Thursday, July 27, 2017
Sunday, June 18, 2017
አገራዊ ንቅናቄው የአገራችንን የፖለቲካ ችግር የሚመጥን መፍትሄ ለመፈለግ ጠቃሚ ነው - ፕ/ብርሃኑ ነጋ።የኢትዮጵያ ጉዳይ ከልብ ያሳስበኛል - አቶ ሌንጮ ለታ
ሰኔ 10፣2009 ዓም
Thursday, June 15, 2017
ጋዜጠኛ ውብሽት ታዬ ለሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታ አቀረበ
አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆኖ ይሰራ የነበረው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ በ2003ዓም ሰኔ ወርላይ ከሌሎች 4 ሰዎች ጋር (ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ፣ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ፣ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሄር እናሂሩት ክፍሌ) የፀረ ሽብርተኝነት ህጉን ተላልፈሃል ተብሎ ክስ ተመስርቶበት የነበረ መሆኑን እና የ14 አመት የእስር ቅጣት እንደተወሰነበት የሚታወስ ነው።Tuesday, April 25, 2017
ህዝባዊ ወያኔ አርነት ትግራይ በውስጡ ያለው ቅራኔ ከፍተኛ ደረጃ መድረሱ ታወቀ።
ህዝባዊ ወያኔ አርነት ትግራይ በውስጡ ያለው ቅራኔ ከፍተኛ ደረጃ መድረሱን እና አስታራቂዎችን እስከመማፀን እንደደረሰ አስተማማኝ መረጃ እንደደረሰው የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን ሚያዝያ 16፣2009 ዓም ፣ምሽት ባስተላለፈው የአጭር ሞገድ ራድዮ ፕሮግራሙ ላይ ገልጧል።ክፍፍሉ ኢትዮጵያን በመጠኑ በተሰጠ መብት እንግዛ ወይንስ በአዋጁ መሰረት ማሰርና በመግደል እንቀጥል? በሚል ልዩነት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
በሌላ በኩል የክፍፍሉ መነሻ በአስተዳደር ጉዳይ ላይ ብቻ ሳይሆን ከሀገሪቱ በተዘረፈ ጉዳይ ዙርያ የሁሉም እጅ ከመኖሩ አንፃር አንዱ ከአንዱ የተሻለ መሆኑን ለማሳየት የሚደረግ ጥረት እና በእዚሁም ሳብያ አንድኛው ቡድን ሌላውን ለማሰር ከማሰብ የተነሳ እንደሚሆን ሲነገር ሰንብቷል።
ኢሳት በራድዮ ፕሮግራሙ ላይ እንደገለፀው ክፍፍሉን ተከትሎ በሕወሓት በእራሱ በተመረጡ የገለልተኛ ቡድን ደረግ የነበረው ሽምግልና ፍሬ ባለማስገኘቱ አትሌት ኃይሌ ገብረ ስላሴ፣ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ፣ የኢትዮጵያ ጥናታዊ አርበኞች ሊቀ መንበር ልጅ ዳንኤል ጁቴ እና ነጋዴዎችን ያካተተ መሆኑ ተሰምቷል።
የክፍፍሉ አሰላለፍ
1ኛ/ በጀነራል ሳሞራ የኑስ የሚመራው ስር የሚገኙ : –
– በወታደራዊ መረጃ ኃላፊ ሜጀር ጀነራል ገብሬ ዲላ ፣
– የሜቴከ (ብረታብረት ኢንጂነሪንግ) ኃላፊ,
– የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አባይ ወልዱ እና
– የአቶ መለስ ባለበት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ሲገኙበት
2ኛ/ በአቦይ ስብሐት የሚመራው ቡድን ስር የሚገኙ : –
– አቶ አባይ ፀሐዬ እና
– የደህንነት ኃላፊው አቶ ጌታቸው አሰፋ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
3ኛ/ ዶ/ር ደብረ ፅዮን እና ዶ/ር አርከበ እስካሁን ከየትኛው ቡድን እንደተሰለፉ አልታወቅም።
የኢትዮጵያ አምላክ ይፈርዳል ሳይውል ሳያድር
በድምፃዊ ኃይልዬ ታደሰ
Thursday, April 20, 2017
ድርቁ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የከፋ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ በ አለም አቀፍ ድርጅቶች ተገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 12 ፥ 2009)
በኢትዮጵያ ተከስቶ ያለውን የድርቅ አደጋ ለመከላከል ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ከሚያስፈልገው የአንድ ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ መካከል 23 ሚሊዮን ዶላር ብቻ መገኘቱ ተገለጸ።
የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ወቅታዊ ምላሽ አለመስጠቱን ተከትሎ ድርቁ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የከፋ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ የተባበሩት መንግስታት እና አለም አቀፍ የዕርዳታ ድርጅቶች አስታውቀዋል።
ባለፈው አመት በሃገሪቱ ተከስቶ የነበረውን ተመሳሳይ የድርቅ አደጋ ከመንግስትና ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ የተሻለ ድጋፍ ተገኝቶ እንደነበር ያወሳው ወርልድ ቢዥን በዘንድሮው አመት የተከሰተው የድርቅ አደጋ ለመከላከ ግን ከሁለቱም ወገኖች የበጀት ጉድለቱ ከፍተኛ ሆኖ መቀጠሉን የሰብዓዊ ዕርዳታ ተቋሙን ዋቢ በማድረግ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ሚድያ አውታር (ኢሪን) ዘግቧል።
የወርልድ ቪዥን የኢትዮጵያ ተወካይ የሆኑት ኤድዋርድ ብራውን አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራትና አለም አቀፍ ተቋማት ለአለም አቀፍ እርዳታ የሚሰጡትን ድጋፍ በመቀነስ ላይ በመሆናቸው ድርቁን በመከላከል ዘመቻውን ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑን አስረድተዋል።
በሃገሪቱ ዳግም ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ መንግስት ለመከላከል እያካሄደ ባለው ዘመቻ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑን ሃላፊው ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል በ222 ጊዜያዊ መጠለያዎች 400ሺ አካባቢ የሚጠጉ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ተረጂዎች ቢኖሩም በ58 ጣቢያዎች ብቻ ያሉት ከመንግስት ድጋፍ እያገኙ መሆኑን የዜና አውታሩ በዘገባው አቅርቧል።
ከ222ቱ መጠለያዎች መካከል 44 በመቶ የሚሆኑ የምግብ ድጋፍ እንደሚያገኙ የተገለጸ ሲሆን፣ ድርቁ በእስካሁኑ ቆይታው 200 ሚሊዮን ዶላር (ከአራት ቢሊዮን ብር) በላይ የሚገመት የእንስሳት ሞት ማስከተሉም ኢሪን አመልክቷል። በአራት ክልሎች ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ በተለይ በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል በነዋሪዎች ላይ የከፋ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ ይነገራል።
የምግብ እጥረቱ እያደረሰ ካለው ጉዳት በተጨማሪ የኮሌራ በሽታ ወረርሽኝ በሰዎች ህይወት ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ በተደጋጋሚ ሲገለፅ ቆይቷል።
በሶማሌ ክልል ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ያለው የድርቅ አደጋ 40 በመቶ አካባቢ የሚሆን የአካባቢውን እንስሳት እንደጨረሰ የተባበሩት መንግስታት የምግብና እርሻ ድርጅት መረጃ ያመለክታል። በተለይ በሶማሌ ክልል የእንስሳት ሃብታቸውን ያጡ አርብቶ አደሮች ከድርቁ ሙሉ ለሙሉ ለማገገም እስከ 10 አመት እንደሚፈጅባቸውም ተመልክቷል።
በተያዘው አመት የበልግ ወቅት በአብዛኛው የሃገሪቱ አካባቢ መጣል የነበረበትን ዝናብ በተጠበቀው መጠን ባለመጣሉ ምክንያት ድርቁ እስከቀጣዩ አመት ድረስ ቀጣይ እንደሚሆን ተሰግቷል።
መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ተርጂዎችን ቁጥር እየጨመረ በመሄድ ላይ መሆኑን በቅርቡ ቢያረጋግጥም ቁጥሩን ግን ከመግለጽ ተቆጥቧል።
መንግስትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 5.6 ሚሊዮን ለሚሆኑ ተረጂዎች አንድ ቢሊዮን ዶላር አካባቢ እንደሚያስፈልግ ከወራት በፊት ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። ይሁንና በእስከ አሁኑ ቆይታ 23.7 ሚሊዮን ዶላር ብቻ መገኘቱ ይፋ ተደርጓል።
በተያያዘ ዜና፣ የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ መንግስት የድርቅ አደጋውን በራሱ እየተቋቋመ ነው ሲሉ ሃሙስ ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል።
ይሁንና የውጭ የእርዳታ ድርጅቶች እና ሃገራት የሚያደርጉት ድጋፍ አናሳ በመሆኑ ድጋፋቸውን ሊያጠናክሩ ይገባል ሲሉ ሃላፊው ጥሪን አቅርበዋል።
ድርቁን ለመታደግ ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር አካባቢ እንደሚያስፈልግ ጥሪ ቢደረግም 93 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ተገኝቷል ሲሉ አቶ ምትኩ አክለው ገልጸዋል።
መንግስት ድርቁን ለመታደግ ተገኝቷል ያለው ገንዘብ የእርዳታ ድርጅቶች ካስታወቁት ጋር የ69 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ልዩነት እንዳለው ታውቋል።
የውጭ ሃገር የእርዳታ ተቋማት ለተለያዩ የሰብዓዊ ዕርዳታ የያዙትን በጀት በሶማሌ ክልል ተከስቶ ላለው የኮሌራ በሽታ ወረርሽኝ እንዲያዞሩት መጠየቃቸው አይዘነጋም።




