Sunday, December 8, 2013

የአና ጐሜዝና የኢህአዴግን “ፍቅር” እንመነው እንዴ?

ፖለቲካ በፈገግታ

የአና ጐሜዝና የኢህአዴግን  “ፍቅር” እንመነው እንዴ?
“ወሬኛም ያውራ ሃሜት ይደርድር
እኛስ ሆነናል ፍቅር በፍቅር
ሊያፈርስ አስቦ የሸረበውን
ተክቦ ሆኗል የሚያገኘው…”
ተቃውሞን የሚፈራ “ሰነፍ” መንግስት ብቻ ነው!
ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ለንባብ የበቃው The Reporter የእንግሊዝኛ ጋዜጣ፣ በፊት ለፊት ገፁ ላይ “GOMEZ In the House” ከሚል ርዕስ ሥር ያወጣው ምስል “Best picture of the year” ለመባል የሚበቃ ነው፡፡ ታሪካዊ ፎቶግራፍ እኮ ነው-ታሪክ የሚናገር! እኔማ ብዙ ነገሮችን በውስጤ አመላላስኩ፡፡ አሁን ማን ይሙት … የፓርላማ አፈጉባኤው የተከበሩ አባ ዱላ እና አና ጐሜዝ እንዲህ “ፍቅር በፍቅር” ይሆናሉ ብሎ የገመተ ነበር? የፕላኔታችን ምርጥ “አዋቂ” (ተንባይ) እንኳን ሊተነብየው የማይችለው እንግዳ ክስተት እኮ ነው፡፡ ሁለት ፈጽሞ ሊቀራረቡ ቀርቶ አንዳቸው የሌላቸውን ስም እንኳን የማያነሱ የሚመስሉን ሰዎች ድንገት እየተሳሳቁ ተጨባብጠው “ፍቅራችን ደራ!” በሚል ስሜት ሲያጓጉን ማየት ያስደነግጣልም፤ ያስገርማልም፡፡ እኔማ የሁለቱን ሰዎች ምስልና ነገረ ስራቸውን ስንት ጊዜ ትክ ብዬ እንዳስተዋልኩት አልነገራችሁም፡፡ እኔን እንዲህ ካስገረመኝ ተቃዋሚዎችን ደሞ ምን ያህል እንደሚያስገርም አስቡት! (ጐሜዝ በ9 ዓመታቸው ማሊያ ቀይረው ከች አሉ እንዴ ያስብላል!) እናላችሁ … ፎቶውን አይቼ አይቼ መጨረሻ ላይ ዓይኔን ማመን ስላቃተኝ “ከምራችሁ ነው?” አልኳቸው ድምጽ አውጥቼ፤ ምስሉ ላይ እንዳፈጠጥኩኝ፡፡
እንዴ … የ97 ምርጫ ጊዜ አና ጐሜዝ በኢህደዴግ ላይ የሰነዘረችው ትችትና ነቀፌታ “ዓይንሽ ላፈር” የሚያስብል ነበር እኮ! እናም ኢህአዴግ “ዓይንሽ ላፈር” ብሏት ነበር፡፡ (በዓይኑ መጣቻ!)
ጊዜ ደጉ ግን ሁሉንም ገለባበጠው፡፡ በነገራችሁ ላይ በጐሜዝና በአፈጉባኤው ተቃቅፎ ፎቶ መነሳት መደንገጤ ሊገርማችሁ አይገባም፡፡ ለምን መሰላችሁ … ራሷ አና ጐሜዝም ብትሆን በአዲስ አበባ በሚካሄደው 26ኛው የአፍሪካ፣ የካሪቢያን፣ የፓስፊክ አገራትና ከአውሮፓ ህብረት ጋር በጋራ በሚያደርጉት የፓርላማ አባላት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ፣ የኢትዮጵያ መንግስት “ቪዛ አይሰጠኝም” የሚል ስጋት እንደነበራት ከእንግሊዝኛው ሪፖርተር ጋር ባደረገችው ቃለምልልስ ገልፃለች፡፡
እኔ የምለው ግን … አፈጉባኤው ከጐሜዝ ጋር ያወረዱት ሰላም በግል ነው ወይስ ፓርቲውን ወክለው? (ብዥታው ይጥራ ብዬ እኮ ነው!) በነገራችሁ ላይ እርቁና ሰላሙ ከአንገት በላይ ቢሆን እንኳን፣ ኢህአዴግ ስሙን በከባዱ ያደሰበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው፡፡   እስቲ አስቡት … በ97 ምርጫ ለተቃዋሚዎች “ተደርባ አሳቅላናለች” በሚል ኩርፊያ፣ ዛሬ በ2006 ይከናወን በነበረ ትልቅ የፓርላማ አባላት ጉባኤ ላይ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ቪዛ ቢከለክል ኖሮ እንዴት embarassing እንደሚሆን? (“ተጠቃሽ የአገር ገፅ ግንባታ” ብየዋለሁ!) እንዲያም ሆኖ ግን “ቂመኛ ነው” የሚባለው አውራው ፓርቲ፤ እንዴት ለአና ጐሜዝ “አንጀተ ቀጭን” (ርህሩህ ለማለት ነው!) ሆነላት? የሚለው ጥያቄ አሁንም ከልቤ አልወጣም። (ሴቲቱ ቆቅ ሳትሆን አትቀርም!) ይገርማል እኮ! እዚህ ኢህአዴግና ተቃዋሚዎች ከ97ቱ የፖለቲካ ውጥንቅጥ በኋላ እርቅ ሳያወርዱ እንደተፋጠጡ አሉት፡፡ (አሁንም ድመትና አይጥ ናቸው እኮ!)
እኔ የምለው … ፎቶውን ትክ ብላችሁ ስታዩት ግን “ፍቅራቸው” ወይም የወረደው ሰላም የምር ይመስላል እንዴ? (የጐሜዝና የአፈጉባኤውን ማለቴ ነው!) እኔማ “እንዳንቺ አይደለንም!”፣ “ይብላኝ ላንቺ”፣ “ነገሩ ነው እንጂ ጩቤ ሰው አይጐዳም” የሚል መልዕክት ኢህአዴግን ከወከሉት ሰውዬ ሳቅ ውስጥ የማነብ እየመሰለኝ ተቸግሬ ሰነበትኩላችሁ  በነገራችሁ ላይ … የሁለቱን የፓርላማ ሰዎች የሳቅ ትርጉም በትክክል የገመተ ይሸለማል (በአውሮፓ ህብረት ስፖንሰር አድራጊነት!)
እናላችሁ … አና ጐሜዝ ከጉባኤው በኋላ በቤተመንግስት እራት ከመጋበዟም ባሻገር ከኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ በታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ዙሪያ መወያየቷን ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልፃለች። እንደውም የኢህአዴግ ባለስልጣናት ሃሳቧን ለመስማት ፈቃደኛ መሆናቸው ራሱ አስደንቋታል (“ምን ደግሰውልኝ ይሆን?” አለማለቷ ይገርማል!) እንዲህ ብላ ብቻ ግን አታበቃም - “ቅመሟ ጐሜዝ”! ከ97 ምርጫ በኋላ የፖለቲካ ምህዳሩ እየጠበበና ዲሞክራሲው እየቀጨጨ መጥቷል ብላለች-በይፋ። በመጨረሻም በሽብርተኝነት ተፈርዶባቸው የታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞችም መፈታት አለባቸው ያለችው ጐሜዝ፤ “የፀረ ሽብርተኝነት ህጉ ዲሞክራሲን ለማቀጨጭ እየዋለ ነው” በማለት በድፍረት ተናግራ ወደ አገሯ ተፈተለከች፡፡ (እኛም እኮ ሌላ አገር ቢኖረን…)
እኔ የምላችሁ … የመስቀል በዓል በዩኔስኮ ስሙ መስፈሩን ሰማችሁ አይደል? የኢቴቪ “አለርጂክ” አለብን የምትሉ የዲሽ ወዳጆችም ብትሆኑ፣ ከሌሎች ሚዲያዎች ሳትሰሙት እንደማትቀሩ እገምታለሁ፡፡ “የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ” በሚል ዘርፍ ነው “መስቀል” የተመዘገበው ተብሏል፡፡ (ኩራት ቢጤ ተሰማኝ!) እንደሰማነው ከሆነ ታዲያ … መስቀል በቅርስነት መስፈሩ ወደ አገራችን የሚመጡ ቱሪስቶችንና ተመራማሪዎችን ቁጥር ያበራክታል ተብሏል፡፡ (ይሄማ ምን ያጠራጥራል!) የእኔ ጥርጣሬ ምን መሰላችሁ? እንግዶቹ የጠበቁትን መስተንግዶና አገልግሎት አግኝተው፣ ሳይቀየሙን፣ በሰላም ወደ አገራቸው ይሸኛሉ ወይ የሚለው ነው፡፡ ከምሬ ነው … ያማሩ የሆቴል ህንፃዎች እኮ መስተንግዶ አይሆኑም! (ብቁ የመስተንግዶ ባለሙያዎች ያስፈልጋሉ ለማለት ነው!) ለመግባባት በቂ የቋንቋ ችሎታ ያላቸው፣ ከሆስፒታሊቲ ኢንደስትሪው ጋር በቅጡ የተዋወቁ የሆቴል ባለሙያዎች፣ አስጐብኚ ድርጅቶች ወዘተ … የግድ ነው፡፡ ያለዚያ የአገር ገፅ ግንባታው የአገር ገፅ እንዳያፈርስ ያሰጋል፡፡ (“አፍሶ መልቀም” አሉ!) የኢቴቪ ጋዜጠኞችም የመጣው ቱሪስት ሁሉ “Ethiopia is an amazing country; its people, its culture …፣” ወዘተ እንዲል መጠበቅ የለባቸውም፡፡ የቱሪስቶች ቁጥር የማይጨምረው ምናልባት የኢቴቪ ኢንተርቪው እያጨናነቃቸው ቢሆንስ? (ገራገር ግምት ናት!)
እናላችሁ … በዩኔስኮ መዝገብ ላይ ስለሰፈረው የመስቀል በዓላችን እያብሰላሰልኩ ሳለ ድንገተኛ ሃሳብ ከአዕምሮዬ ተገፍትሮ ሲወጣ ተሰማኝ፡፡ ወዲያው ጅራቱን አንቄ ያዝኩት፡፡ ሃሳቡ እንግዳ ቢመስልም ክፋት ግን የለውም፡፡ ምን መሰላችሁ? ዲሞክራሲ ባህላችንን ለምን “ከማይዳሰስ ዘመናዊ” ቅርስነት” በዩኔስኮ አናስመዘገበው? … የሚል ነው፡፡
(“አና ጐሜዝ ዲሞክራሲያችሁ ቀጭጯል” የምትለውን መርሳት ነው!) በዚያ ላይ “democracy is a process” (በኢህአዴግ ቋንቋ “እየወደቅን እየተነሳን ነው”) የሚል አባባል አለ አይደል? እናላችሁ … አል ስሚዝ የተባሉ አሜሪካዊ ፖለቲከኛ ምን ይላሉ መሰላችሁ - ስለ ዲሞክራሲ፡፡ “የዲሞክራሲ ህፀፆች የሚታከሙት በበለጠ ዲሞክራሲ ነው” (የ“ተማረ ይግደለኝ” ሳይሆን “በደንብ ያስተምረኝ” አልኩኛ!) ለእኛ አገር ቀረብ የሚል የመሰለኝን ደግሞ እነሆ - “ልማት ዲሞክራሲን ይፈልጋል፤ እውነተኛው የህዝብ ማሳተፍያ!” ይህን የተናገሩት ደግሞ የበርማ የፖለቲካ መሪና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ናቸው፡፡
እናንተ … ለካስ ኢህአዴግ “ዲሞክራሲ ለእኛ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው” የሚለው ወዶ አይደለም፡፡ (ዲሞክራሲ በአንድ ጀንበር ተቦክቶ የሚጋገር ሳይሆን ሂደት መሆኑን ግን አትርሱ!) እኔ የምላችሁ … ግን ተቃውሞን አምርረው የሚጠሉ፣ ተቃዋሚዎችን እንዴት ብለን አይተን የሚሉ መንግስታትና ገዢ ፓርቲዎች እጅግ “ሰነፎች” አይመስሏችሁም?” “የለም፤ አምባገነኖች ናቸው እንጂ!” ልትሉኝ ትችላላችሁ፡፡ እኔ ግን ምን እላለሁ መሰላችሁ? የሚቀድመው ስንፍናቸው ነው! ከዚያ ነው አምባገነንነታቸው የሚከተለው፡፡
የምን ስንፍና መሰላችሁ? ለህዝብ ቅሬታ በቂ ጆሮና ተገቢውን ምላሽ ያለመስጠት ስንፍና!! የህዝብን አንገብጋቢ ችግሮች በወቅቱ ያለመፍታት ስንፍና!! የስልጣን ኮርቻ ላይ ሲወጡ ለህዝብ የገቡትን ቃል ችላ የማለት ስንፍና!! የህዝብን መብትና ነፃነት በማን አለብኝነት የመደፍጠጥ ስንፍና!! ብዙ እንዲህ ያሉ … ስንፍናዎች ሲጠረቃቀሙ አምባገነንነት ይወለዳል ይላል-በልምድ ላይ የተመሰረተው ጥናቴ፡፡ በነገራችሁ ላይ … የህገመንግስት አንቀጽ ደልዞ ወይም የምርጫ ኮሮጆ ገልብጦ የስልጣን ዕድሜን ማራዘም  የ“ሰነፍ መንግስታት” መገለጫ ነው፡፡ የሥልጣን ጥመኞች እኮ “ሰነፎች” ናቸው-ከቤተመንግስት ወጥተው ተራ ህይወት መኖር ሞት የሚሆንባቸው!! (ካላመናችሁኝ ራሳቸውን ጠይቋቸው!!)  በመጨረሻ የዲሞክራሲ ዘብ ነኝ ለምትለው አና ጐሜዝና እጅ መጠምዘዝ አይቻልም ለሚሉት የፓርላማ አፈጉባኤ የንዋይ ደበበን ዘፈን ጋብዣቸው ልሰናበት፡፡

ተቃውሞን የሚፈራ “ሰነፍ” መንግስት ብቻ ነው!

Friday, December 6, 2013

Gov't Orders Closure Of Kenya-Ethiopia Border As Insecurity Worsens

http://www.youtube.com/watch?v=ICygrqiAAeE

Nelson Mandela, anti-apartheid icon and father of modern South Africa, Dies

 Nelson Mandela, the revered statesman who emerged from prison after 27 years to lead South Africa out of decades of apartheid, has died, South African President Jacob Zuma announced late Thursday.
Mandela was 95. (CNN)
nelson-mandela
“He is now resting. He is now at peace,” Zuma said. “Our nation has lost its greatest son. Our people have lost a father.”
“What made Nelson Mandela great was precisely what made him human,” the president said in his late-night address. “We saw in him what we seek in ourselves.”
Mandela will have a state funeral. Zuma ordered all flags in the nation to be flown at half-staff from Friday through that funeral.
Mandela, a former president, battled health issues in recent months, including a recurring lung infection that led to numerous hospitalizations.
With advancing age and bouts of illness, Mandela retreated to a quiet life at his boyhood home in the nation’s Eastern Cape Province, where he said he was most at peace.
Despite rare public appearances, he held a special place in the consciousness of the nation and the world.

Wednesday, December 4, 2013

በመርካቶ ዛሬ በተነሳው የእሳት አደጋ ዙሪያ አዳዲስ መረጃዎች



               አሁን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ በመርካቶ አካባቢ በቀድሞው ቦምብ ተራ (የአሁኑ ጆንያ ተራ) የተነሳው ቃጠሎ በመጨረሻም በቁጥጥር ስር ውሏል። በአደጋው ከቀደም ብለን በሰበር ዜና 4 ሰዎች መጎዳታቸውን የዘገብን ሲሆን አሁን ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር ከ10 በላይ ማደጉ ጨምሮ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በአደጋው የደረሰው የንብረት ጥፋት ከፍተኛ ሲሆን እስካሁን በቁጥር የተቀመጠ መረጃ አልተገኘም። ሆኖም በርካታ ሱቆች ግን ወድመዋል።
ቀደም ሲል ከ2 ሰዓት በፊት የዘገብነው ዜና ከዚህ ሥር አለ።
በመርካቶ የተነሳው የእሳት አደጋ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ አልበረደም። የዘ-ሐበሻ የአዲስ አበባ ዘጋቢዎች እንዳሉት ከሆነ ከቀኑ 8 ሰዓት የተነሳው እሳት ቃጠሎ በእሳት አደጋ ብርጌድ ሊጠፋ ባይችልም 4 ሰዎች በቃጠሎ አደጋ ደርሶባቸው ወደ ተክለሃይማኖት ሆስፒታል ተወስደዋል።
እሳቱ በተለምዶ ቦንብ ተራ (የአሁኑ ጆንያ ተራ) ተብሎ የሚጠራውን አካባቢ ሁሉ መካለሉን፤ በአካባቢው የዘይት ሱቅ በመቃጠሉ የእሳት አደጋው መባበሱን የገለጹት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች የእሳት አደጋው ብርጌድ አደጋውን ሊቆጣጠር ያልቻለው በአካባቢው ያሉ ሱቆች በልብስ የተጨናነቁ በመሆናቸው ተብሏል። የእሳት አደጋው ኮልፌ፣ እንዲሁም አራዳ ድረስ በመሄድ የማጥፊያ ውሃዎችን እየቀዳ እንደሚገኝ የገለጹት ምንጮች ለምን መርካቶ አካባቢ ውሃ እንደማይቀዱ የተገለጸ ነገር የለም።
እስካሁን ድረስ ወደ 3 የሚጠጉ የአስፓልት መሸጋገሪያ ያላቸው መንግዶች ስር ያሉ ሱቆች መቃጠላቸውን ያስታወቁት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከአየር መንገድ እሳቱን ለማጥፋት እግዛ ተገኝቷል ብለዋል። በአካባቢው የ እሳት አደጋውን ተከትሎ ዝርፊያ ሊከሰት ይችላል በሚል ፍራቻ እንዳለ የገለጹት ዘጋቢዎቻችን ነጋዴዎች ንብረታቸውን በግልጽ መኪናዎች በመጫን ከአካባቢው እየሸሹ ነው ብለዋል።
በሌላ በኩል በአካባቢው ያሉ ነጋዴዎች የእሳት አደጋ አጥፊዎች በቅድሚያ እሳቱን ከማጥፋት ይልቅ በገንዘብ እንደሚደራደሩ ያላቸውን ብሶት ለዘ-ሐበሻ ዘጋቢ ተናግረዋል። አንዳንድ ነጋዴዎች እሳቱ አደጋ ሆን ብሎ እንዲባባስ እና ቶሎ እንዳይጠፋ እየተደረገ ያለ ሴራ አለ ብለው የሚያምኑ ሲሆን “መንግስት ቦምብ ተራ(ጆንያ) ተራን ለማፍረስና ለባለሃብት ለመስጠት እየተጠቀመበት ያለው ሴራ ሊሆን ይችላል” ሲሉ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ።
ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እናቀርባለን።
http://www.youtube.com/watch?v=Qt7I30g7Kgs#t=11

Tuesday, December 3, 2013

“…it was not easy for a non Tigrian PM to assert his role as PM ” Ana Gomez

Ana GomezAna Gomes is coordinator and spokesperson of the foreign affairs committee for her political group, the Social-Democrat. With 200 members the Social-Democrat is the second largest group within the European Parliament. For Ethiopia and Ethiopians though Ana Gomes is best remembered for her role as the leader of the EU election observers’ team during the 2005 crisis-induced general election in Ethiopia. She has had a troubled relationship with Ethiopia’s late Prime Minister Meles Zenawi, who she still calls “a dictator,” after she published her report in which wrote the election was massively rigged. Eight years later, Ana Gomes came to Ethiopia to participate in the just concluded 26th ACP-EU parliamentary meeting. Her arrival in Addis Ababa caught many, who thought she would never be allowed to set foot in Ethiopia, by a surprise. Please read her exclusive interview with Addis Standard during the 26th ACP-EU parliamentary meeting.
AS - Your question to the development commissioner Andris Piebalgs was on Ethio-Djibouti road project funded by the EU. The commissioner replied EU no longer funds road projects in Ethiopia because construction work is given to companies without auction or given to friendly companies. What happened to the Ethio-Djibouti road project at the end?
Ana- Gomes - I don’t know if it was the auction. I raised the issue because some very concerned European friends told me about that because there is a lot of money from the European taxpayers which was supposed to be directed to development that was diverted. I only talked about the road. But I just confirmed with the EU commission representative that it’s indeed two contracts; one, a railway between Addis Ababa and Djibouti; the EU funding was around 45 million Euros, and two, 50 water tunnels project, by the same company worth 20 million Euros. The company was an Italian company called CONSTAT. That company adds Ethiopian Contractors/subcontractors. Obviously it was chosen by the ministry of finance with EU agreement. It’s a project that has gone very wrong because nothing has been achieved, and the money has been deviated.  EU has started investigation, arbitration is going on; it also involved your government.  And support has been cancelled. They are apparently trying to recover the money from the company. But the money has gone, so the investigation goes on. I was promised for the details by the European commission. It doesn’t mention road. It’s a bit weird however that the EU development commissioner mentioned road construction. And the EU signing new agreement to fund road projects in Ethiopia is contradictory. I think it’s important to clarify all these contradictions for the sake of taxpayers in Europe and also for the Ethiopian people. I am heartened by the fact that PM Hailemariam [Desalegn] has started taking measures even against the high officials who are involved in corruption. So I have to find out. In fighting corruption the main element is transparency. So this element has to be put out for the people to know. There are some things to be checked.
AS - EU funded hydropower project-Gilgel gibe 3 was given without auction to Salini Construction, an Italian company. A few months after it went operational part of it caved in and was closed. The EU criticized openly the handing out of the construction without auction. But it didn’t decide not to fund hydropower projects.
Ana Gomes - I am very interested to learn about that. I need to note down that information. I will find out about it and ask the EU.  I am glad you asked this. I have not been able to follow in detail all this development processes because I was not in the EU development committee.
AS - ACP-EU joint parliamentary assembly has democratic agenda. The speaker of the house of people’s representative of Ethiopia Abadula Gemeda said, “we have achieved a lot in building democracy, peace and good governance.” Do you buy that? Do you think a lot has been achieve?  
Ana Gomes - No! In many respect I see a lot of the old ways. Meles was an expert in using jargons such as good governance, the rule of law, democracy, sustainable development, but in practice doing just the opposite. It was a smart leadership which uses politically correct languages for Europeans and Americans consumption. But the practice was really oppressive. What I saw during Meles Zenawi was a dictatorship. I have lived in dictatorship in my own country. I believe this persists in the mind set of many authorities.
But at the same time, I realize there is indeed some opening, some realization [that] Ethiopia can’t continue this way.  Ethiopia needs change. Even some of the people who have that politically correct speech that everything has been achieved in Ethiopia in public, in private conversation with me they acknowledged that Ethiopia needs change, and that it is the time to really promote important, drastic changes. In that sense I welcome the move that the PM Hailemariam has initiated the prosecution of high officials, even a minister charged with corruption. I hope this will be the first step in the right direction. At the debate we were discussing the independence of the judiciary.  I used the debate to say that Judicial Independence doesn’t exist in Ethiopia, although it’s stated. I recalled the judges who flee the country in 2005 because they refuse to tamper with the conclusion on the inquiry about the massacre in 2005. They were pressed by the [late] PM and the government to do that. These were very courageous people who put all their lives and their families [at risk].  I also highlighted that trials of all political prisoners but in particular journalists Eskinder Nega, Wubeshet Taye, Riyot Alemu and others like DebebeEshetu; [political] leaders Andualem Arage e.t.c. were not fair; all the people [including] Europeans who were able to be present at some of these trials said they [the prosecutors] never produced any significant evidence against them and indeed the trials were not fair.  So I hope I have made this appeal today here.
AS - But they faced terrorism charges…?
These terrorist charges are not credible, so I appeal for their liberation in the spirit of openness. You have now a sort of dual register. In public it said one thing in private it acknowledges that Ethiopia must change. Or Ethiopia needs support to change. In that context, indeed bold decisions should be taken to liberate these people, because some of these people are icons of the younger generation. Very educated, qualified generation which Ethiopia needs to develop itself. I receive a mail, a standard letter everyday from an Ethiopian who manages to flee the country and who is somewhere in Kenya, Uganda ….Nigeria asking me to write a letter to the UNHCR saying they need political asylum. So I know Ethiopia looses the best, most qualified generation not only because of lack of jobs but because there is politically closed environment with which these young qualified people cannot live. I know Ethiopia faces serious terrorist threat as we all do, Ethiopia in particular because of the neighborhood and the tension that has been built up by Meles Zenawi between Muslims and Christians inside Ethiopia which was not an issue in 2005 but in the meantime became a big source of concern.  If the government continues the old ways repressing this bright, younger people who are now connected to the world in a way the regime cannot control them via the twitter, and facebook, and so on. Obviously many of these young people will be driven into the hands of radicals and extremists. Even to be recruited by terrorists.  It is what we see happening in other countries in the region. So, it is very important to open up democratically for the security of the country.  Read more

የኢህአዴግ የድርድር ጥያቄ– ከፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ)


ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም
አንድ፣ ኢሳት ፣ ኢህአዴግን እና ግንቦት7ትን የተመለከተ ዘገባ ካቀረበ በሁዋላ አንዳንዶች ዜናውን ሲጠራጠሩት ተመልክቻለሁ፣ ያሽሟጠጡም አልታጡም። መጠራጠርም፣ ማሽሟጠጥም የሰውልጅ ባህሪ በመሆኑ አልገረመኝም። ትንሽ የገረመኝ አንዳንድ “ጋዜጠኞች” መረጃውን ካገኙ በሁዋላ በራሳቸው መንገድ አጣርተው ሀቁን ማውጣት ሲችሉ እነሱም እንደሌላው መልሱን በማንኪያ እንዲቀርብላቸው መፈለጋቸው ነው። ጋዜጠኛ “ጥቆማ” ከተሰጠው ተመራምሮ፣ የምርምር ስራውን ይጽፋል እንጅ እንደ አንባቢ መልሱ ተዘጋጅቶ እንዲቀርብለት አይጠብቅም፣ ጥያቄ መጠየቅማ ማንም ይጠይቃል፣ ጋዜጠኛን ጋዜጠኛ ወይም ተመራማሪ የሚያደርገው ለጠየቀው ጥያቄ ላይ ታች ብሎ መልስ ማቅረብ ወይም በአሰባሰባቸው መረጃዎች ላይ ተንተርሶ ትንተና መስጠት ሲችል ነው ( በሁለተኛው መስፈርት መሰረት ተመስገን ደሳለኝን እና በእስር ላይ የሚገኘው ውብሸት ታየን አደንቃለሁ)።
ሁለት፣ ዜናውን እንደሰማሁ መጀመሪያ የመጣልኝ ጥያቄ “እና ምን ያስገርማል?” የሚለው እንጅ፣ “ድርድሩ የተጠየቀው መቼና በእነማን በኩል ነው?” የሚለው አልነበረም። የአለም የፖለቲካ ታሪክ በግጭትና በድርድር የተሞላ ነው። “ድርጅቶች ይጋጫሉ፣ ይደራደራሉ፣ ምን ያስገርማል?”፣ በፖለቲካ ትግል” በመቃብሬ ላይ ..” የሚባል ነገር የለም። “ለምን ሰበር ዜና ሆነ ታዲያ?’ እንዳትሉኝ፣ ሰበር ዜና ማለት አስገራሚ የሆነ ዜና ማለት አይደለም ።

ሶስት፣ ቀጥሎ የመጣልኝ ጥያቄ “ኢህአዴግ ከግንቦት7 ጋር መደራደር ለምን ፈለገ?” የሚለው ነው። ይህን ጥያቄ ለመመለስ ” የፖለቲካ ድርጅቶች የእንደራደር ጥያቄ የሚያቀርቡት መቼ ነው?” የሚለውን ማየት ነበረብኝ። የፖለቲካ ድርጅቶች በአብዛኛው ለድርድር የሚቀመጡት ህልውናቸውን ለማቆየት ወይም ተደራድሮ የሚገኝ ጥቅም ሳይደራደሩ ከሚገኝ ጥቅም ( ጉዳት) የተሻለ ሆኖ ሲያገኙት ነው። በዚህ ንድፈሀሳብ ላይ ተመስርቶ ኢህአዴግ እና ግንቦት7 አሁን ያሉበትን ቁመና መፈተሽ ይገባል። ኢህአዴግ ከመለስ በሁዋላ ኢህአዴግ አለመሆኑ ይታወቃል።ሊቀመንበሩ ድርጅቱን ይዞ ለመቀጠል ተቸግሯል፣ (ምናልባትም በቅርቡ ይፋ የሚሆኑ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከፍተኛ የገንዘብ ችግር አጋጥሞታል)፣ የ ህዝቡ ልብ እንደሸፈተ አውቋል፣ ወጣቱ ለውጥ እንደሚፈለግ ተረድቷል፣ ሰራዊቱ የሚተማመንበት ሀይል እስኪያገኝ እንጅ እንደሚከዳው ተገንዝቧል። በአጠቃላይ መጪው ጊዜ ለኢህአዴግ ብሩህ አለመሆኑን ግንባሩ ጠንቅቆ ያውቃል። በዚህ አደጋ ውስጥ ሆኖ ጊዜ ለመግዛትና ድርጅቱን ለማጠናከር የድርድር ጥያቄ ቢያቀርብ አይገርምም።
ግንቦት7 ለኢህዴግ “አጣዳፊ ጠላት” (immediate threat) ሆኗል እያልኩ አይደለም፣ ነገር ግን እምቅ ጠላት ( potential threat) መሆኑን አልጠራጠርም ። አንድ ድርጅት ለሌላው ድርጅት አጣዳፊ ጠላት የሚሆነው ፣ አሁን ባለበት ሁኔታ፣ ከተቃራኒው ድርጅት የበለጠ ወይም ተመጣጣኝ የሆነ የሀይል ሚዛን ሲኖረው ነው። ግንቦት7 ኢህአዴግን ዛሬውኑ ለማስወገድ አይችልም ምክንያቱም ከኢህአዴግ የሚበልጥ ወይም ተመጣጣኝ የሆነ ሀይል የለውምና ፤ ነገር ግን በጊዜ ሂደት እንደሚያስወግደው መገመት ይቻላል፣ ከመለስ በሁዋላ ያለውን ሁኔታ ብታጠኑ የኢህአዴግ የሀይል ሚዛን ወደ ታች እየወረደ፣ በአንጻራዊ መልኩ የግንቦት 7 የሃይል ሚዛን ደግሞ ወደ ላይ እየወጣ ነው፣ የ ግንቦት7 መሪዎች በዚህ አመት የሀይል ጥቃት እንደሚጀመሩ አስታውቀዋል፣ በዚህ አመት ቀርቶ በሚቀጥሉት 3 አመታት ጥቃት ከፈጸሙ እያደጉ መሆኑን የሚያሳይ ነው ( 4 ፓይለቶች መክዳታቸውንም አንዘንጋ)። የፖለቲካ ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ሁለት አይነት ሀይል አለ። አንዱ መቺው ሀይል ( hard power) ሲሆን ሌላው ደግሞ መለስተኛው ሀይል ( soft power) ነው። መቺው ሀይል የሚባለው ወታደራዊው ሀይል ነው። በዚህ በኩል ኢህአዴግ ከግንቦት7 በብዙ እጅ የሚልቅ ጉልበት አለው። ነገር ግን ግንቦት7ትም በዚያው ጎዳና እየተጓዘ መሆኑን መርሳት የለብንም።
መለስተኛ ሀይል (soft power) የሚባለው ደግሞ የፕሮፓጋንዳ መሳሪያዎችን፣ ጥራት ያለው የሰው ሀይልን ( መሪም ተከታይም)፣ ህዝባዊ ድጋፍ ፣ የካፒታል አቅም ፣ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት የመሳሰሉትን ያካትታል። ግንቦት7 በዚህ በኩል ከፍተኛ ጉልበት መገንባቱን መመስከር ይችላል። ከኢህአዴግ ተመጣጣኝ የሆነ ካፒታል ባይኖረውም፣ ከሌሎች ድርጅቶች የተሻለ ካፒታል( ገንዘብ)እንደሚኖረው ከስራዎቹ መገመት ይቻላል ። የተማሩ ሰዎችን በመያዝ በኩልም፣ ከኢህአዴግ ቢበልጥ እንጅ አያንስም። በፕሮጋንዳውና በህዝብ ድጋፍ በኩልም እንዲሁ። እንዲያውም የግንቦት7 የፕሮፓጋንዳ ማሽኖች ከኢህአዴግ የተሻሉ ለመሆናቸው ብዙ አስረጅ አይጠይቅም፣ የግንቦት7 ራዲዮና ዌብሳይት እስከዛሬ ሳያቋርጥ እየሰራ ነው፣ ጠንካራ የፓልቶክ ደጋፊዎችም አሉት። ኢህአዴግ ራሱ የሚሰራላቸው ፕሮፓጋንዳም ቀላል አይደለም። ኢህአዴግ ቢያንስ በውጭ ያለውን ድጋፉን፣ በተለይም ለጀመራቸው የአባይ እና ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ገንዘብ ለመለመን ሲል ግንቦት7ን ለድርድር ቢጠይቀው አይገርምም። ኢሳት የግንቦት7 ነው ብሎ ስለሚያስብም፣ ኢሳትን እንዲያስቆምለት ልደራደርህ ቢል አሁንም አይገርምም። (በኢሳት ላይ እንኳ ቀልድ የለም፣ መደራደር ከፈለገ ከኢሳት ጋር እንጅ ከግንቦት7 ጋር ሊሆን አይችልም፣ ምክንያቱም ግንቦት7 ስለኢሳት ምንም የሚያገባው ነገር የለምና፣ ከኢሳት ጋር ድርድር ከተጀመረም ለኢሳት የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ዙሪያ እንጅ፣ ከስራው ጋር የተያያዘ እንደማይሆን መቶ በመቶ እርግጠኛ ነኝ)

አራት፣ ኢህአዴግ ከግንቦት7 ጋር ብቻ ነው ወይ ድርድር የመረጠው? እኔ ባለኝ መረጃ ኢህአዴግ በእነ ፕ/ር ኤፍሬም ይስሀቅ በኩል ላለፉት 4 ወራት ከእነ አቶ ሌንጮ ለታ ድርጅት ጋር ሲነጋገር ነበር። ይህን ጠንቅቄ አውቃለሁ። ከኦብነግ ጋርም እንዲሁ ተደጋጋሚ የድርድር ጥያቄዎች ቀርበዋል። እነዚህ ድርጅቶች በፓርላማ “አሸባሪ” የተባሉ ናቸው። እና ለግንቦት7 ጥያቄ ቢያቀርብ ምን ይደንቃል? ፖለቲካ እኮ ፊት ለፊት የምትናገርውና በውስጥ የምታደርገው የተለየ ነው። That is politics. በነገራችን ላይ ” አንደኛው የአለም ጦርነት የተጀመረው በድብቅ በሚካሄድ ፖለቲካ የተነሳ ነው” ተባለና ፖለቲካ ግልጽነት እንዲኖረው ተብሎ አዲስ አስተሳሰብ ለረጅም ጊዜ ተራመደ። ፖለቲካ ግን ዛሬም ፊትና ጀርባ እንደያዘ ቀጥሎአል።
አምስት፣ “ጥያቄው በእነማን በኩል ቀረበ?’ የሚለውንም ለራሴ አንስቻለሁ። የድርጅቱ መሪዎች መልሱን ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም፣ ነገር ግን የራሴን ግምቶች አስፍሬአለሁ። አንድ፣ በቅርቡ በእነአቦይ ስብሀት የተመራ ቡድን አሜሪካ ከርሞ ሄዷል። ሁለት፣ ፕ/ር ኤፍሬም አሜሪካ ከርመዋል፣ ኦነጎችን ለማስታረቅም ላይ ታች ሲሉ ከርመዋል። ሶስት፣ በቅርቡ የአውሮፓ እና የካረቢያን አገሮች ስብሰባ በአዲስ አበባ ተካሂዷል፣ ብዙ ዲፐሎማቶችም አዲስ አበባ ነበሩ። አራት፣ ኖርዌይና ሆላንድ ሁሌም ተቃዋሚዎችን ለማቀራረብ ይሰራሉ። ይዋል ይደር እንጅ ትክክለኛውን መልስ እናገኛለን። መልሱ ግን ከጠቀስኳቸው ሰዎች ወይም አገሮች በአንዱ ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ። የእንደራደሩ ጥያቄ ለመቅረቡ ግን መቶ በመቶ እርግጠኛ ነኝ። እስከዛው እንደ ጋዜጠኛ መላ ምት በማስቀመጥ ምርምራችን መቀጠሉ ተገቢ ነው።

ስድስት፣ ግንቦት7 ለምን ይህን ድርድር ይፋ ማድረግ ፈለገ? ኢህአዴግ አስቀድሞ በኢቲቪ ” ከግንቦት7 ጋር ሲያደርግ የነበረው ድርድር ከሸፈ” ብሎ መግለጫ ቢሰጥ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስቡት? የግንቦት7 ደጋፊዎች የድርጅቱን መሪዎች በጥሩ አይን የሚያዩዋቸው አይመስለኝም፤ ግንቦት7ትም ውስጥ አለመተማመን ይፈጠርና ድርጅቱን ከሁለት ሊከፍለው ይችል እንደነበር መገመት ይቻላል፣ ዲሞክራሲያዊ ነኝ የሚል ድርጅት ከአባሎቹና ከህዝቡ የሚደብቀው ነገር መኖር የለበትም። ግንቦት7 በመግለጫው “ድርድር መደረግ ካለበት ከሁሉም ድርጅቶች ጋር ነው፣ ሁሉንም ነገር ግልጽ እናደርጋለን የምንደብቀው የለንም” ብሎአል። ትክክል ነው። እውነተኛ ድርድር ሲጀመር ለጊዜው ይፋ የማይወጡ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ፣ ድርድር ተጠየቅሁ ብሎ መግለጫ መስጠቱ ግን የሚገርም አይመስለኝም። ግንቦት7 መረጃውን ከኢህአዴግ ቀድሞ ይፋ ማድረጉ ድርጅቱን ከመከፋፈል ማዳን ብቻ ሳይሆን ንቅናቄው ከኢህአዴግን አንድ እርምጃ ቀድሞ የ ሚያስብ መሆኑን ለማሳየትም ጠቅሞታል።
በአገር ውስጥ ያሉ ጋዜጠኞች በኢህአዴግ በኩል ያለውን መልስ ይዘውልን እንደሚቀርቡ ተስፋ እናድርግ።

Monday, December 2, 2013

ሰማያዊ ፓርቲ አፄ ምኒልክ ያረፉበትን 100ኛ አመት ሊያከብር ነው


ኢ/ር ይልቃል ከደጋፊዎቻቸውና ከጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ጋር ይወያያሉ
ሰማያዊ ፓርቲ አፄ ሚኒልክ ያረፉበትን መቶኛ አመት ታህሳስ 3 ቀን 2006 ዓ.ም በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚያከብር የገለፁ ሲሆን፤ የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ትናንት ወደ ጀርመን በማቅናት ከፓርቲው ደጋፊዎችና ከጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ይወያያሉ ተባለ፡፡ አፄ ምኒልክ ያረፉበትን መቶኛ ዓመት ለመዘከር በሚዘጋጅ የፓናል ውይይት፣ በምኒልክ ዙሪያ የኢትዮጵያ ምሁራን የጥናት ጽሑፍ እንደሚቀርብ የገለፁት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው በጽሑፎቹ ዙሪያ ሌሎች የአፍሪካ ምሁራንም ይወያያሉ ተብሏል፡፡ እንጦጦ የሚገኘው የምኒልክ ቤተ መንግስትን ጨምሮ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የአፄ ሚኒልክ ፋውንዴሽን የሆነውና ባዕታ ማሪያም አጠገብ የሚገኘው የካህናት ማሰልጠኛና የአረጋዊያን መርጃ እንደሚጐበኙም አቶ ብርሃኑ ተናግረዋል፡፡ አፄ ምኒልክ በዘመናቸው ምን ዓይነት መሪ እንደነበሩ የሚያሣይ የፎቶ ኤግዚቢሽን በፓርቲው ጽ/ቤት እንደሚካሄድም ተጠቁሟል፡፡ ፓርቲው፣ የአፄ ምኒልክን ህልፈት መቶኛ አመት ለመዘከር ለምን እንደፈለገ የተጠየቁት አቶ ብርሃኑ፣ አፄ ምኒልክ ኢትዮጵያን ከቴክኖሎጂ ጋር ከማስተዋወቃቸውም በተጨማሪ በአድዋው ጦርነት ጥቁሮች ነጮችን ማሸነፍ እንደሚችሉ ያሳዩ ቆራጥ መሪ ናቸው ብለዋል፡፡ “በእርሳቸው ዘመን ቴክኖሎጂ እንደ ሰይጣን ይቆጠር ነበር” ያሉት አቶ ብርሃኑ፣ ከካህናቱና ከቀሳውስቱ ጋር እየተሟገቱ ታላቋን ኢትዮጵያን ቴክኖሎጂ ቀመስ በማድረጋቸው ሊዘከሩ ይገባል ብለዋል አፄ ሚኒልክ በወቅቱ ባቡር፣ ስልክ፣ መኪና፣ ፖስታ፣ ሆቴልና ባንክ በመሳሰሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ህዝባቸውን ተጠቃሚ አድርገዋል ያሉት አቶ ብርሃኑ፣ “ዛሬ ስለ ባቡርም ሆነ ስለአጠቃላይ የቴክኖሎጂ ልማት ስናወራ ቅድሚያ መታወስ ያለባቸው አፄ ሚኒሊክ ናቸው” ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል፤ የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል በውጭ አገራት ከሚገኙ ደጋፊዎች በቀረበላቸው ግብዣ ትላንትና ወደ ጀርመን መጓዛቸውን አቶ ብርሃኑ ገልፀዋል፡፡ በሁለት ሳምንታት የጀርመን ቆይታ፣ ኢ/ር ይልቃል በሶስት የአገሪቷ ከተሞች ከደጋፊዎች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ የገለፁ ሲሆን፤ ከጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለመወያየት ፕሮግራም ተይዞላቸዋል ብለዋል - አቶ ብርሃኑ፡፡ ኢ/ር ይልቃል ወደ አሜሪካ በማምራት በሰባት ስቴቶች የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታና የፓርቲውን እንቅስቃሴ በማስተዋወቅ ደጋፊዎችን እንደሚያደራጁ አቶ ብርሃኑ ተናግረዋል።