ታላቅ ሃገራዊ ውይይትና የመዝናኛ ምሽት በኦስሎ ኖርዌይ Sathurday Feb.3,2018 ከ14 ሰአት ጀምሮ!
ኢትዮጵያውያን ህብረታችን ውበታችን መገናኘታችን ደግሞ የጥንካሬያችን ምንጭ ነውና ኑ ሰብሰብ ብለን ስለሃገራችን እየመከርን ዘና እንበል፣፣
03.02.2018 ከ14: 00 ጀምሮ በባህላዊ ምግብና መስተንግዶ የታጀብ የመመካከሪያ ልዮ ስብሳባ ስለተዘጋጀ በኖርዌይ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ተጋብዛችዋል !!!
በዚህ ስብሰባ በሃገራችን ጉዳይ ላይ የተለያዩ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ከሚያራምዱት የልዩነት ሃሳብ ባሻገር በጋራ አንድ ሊያረጉን በሚችሉ ሃሳቦች ላይ እንወያያለን፣ እዚሁ ኖርዌይ በዜጎቻችን ላይ የሚደርሱ ችግሮችን በጋራ እንዴት መቁዋቁዋም እንደሚቻል እንማከራለን ::
በዚሁ ዝግጅት በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ላይ የሚሰሩ የፖለቲካ ድርጅቶችና ግለሰቦች በደብዳቤ የተጋበዝሁ በመሆኑ በዝተን የምንታይበት እና የበዛ ሃሳብ ማንሸራሸሪያ መድረክ ይሆናል::
እርሶም ከወዲሁ ቀኖኑን ከኛ ጋር ለማሳለፍ ያቅዱ !!!
ስብሰባችንን ታላቁ አርቲስት ሻንበል በላይነህ በባህላዊና ሐገራዊ ዘፈን ያደምቀዋል !!!
ቦታ : አንቲሬሲስት ሴንተር የስብሰባ አዳራሽ :: ( Storgata 25 , 0184 Oslo )
የስብሰባው አስተባባሪ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጭ ድርጅት በኖርዌይ ::