረ ሥርወ-መንግስት፣ የበለጠ ጉልበተኛ ተነስቶበት፣ በተራው ከመንበሩ በኃይል ሲገለበጥ ቅኝ-አገዛዝና ኢ-ሰብአዊ ብሎ ለመኮነን መሞከሩ ውሃ የሚያነሳ ሙግት ሊሆን አይችልም። እዚህ ጋ ሊዘነጋ የማይገባው ጉዳይ፣ በተለይም ከአፄ ምኒሊክ መንገሥ ወዲህ የኦሮሞ ማሕበረሰብ ቋንቋውን ጨምሮ የባሕል እሴቶቹ ተውጠው፣ የአገሪቱ ወካይ እንዳይሆኑ መጨፍለቃቸውን ነው፤ እንደምሳሌም የገዳ ሥርዓት ምንም እንኳ ሁሉንም የቋንቋው ተናጋሪ ያቀፈ ባይሆንም (የ‹‹ጊቤ ግዛት›› ተብለው የሚታወቁት፡- ጅማ፣ ሊሙ፣ ጎማ፣ ጉማ እና ጌራ ከገዳ ይልቅ በንጉሣዊ ሥርዓት ሲተዳደሩ፤ ወለጋና ኢሊባቡርን የመሳሰሉ አካባቢዎችም በ‹‹ሞቲ›› ይመሩ ስለነበር) የአክሱም ሐውልትን ወይም የጎንደር ግንብን ያህል በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ቦታ አለማግኘቱ አይካድም። እንዲሁም በሌላ ቋንቋ ተናጋሪው ዘንድ ‹‹ጣኦት ማምለክ›› ተደርጎ የሚቆጠረው የኢሬቻ ክብረ-በዓል አረዳድ ስሁት ስለመሆኑ ቢረፍድም የመስከሩ ጠቀሜታ የጎላ ነው። ይህ የምስጋና ሥነ-ስርዓት በአገሪቱ ታሪክ ተገቢውን የክብር ስፍራ ሳያገኝ መገፋቱን በማመን፣ ሚዛንን ማስተካከል ግድ ይላል። በጥቅሉ ምግቡ፣ አለባበሱ፣ ሙዚቃውና መሰል እሴቶቹ በትልቁ የታሪካችን ገፅ በበቂ ደረጃ አለመወከላቸውን ዛሬም ለማድበስበስ መሞከሩ መፍትሔውን ከማራቅ፤ አሊያም ልዩነትን ከማስፋት ያለፈ ፋይዳ አይኖረውም። መቼም በዛሬይቱ ኢትዮጵያ፣ የመገንጠል ጥያቄ ያነሱ ቡድኖች መኖራቸው ደብቀን የምናስቀረው ሚስጥር አይደለም፤ ከኦሮሚያ እስኪ ኦጋዴን፤ ከጋምቤላ እስከ ቤንሻንጉል ድረስ ይህን ለማስፈፀም የሚተጉ የታጠቁ ኃይሎች ተፈጥረዋልና። በርግጥ እነዚህ ኃይሎች የቆሙበት መሰረት ማሕበረሰቡን የሚወክል ነው ወይስ የራሳቸውን የሥልጣን ጥማት ብቻ የሚያረካ? የሚለው ገና ያልጠራ፣ አሁንም አጥጋቢ መልስ ያላገኘ ጥያቄ እንደሆነ ይታወቃል። ፖለቲካዊው ፍላጎት ማሕበራዊ ውሉን የዋጠው ይመስላል።
ኤርትራን ያጣንበት ምክንያትም ከዚህ ብዙም እንደማይርቅ ጥርጥር የለውም። አሁንም የዚህን ጥያቄ ውል ከሳትን ሌላ የምናጣው ክፍለ-አካል መኖሩ አይቀሬ ነው። ስለዚህም ነው በ‹‹ሕዳሴው አብዮት›› እንደ አዲስ በምትገነባው ኢትዮጵያችን ጥያቄዎቹ በቀዳሚነት ምላሽ ሊያገኙ ይገባል ብዬ የምከራከረው። በለውጡም፣ እነዚህ ጎታች የፖለቲካ አቋሞች እና አቀንቃኞቹ ዘላቂ መፍትሔ አግኝተው የአንድነት ዘመን አብሳሪ እንደሚሆኑ አልጠራጠርም።
በተቀረ በኦሮሞ ላይ አንድ ብሔር በተለየ መልኩ በደል አድርሷል፣ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ፈፅሟል… መሰል ትርክቶች ጭራና ቀንድ ተሰክቶባቸው ግብረ-ሂትለርና ፋሽስታዊ ድርጊቶች ተመስለው የሚቀርቡበት አውድ ከተራ ጊዜያዊ የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳነት ያለፈ፣ በዕውን ለመፈፀማቸው ምንም አይነት የታሪክ ሰነድ አልተገኘም። ከጥቂት ሳምንት ቀደም ብሎ በዚህ ርዕሰ-ጉዳይ ዙሪያ ከታሪክ ምሁሩ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ጋር ስንወያይ ‹‹ወደ አኖሌ (አርሲ) ከዘመተው የአፄ ምኒሊክ ሠራዊት መካከል አብላጫው ኦሮሞ ነው›› ሲሉ መግለፃቸውም፣ ከዶ/ሩ የትምህርት ደረጃ፣ ከረዥም ዓመት የሥራ ልምዳቸው እና ከቋንቋው ተናጋሪ አብራክ የተገኙ ከመሆናቸው አኳያ ችግሩን ወደ አንድ ብሔር ማላከኩ ስህተትለመሆኑ ሁሉንም የሚያስማማ ይመስለኛል። ታቦር ዋሚም ከላይ በጠቀስኩት መጽሐፍ (ከገፅ 275-278) ከአማራው ነገስታቶች ጋር ጋብቻ የፈፀሙ ኦሮሞ ንጉስና ንግስት በማለት በስዕላዊ መግለጫ አስደግፈው ያቀረቡት የቋንቋው ተናጋሪ ንጉሦችና ነገስታት ስም ዝርዝር እንደተጨማሪ ማስረጃ ሊወሰድ ይችላል። ጸሐፊው ለማሳያነት ከጠቀሷቸው ውስጥ የአፄ ቴዎድሮስ-እቴጌ ተዋበች፣ የአፄ ምኒሊክ-ጣይቱ ብጡል፣ የንግስት ዘውዲቱ-ወሌ ብጡል፣ የአፄ ኃይለስላሴ-እቴጌ መነን፣ የምኒልክን እህት ያገቡት-ንጉስ ሚካኤል… የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት እንደነበሩ አትተዋል። ከዚሁ ጋርም አያይዘው በተለያየ ጊዜ በሀገሪቷ የተከሰቱት የኃይል ግጭቶች አሰላለፍ በብሔር ከመቧደን ይልቅ፣ በሥልጣንና በጥቅመኝነት ላይ የተመሰረቱ እንደነበረ ፈራ-ተባ እያሉም ቢሆን እንዲህ ሲሉ ገልፀውታል፡- ‹‹በጣም የሚገርመው ከሣህለ ሥላሴ ጊዜ ጀምሮ እስከ አፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግስት ድረስ በኦሮሞው ላይ ሲካሄዱ ለነበሩት ዘመቻዎች ሁሉ ግንባር ቀደም ተዋናዮቹ በተለያዩ ምክንያቶች ከነገሥታቶቹ ጋር ጊዜያዊና ዘላቂ ዝምድና የፈጠሩ እራሳቸው ኦሮሞዎች መሆናቸው ነው። …(ራስ ጎበና) እኚህ የኦሮሞ መስፍን የታወቁ ፈረሰኛ፣ ጀግና፣ ተዋጊና ወታደራዊ ስትራቴጂስት ከመሆናቸው በላይ በኦሮሞ የውጊያ ስልትና በኦሮሞ ሥነ-ልቡና ላይ የጠለቀ እውቀት ነበራቸው።
ይህንን ብቃት ሙሉ በሙሉ ለምኒሊክ አገልግሎት አውለውታል። ከሁሉም በፊት ምኒልክ ሳይሆኑ የኦሮሞን ግዛት ያሸነፉት ራስ ጎበና ነበሩ።›› (ገፅ 499-500 እና 503)። ይህን መሰሉ የኃይል ትንቅንቅ ከአርሲና ባሌ በፊት ቤጌምድርና ትግራይ ውስጥ በተከሰተበት ወቅት ኦሮምኛ ተናጋሪው በአሸናፊነት በመውጣቱ ለ86 ዓመት ያህል ሥልጣን ይዞ መቆየቱን ከላይ አይተናል። መቼም የጁዎች፣ ጎንደሮችን ድል አድርገው ሥርወ-መንግስታቸውን ደብረ ታቦር ላይ የመሰረቱት በምርጫ ካርድ (ያለነፍጥ) ነበር ካልተባለ በቀር፣ አንዱን ወገን ለይቶ በሂትለርነት መኮነኑ ፍትሃዊ ካለመሆኑም ባለፈ፤ የሚጠቅመው ከመከራ ነፃ እንዲወጣ የምንዋትትለትን ሕዝብ ሳይሆን፣ የአገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም ነው።
በተጨማሪም በራሱ በቋንቋው ተናጋሪዎች ብቻ ከተዘጋጁ ድርሳናት የጠቀስኳቸው እነዚህ ሁነቶች፣ በማስረጃ ያልተደገፈውን (አፈ-ታሪኩን) የአኖሌ ጡት ቆረጣ ትርክት ተአማኒነት ያሳጡታል። ከዚህ ባለፈ የተሸነፈ ሠራዊትን እጅ-እግር መቁረጥ ምኒሊክም ሆኑ ከእርሳቸው በፊት የነበሩ ገዥዎች ይፈፅሙት የነበረ ጭካኔ መሆኑ አይስተባበልም፤ እንዲያውም በአንድ ወቅት አፄ ቴዎድሮስ፣ በሸዋ ላይ ሾመውት የነበረው የምኒሊክ አጎት አቤቶ ሠይፈ ‹‹ሸፍቶብኛል›› በሚል አንኮበር ድረስ መጥተው ወግተው ድል ካደረጉት በኋላ ሠራዊቱ በሙሉ አንድ እጅና አንድ እግሩ እንዲቆረጥ ማድረጋቸውን ተከትሎ፡- «አፄ ቴዎድሮስ እጅግ ተዋረዱ የሸዋን ሰው ሁሉ እጅ ነስተው ሄዱ» ተብሎ መገጠሙ የጉዳዩን እውነታነት ለማሳየት በቂ ነው። (የእስልምና እምነት እና የኦሮምኛ ተናጋሪው ማሕበረሰብ ጥያቄዎች፣ በ‹‹ሕዳሴ አብዮት›› የሚኖራቸውን የመፍትሔ ሃሳብ በተመለከተ ሳምንት እመለስበታለሁ)