Monday, January 27, 2014

ዳር ሆነው የሚመለከቱት የጎሳ ፖለቲካ ምሱ “ደም”!!


“ህወሃት” የሚባለው የትግራይ ነጻ አውጪ ትግራይን መቼና ከማን ነጻ እንደሚያወጣ በውል የተቆረጠ ቀን ባይኖርም ህገ መንግስታዊ ዋስትና ግን አለው በሚል እየተተቸ 23 ዓመታትን አስቆጥሯል። አገር እየመራም ነጻ አውጪ፣ በረሃም እያለ ነጻ አውጪ፣ በአህጉርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲወከልም ነጻ አውጪ!!
ይህንን የተለመደና ግራ የሚያጋባ እውነት ያነሳነው ወደን አይደለም። ይህ የህወሃት ግልጽ መለያና ከመለያው የሚነሳው ትንታኔ ለማንም የተወሳሰበ ይሆናል ብለንም አንገምትም። ኢህአዴግ የሚባለው የ”ሎሌዎች” ስብስብ ያበጀውና የሚመራው ህወሃት ከሌሎቹ በተለየ በነጻ አውጪ ስም 23 ዓመት አገር ሲገዛ ሌሎቹ “የነጻ አውጪ” ስም አለመያዛቸው ግን ሁሌም ሊመረመር የሚገባው ጉዳይ ይመስለናል።
አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ “ነጻ” መውጣት ያለባቸው ህወሃቶች ሳይሆኑ ሌሎች የአገራችን ህዝቦች፣ የትግራይን ንጹሃንን ጨምሮ ነው። ህወሃት ሲጠነሰስ ጀምሮ የነበሩትን ቀደምት አመራሮች በሂደት እየበላ አራት ኪሎ የደረሰው፤ ህወሃት መጥበብ የጀመረው ገና ከጥንስሱ ጊዜ ጀምሮ ነው። ስለ ህዋሃት የሚወጡ የምስክሮች ሪፖርቶችና መረጃዎች እንደሚያረጋግጡት ህወሃት በደም የታጠበ፣ በደም የተለወሰ፣ የበርካታ ንጹሃን ደም ያጨማለቀው፣ ታሪኩ ሁሉ በደም ዙሪያ የተሰራ፣ አሁንም ከዚሁ የደም ቁማር ነጻ መሆን ያልቻለ መሆኑን ነው።
ህወሃት ግዛቱን እያሰፋ ሲሄድና አጋጣሚው ሲያመቸው ከተቋቋመለት መሰረታዊ ሃሳቡ ዘሎ “መንግስት” መሆን ሲያምረው “ኢህአዴግ” የሆነው ዓላማውን በወጉ ከ”መጥበብ ወደ መስፋት” በመቀየር ሳይሆን “በሰፍቶ መጥበብ ውስጥ” እየተጫወተ አገርና ህዝብን ረግጦ ለመግዛት ነው። ለዚህም ይመስላል ኢህአዴግን አሁን ድረስ “አገዛዝ” ከማለት በዘለለ በመንግሥትነት ሊጠሩት የማይፈልጉ የበረከቱት።
በግብር እንደታየው በህወሃት “የሰፍቶ መጥበብ” ጨዋታ ውስጥ ቅድሚያ ትግራይ መወለድ፣ ሲቀጥል የትውልድ ቦታንና ስምን በመቀየር ማጭበርበር፣ ከዛም ታማኝ መሆን፣ ከሁሉም በላይ አነስተኛ ክልል በሚል ስልታዊ አካሄድ ብርና ኮብራ እየሸለሙ ማታለል፣ የአገዛዙ መለያ ሆነ። አሁን ድረስም ይዘቱ ባይቀየርም አፈጻጸሙ ግን ከክልል ወደ አውራጃ፣ ከአውራጃም ወደ ወረዳና ቀበሌ፣ ከወረዳና ቀበሌ ወርዶ ስጋና ደም የሚቆጠርበት የስልጣን ቅርምት ደረጃ “እድገት” አሳይቶ ይገኛል።
በዚህ መልክ በተዋቀረው የህወሃት አገዛዝ ቁጥጥርና ክትትል አስቸጋሪ በመሆኑ አገሪቱ በሙስና በሰበሰች። ሙስናው ፈር ለቅቆ በድሃው ህዝብ ላይ ነገሰ። አወቃቀሩ ስርዓቱን በመታደግ ላይ የተመሰረተና የህወሃትን ባለጊዜዎች ስልጣን ማስጠበቅ በመሆኑ ሁሉም ነገር ሸተተ፤ ገለማ። ያቋራጭ ሃብታሞች ናኙ። ግንባታው ጨሰ። “ህዳሴው” ለተወሰኑ ወገኖች ፈንጠዝያ የተሰጠ ስያሜ ሆነ። ግድያ፣ እስር፣ እንግልትና አፈና እደግ ተመንደግ ተባለ። ነገሩ እንዲስተካከል ትግል የሞከሩ ተባረሩ፣ ታሰሩ፣ የተገደሉም አሉ። የተሰደዱ ጥቂት አይደሉም። አገር ውስጥ የቁም እስረኛ ሆነው ጊዜ የሚጠብቁ ቁጥራቸው ቀላል አይደለም።
ሲጀመር በብሔር ብሔረሰቦች ስም ሲምሉና ሲገዘቱ የነበሩት የህወሃት መሪዎች፣ የራሳቸውን ሰዎች ሳይቀር ወረዳ እየለዩ የፈጸመባቸው ተግባር፣ በሌሎች የአገሪቱ ህዝቦች ላይ ከስርዓቱ መርህ በመነሳትና “በጥጋብ” የተፈጸመው በደል፤ “የገዢው መደብ ነኝ” በሚል ንጹሃንን ከስራና ከሃብታቸው ከማፈናቀል ጀምሮ የተሰራባቸው ግፍ ከጎሳ ፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ጋር ተዳምሮ የተካረረ ደረጃ ደርሷል።
የከፋቸው በዝተው ቂማቸው እየተናነቃቸው ይገኛሉ። የህወሃት አመራሮች ከፊታቸው ክፉ ዘመን ስለመኖሩ ብዙም የተጨነቁ አይመስሉም። የቂም በትር ቀጠሮ የለውም። ቂም ቦታ አይመርጥም። የጎሳ ፖለቲካ በባህሪው ምሱ ደም ነው። የጎሳ ጣጣ ባለባቸው አገሮች የታየው ይኸው እውነት ነው። በተለይ ህወሃቶች አሁን ባጨመላለቁት ደረጃ እንለካው ከተባለ አደጋ አለ፤ ያውም ግልጽ የሆነ አደጋ። ችግሩ ሲነሳ፣ ቂም በትር ሲሰነዝር፣ ጥላቻ ልጓሙ ሲበጠስ፣ በብርና በመሳሪያ ብዛት መታደግ የሚቻል አይሆንም። ይህንን ስንል ላገራችን ችግርና የደም አታሞ ለመምታት አይደለም። የቆምንለት ዓላማና የሙያ ቃልኪዳናችን ከጎሠኝነት ይልቅ ሰብዓዊነትን ማስቀደም መሆኑን የሚጠሉንም ጭምር ያውቁታል፡፡ በዚህ የሰፋ ራዕይ ውስጥ ስላለን የመጥበብ አደጋ ምን እንደሆነ በግልጽ ይታየናል፡፡ ስለዚህ የአደጋ ማስጠንቀቂያ እንሰጣለን፡፡
ዛሬ ዳር ቆመን የምንመለከተው የጎረቤታችን ደቡብ ሱዳን የጎሳና የዘር ጭፍጭፍ “እኛም ቤት እሳት አለ” ስለሚያሰኝ ነው። የሚታሰሩ፣ የሚገረፉ፣ የበይ ተመልካች የሆኑ፣ የተገደሉ፣ አሁን ድረስ በስቃይ ላይ ያሉ … ቤቱ ይቁጠራቸውና ዘመድ፣ ወገን፣ ተቆርቋሪ፣ አለኝታ፣ ታዳጊ አላቸው። ብሶት ህወሃትን ብቻ አይወልድምና ሁሉም ረጋ ብሎ ያስብ። ህወሃት ብቻ የብሶት የበኩር ልጅ አይደለም፤ ሊሆንም አይችልም። ሲያሻ ህግ እየተጠቀሰ፣ ሲያሻ በተቀነባበረ ድራማ፣ ሲፈለግ በተፈለገው መንገድ የሚፈነጭበት ጊዜ ሳያረጅ ለሰላም ሁሉም እጁን ያንሳ!! የጎሳ ፖለቲካ ምሱ ደም ነውና ሃዘን ሳይመታን በእውነተኛ እርቅ ጊዜው ሳያልፍብን የጎሳ ፖለቲካን ምስ እናምክን!! ተቃዋሚዎችም ጭምር!

Monday, January 20, 2014

አሳሳቢና የወደቀ እንጂ አበረታች የኢኮኖሚ እድገት የለንም!!



ምንሊክ ሳልሳዊ በተጭበረበረ ፖለቲካ ላይ ወያኔ እየገነባ ያለው ኢኮኖሚ እየተንኮታኮተ መሆኑ ይህንን ተከትሎ ከፍተኛ የሆኑ የገንዘብ ተቋማት ብሄራዊ ባንክን ጨምሮ ሙስናው በፈጠረው የኢኮኖሚ እብደት አጣብቂኝ ውስጥ መሆናቸው ተረጋግጧል::ተነሳሽነት ካለ በሃገሪቱ ውስጥ ያሉ ችግሮች የሚፈቱ እና አስቸጋሪ ያልሆኑ ናቸው:: ሆኖም ከፍተኛ የሆኑ የሕወሓት ባለስልጣናት በሙስና እና በፖለቲካ ማጭበርበር የህዝብ ችግሮች እንዳይፈቱ እያደረጉ ነው::

የኢኮኖሚው መንኮታኮት እና የንግዱ እንቅስቃሴ ዝምታ ምንም አይነት ኤክስፐርት መቅጠር ወያንም በጉዳዩ ላይ ተቋም አዋቅሮ ምርምር እና ጥናት ማድረግ አያስፈለገውም በገሃድ እየታየ ያለ ነው:: የመንግስት ሚዲያዎች የሃሰት ፕሮፓጋንዳ እና የበለጸጉት ሃገራት ብሄራዊ ጥቅምን ተመርኩዞ የሚወጣ የእድገት ቁጥር ቁልል ይህንን ለመደበቅ አልቻሉም::በአደባባይ በይፋ እያየነው ነው::በሃገሪቷ ላይ የተፈጠረው ሙስናን መሰረቱ ያደረገው የዋጋ ግሽበት እና የውጪ ምንዛሪ አቅርቦት ባዶ መሆን ሌተር ኦፍ ክሬዲት ለመክፈትም አለመቻሉ የፋብሪካ ውጠቶችን ለማምረት የሃገር ውስጥ ማኑፋክቸሮች ለምርቶቻቸው የሚያስፈልጓቸውን በወቅቱ በቦታል አለማግኘት የውጪ ምንዛሬ አቅርቦት ባዶነት ለስራቸው መኮላሸት ምክንያት እየሆኑ ሲሆን የባንክ ብድሮች ሙስናን መሰረት አድርገው መስራታቸው የመንግስት ድርጅቶች አስፈላጊውን ክፍያዎች በገንዘብ እጥረት አለማድረጋቸው የንግዱን እንቅስቃሴ እያንኮታኮተው ሲሆን ይህ ደግሞ የሰራተኛ መፈናቀልን እና ሰርቶ የመኖር መብት ማጣትን ውጤታማ እያደረገ ነው::ገስት ሃውስ፣ ጫት ቤት፣ ሺሻ ቤት፣ማሳጅ ቤት፣… በየቦታው መስፋፋት የሃገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት ሳይሆን ውድቀት እና የትውልድን ዝቅጠት ያመለክታል::

በወያኔ መንግስት ነጋዴውን እና ንግዱን እንመራለን በሚሉ ባለስልጣናት እና ሰራተኞቻቸው ዙሪአ እንዱም ከነጋዴው ጋር በመካከላቸው መተማመት የጠፋ ሲሆን የሙስናው ገመድ ሊያንቀኝ ይችላል በሚል ስልጣናቸው ሆኖ ያሉ ሰዎች ማንኛውንም ስራዎች ለመስራት የበላይና የበላይ ትእዛዝ የሚጠብቁበት በተጨማሪም ቀላል የሆኑ ፍቃድን የማውጣት እና የመመለስ ስራዎች ችግር እየፈጠሩ መሆኑ ሲታወቅ የግል ጥቅመኝነትን እንደ ዋነኛ መዘውር ማድረጋቸው ቢሮክራሲውን ተብትበውት ለኢኮኖሚው መንኮታኮት የፖለቲካው ድርሻ ጭነት ዋነኛው መሆኑን በገሃድ እየታየ እና ለሃገር እና ለህዝብ ደንታ የሌላቸው ከፍተኛ ባለስልጣናት ለራሳቸው ሙስና እና ማጭበርበር ያመቻቸው ዘንድ በፈጠሩት ሰንሰለት ኢኮኖሚውን በባዶ አስቀርተውታል::

ፖለቲካው የወለደው ጭካኔ የፈጠረው የኢኮኖሚ መዛባት ህዝቦች የሚያገኙትን መረጃ በስራት እንዳያገኙ የህትመት ውጤቶችን እየጎዳ ነው::ይህ ከወያኔ ባለስልጣናት የሚተላለፉ መመሪያዎች ውጤት የሆነው እና ሀገሪቷን ለድቀት የዳረጋት የስልክ ትእዛዝ የህዝቦችን መረጃ የማግኘት መብት ከመጉዳቱም በላይ ወረቀት እና ቀለም የለም፣ ማሽን ተበላሽቷል፣ …በሚል ምክንያት ፕሬሱ የሕትመት ችግር እያጋጠመው ነው፡፡ ከምጣኔ ሃብት እንቅስቃሴ አኳያ ሲታይ እጅግ አስቸጋሪ ስለሆነ ኢኮኖሚውን አንገላቶት ገደል ጨምሮታል::

ኢኮኖሚውን ያጠናክራሉ በሚባሉ የንግድ ተቋማት የሚሰማውን አቤቱታ እና ቅሬታ የሚያዳምጥ በመጥፋቱና ቅሬታ ሰምቶም መፍትሄ ና ውሳኔ የሚሰጥ አካል ባለመኖሩ መተማመኖች በመስፋታቸው መዋእለ ንዋዬን አፍስሼ በኋላ ቢያስቆሙኝስ ቢነጥቁኝስ በማለት የሚሰጋው ነጋዴ ጨምሯል ፡፡ ለችግሮቻችን መፍትሄ ስጡንየሚለው መብዛቱ አዳማጭ መንግስት በመጥፋቱ ሥራ ለማቆም የሚገደዱ እየበዙ ነው፡፡ በባንክ ዕዳ ተወጥረው የሠራተኛ ደመወዝ እየከፈሉ፣ ለቢሮ፣ ለመጋዘን፣ ለኤሌክትሪክና ለተለያዩ ወጪዎች በመዳረግ ገቢ የማያውቁ በርካታ የሥራ ዓይነቶች አሉ፡፡ ድርጅታቸው እንዳይዘጋ አንድ ቀን ችግሩ ይፈታል በሚል ተስፋ፣ እንዳይቀጥሉ ደግሞ የወጪ መብዛት እያስጨነቃቸው ጭንቅ ውስጥ የገቡ በርካታ ናቸው፡፡ ሥራቸውን ያቆሙም አሉ፡፡

በሃገሪቱ የተፈጠረው ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግዥበት እና የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት ዜሮ መሆን የገንዘብ ምንጭ ይሆናሉ የተባሉትን ሁሉ በባዶ አባዝቶ ከየባንኩ ግድግዳ እያላጋቸው ነው::ወያኔ ምእራባውያንን ለማታለል ለፖለቲካው ፍጆታ ለመበልጸግ ሲል የጀመራቸው ስማቸው ልማት የተባሉት የሃገሪቷን የገቢ አቅም ያላመዛዘኑ እና የግሉን የገንዘብ ተቋማት የተፈታተኑ ከመሆኑም በላይ ባንኮች በየቦታው ያላቸውን አክሲዮኖች እስከመሸጥ እንዲደርሱ አድርጓቸዋል::

ፖለቲካን ተገን አድርገው የተቋቋሙ የንግድ ድርጅቶች ሌላውን የንግድ ክፍል አላሰራ ከማለታቸውም አስፈላጊውን የግብር እና የቀረጥ ገቢዎች አላመክፈላቸው እና ትልልቅ የንግድ ገቢዎችን በሞኖፖል ገዢውን ፓርቲ ተንተርሰው ማንቀሳቀሳቸው ለሃገሪቱ የኢኮኖሚ መውደቅ ሌላው ምክንያት ነው::

በአጠቃላይ ያለው የወያኔ ጁንታ በፖለቲካው ላይ ተመርኩዞ የፈጠረው ኢኮኖሚ ምንም ውጤት አለማምጣቱን መመልከት ስለተሳነው ኢትዮጵያውያን ሁሉ በጋራ ይህንን አጭበርባሪ ስርኣት ገርሲሰን መጣል የዜግነት ግዴታችን መሆኑን ለማሳሰብ እወዳለሁ::

Thursday, January 16, 2014

ወሬ አይደለም፤ አገር ቤት አንገባለን” ሌንጮ ለታ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ “መረጃ የለኝም”


odf lencho
የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር ከፍተኛ አመራርና ጸሐፊ የነበሩት አቶ ሌንጮ ለታ አዲስ ያቋቋሙትን ድርጅት ይዘው አዲስ አበባ እንደሚገቡ አስረግጠው ተናገሩ። አቶ ሌንጮ ድርጅታቸው ኢትዮጵያ ገብቶ ለመታገል መወሰኑ ለምን ወሬ እንደሚባል እንዳልገባቸውም አመላክተዋል። በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ኢትዮጵያ መግባታቸውን ኦነግ እንደሚቀበለው ተጠይቀው “ኦነግን ጠይቅ” በሚል ጠበቅ ያለ መልስ ሰንዝረዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ እንደሌለው አመልክቷል።
ጥር 5 ቀን ከጀርመን ድምጽ የአማርኛ ፕሮግራም ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት አቶ ሌንጮ “ኖርዌይ ተቀምጠን ምን እናደርጋለን? ሃገር ቤት ገብተን እንታገላለን” ሲሉ ወደ አገር ቤት ለመመለስ መወሰናቸውን ግልጽ አድርገዋል። “ይሳካል?” በማለት ጠያቂው ላቀረበው “ይሳካል አይሳካም ተብሎ ወደ ትግል አይገባም” በማለት አቶ ሌንጮ ማምረራቸውን በሚያሳብቅ ሁኔታ መልስ ሰጥተዋል።
ህወሃት የዘረጋውን የፌዴራል ሲስተም እንደሚቀበሉትና የኦሮሞ ህዝቦች ጥያቄም በዚያው ውስጥ ሊመለስ እንደሚችል ያመለከቱት አቶ ሌንጮ፣ “በታሪክ፣ በባህል፣ በቋንቋ የተመሰረተ ሳይሆን በህግና በህገመንግሥት በተደነገገ የህዝቦች አንድነት እናምናለን” ብለዋል። የግለሰብ መብት ከብሔር መብት መቅደም አለበት፣ የብሔር መብት አስቀድሞ ሊከበር ይገባዋል በሚል ሁለት አቋም ከሚያራምዱት የተለየ ፕሮግራም እንዳላቸውም አቶ ሌንጮ አስታውቀዋል። የግለሰብም ሆነ የቡድን መብት መከበር አለበት የሚል ፕሮግራም ያለው አዲሱ ድርጅታቸው በዚህ አቋሙ ከሌሎች እንደሚለይ አመልክተዋል።
በምርጫ የመሳተፍን ጉዳይ አስመልክቶ የእሳቸው ድርጅት ብቻ ሳይሆን ሁሉም ተቃዋሚ ሃይሎች ወደ ምርጫ ቢገቡ ፍላጎታቸው መሆኑንን አቶ ሌንጮ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ከምርጫ በፊት ብዙ ጥያቄዎች እንዳሉ አመልክተዋል። ዴሞክራሲን ኢትዮጵያ ውስጥ ለማስፋፈት ምርጫ ብቻውን መፍትሔ እንዳልሆነም ጠቁመዋል። ህዝብን አገር ቤት ገብቶ ማስተማር፣ መቀስቀስና ማብቃት በዋናነት አስፈላጊ እንደሆነም አስምረውበታል።
ከኢህአዴግ ጋር ድርድር ስለማድረጋቸው ለተጠየቁት፣ እስካሁን የተደረገ ድርድር እንደሌለ አቶ ሌንጮ ጠቁመዋል። አያይዘውም ከኢህአዴግ ጋር ብቻ ሳይሆን ከተቃዋሚ ድርጅቶች ጋርም የመደራደር እቅድ እንዳላቸው አመልክተዋል። አቶ ሌንጮ በተደጋጋሚ አገር ቤት መሄዳቸው መገለጹንም በማንሳት አስተባብለውታል። አቶ ሌንጮ ድርድር ስለመደረጉ ባያምኑም በተለያዩ ጊዜያት በኖርዌይና በተለያዩ አገራት ከኢህአዴግ መልዕክተኞች ጋር አሁን ይፋ ባደረጉት ጉዳይ ዙሪያ መነጋገራቸው መዘገቡ ይታወሳል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣም በቅርቡ ኢህአዴግ ብሔር ተኮር ከሆኑ ድርጅቶች ጋር ድርድር እያደረገ መሆኑንና ከሌሎች ማናቸውም ፓርቲዎች ጋር ለመደራደር ሃሳብ እንደሌለው ምንጮቹን ጠቅሶ መዘገቡይታወሳል።
አቶ ሌንጮ የሚመሩት ድርጅት ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት መወሰኑን አስመልክቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ዲና ሙፍቲ “መረጃ የለኝም፤ የድርጅት ሰዎች ብትጠይቅ የተሻለ ነው” በማለት ዜናውን ይፋ ላደረገው የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ ተናግረዋል።lencho and melesየሚመለከታቸውን አካላት ለማግኘትና በሪፖርቱ ለማካተት እንዳልተቻለ ከሪፖርቱ ለመረዳት ተችሏል። አብዛኛው የኦነግ ደጋፊዎች የነበሩ በድርጅቱ የትግል ጉዞና ውጤታማ አለመሆን መማረራቸውን የተለያዩ ድረገጾች በስፋት ይዘግቡ ነበር።
ለአቶ መለስ ቅርብ እንደነበሩ የሚነገርላቸው አቶ ሌንጮ “አገር ቤት ገብተው ይሳካላቸው ይሆን?” የሚለውን ለመናገር “ህገ መንግሥቱንና ህገ መንግሥታዊ ስርዓቱን ተቀብዬ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ተስማምቼና ወድጄ ወደ አገር ቤት ለመግባት ችያለሁ” በማለት ኢቲቪ ዜናውን ይፋ ሲያደርገውና “ያሳዘነውን መንግስትና ህዝብ ይቅርታ እንጠይቃለን” ሲሉ ከተደመጠ በኋላ እንጂ ከወዲሁ አስተያየት መስጠት እንደሚቸግራቸው አስተያየት እንዲሰጡ የጠየቅናቸው ተናግረዋል። “ውሳኔውን ተፈጥሯዊ ጫና” ነው ያሉም አሉ።

ፕ/ር በየነ “የአካኪ ዘራፍ ትግል አክሳሪ ነው፤ የስሜት ፖለቲካ ያብቃ” አሉ “ከኤርትራ ጋር መስማማት አግባብ ነው፤ ግን ፍርሃቻ አለኝ”


“የአካኪ ዘራፍ ፖለቲካና ከስሜት ያልጸዳ የፖለቲካ ትግል መሪውንም ሆነ አምኖ የሚመራውን ህዝብ ለድል” እንደማያበቃ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ገለጹ። ከኤርትራ ጋር ስምምነት ቢደረግ መልካም መሆኑን፣ ነገር ግን ስምምነቱ የመሪዎችና የፖለቲከኞች ሳይሆን የህዝብን ስሜት የጠበቀ ሊሆን እንደሚገባውም ጠቁመዋል።
ከጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ጋር በተለይ ቃለ ምልልስ ያደረጉት ፕ/ር በየነ “አሁን ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሁኔታ ከመቼውም ጊዜ በላይ አስተዋይነት የሚፈልግ፣ ዘመናዊ የትግል ስልት የሚጠይቅ ነው” በማለት ተናግረዋል። በቃለ ምልልሳቸው ደጋግመው  “አሁን በተያዘው የአካኪ ዘራፍ መንገድ የትም አይደረስም” በማለት ምክንያታቸውን ዘርዝረዋል።
ትንንሽ ጠርዝ በመያዝ የትም የማይደርስ ትግል ከየአቅጣጫው እንደሚፈለፈል ፕ/ር በየነ አመልክተዋል። በዚሁ የተነሳ ስትራቴጂካልና ታክቲካል ጉዳይ የመለየት አቅም አናሳ በመሆኑ የፖለቲካው መንደር የርስ በርስ ንትርክና ውግዘት ሊሆን እንደቻለ ገልጸዋል። ለዚህም ተጠያቂዎችና ቅድሚያ ተወቃሾች ህዝብና አገር የምትፈልጋቸው የዘመናዊ ለውጥ መሪዎች መሆን ሲገባቸው የዳር ተመልካች የሆኑት የአገሪቱ ልሂቃን እንደሆኑም በግልጽ ተናግረዋል።
“ችግሩ በአገር ውስጥ ባሉት ልሂቃን ላይ ጎልቶ ቢታይም፣ በውጪው ዓለም ባሉት ምሁራኖችም ላይ ተመሳሳይ ችግር አለ” የሚሉት ፕ/ር በየነ “እነዚሁ ክፍሎች ትግሉን ከመቀላቀል ይልቅ እኛን በመውቀስ አገራዊ ሃላፊነታቸውን የተወጡ መስለው ይታያሉ” ሲሉ ስሜታቸውን ገልጸዋል።
“የፖለቲካው መስመር ክፍተትን አይወድም” በማለት የሰከነ አመለካከት ላላቸውና ከስሜት ፖለቲካ ነጻ ለሆኑት ዜጎች መልዕክት ያስተላለፉት ዶ/ር በየነ፣ ሰዓትና በጀት በመመደብ የተለየ አመለካከት ያላቸውን ክፍሎች ሰድቦ የማሰደብ ተግባር ሲከናወን ማየታቸው በጅጉ እንደሚያሳዝናቸው ተናግረዋል። በጦር መሳሪያና በሃብት ብዛት መፎካከር ባይቻልም፣ በሰብአዊ ብቃት ኢህአዴግን መፎካከር እንደሚቻል የጠቆሙት ዶክተሩ የተቃዋሚው ሰፈር በተቃራኒው የተፈረካከሰ፣ እርስበርስ ለመባላት ቅድሚያ የሚሰጥ፣ የትግል ስልቱም ሆነ አቅሙ ስትራቴጂካዊና ታክቲካል ጉዳዮችን መለየት በማያስችል ደረጃ የተዋቀረ መሆኑ ትግሉን ፍሬ አልባ እንዳደረገው ተናግረዋል።
beyene_petros“ለአውራነት/ኮርማነት የታሰበ በሬ ተመልሶ ላሚቱን ጠባ” በሚል በሃድያ የሚነገር ተረት በማስታወስ ሃሳባቸውን ያጠናከሩት ዶ/ር በየነ፣ የዚህ ሁሉ ችግር መንስዔው የልሂቃኑ ዝምታ እንደሆነ አመልክተዋል። አገራቸውን ወደ ተሻለ መንገድ ለማሸጋገር የሚችሉ ሁሉ ዝምታቸውንና ዳር ቆመው የሚመለከቱትን የአገራቸውን ውድቀት እንዲታደጉ ጥሪ አቅርበዋል። ዶ/ር ነጋሶ የወሰዱትን ርምጃ በማንተራስ ስለ ፖለቲካ ጡረታም ተጠይቀው መልስ ሰጥተዋል።
“እናንተ አርጅተሃል ካላችሁ እንጂ እኔ አላረጀሁም። ጤነኛ ነኝ። የነጋሶን ያህል እድሜም የለኝም” በማለት መልሳቸውን ይጀምራሉ። በማያያዝም “ልተውስ ብል እንዴት ብዬ?” ሲሉ ይጠይቃሉ። “ልሂቃኑ ዳር ቆመው ተመልካች ሆነዋል። በዚህ ላይ የምመራቸውና ውህደት የፈጠሩት የደቡብ ህብረትና የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራት ፓርቲ አደራውን ከኔ አላወረዱም። አሁን በቃኝ ማለት ሰራዊት በትኖ እንደሚፈረጥጥ መሪ የመሆን ያህል ነው።”
ኸርማን ኮህን በቅርቡ ይፋ ያደረጉትን የእርቅ ሃሳብ አስመልከቶ ማብራሪያ ሰጡት ዶ/ር በየነ “በአልጀርሱ ስምምነት መሰረት የሚደረግ ስምምነት ከቶውንም ቢሆን ተቀባይነት የለውም። ከኤርትራ ጋር እርቅ መልካም ቢሆንም በፖለቲከኞችና በውስን ሃይሎች ፍላጎት ተከናውኖ ሰዶ ማሳደድ እንዳይሆን እፈራለሁ” ብለዋል። ከዚሁ ጋር በማያያዝ አሜሪካ በኢህአዴግና በወያኔ የፖለቲካ እምነት ደስተኛ እንዳልሆነች ተናግረዋል። ድጋፍ የምትሰጠው ከፍቅር ብዛት እንዳልሆነ በማመልከት የተቃዋሚው ክፍል ይህንኑ ቀዳዳ ሊጠቀምበት ይገባል ብለዋል። “ታዲያ” አሉ ፕ/ር በየነ “ታዲያ በማንጓጠጥና በዘለፋ ሳይሆን በሰከነ መንፈስና ስሜትን በገደለ አስተዋይነት” ሊሆን ይገባል። በመጪው ምርጫ የ1997 ምርጫ ዓይነት ሁኔታ እንዲፈጠር ዘመቻ መጀመሩንና የድጋፍ ፍንጭ መታየቱን የገለጹት ዶ/ር በየነ ስለ ሃይል አማራጭና ኢህአዴግ፣ በተለይም ህወሃት ውስጥ አለ ስለሚባለው የመፈረካከስ ችግር ተጠይቀው “ጦርነት የሁለት የጎበዝ አለቆች ጸብና ድብድብ ነው። ከአሁን በኋላ እኔ ላገሬ ጦርነት አልመኝም” በማለት ከምክንያታቸው ጋር አስቀምጠዋል። ህወሃትና ኢህአዴግ ውስጥ አለ ስለተባለ የመፈረካከስ ችግር “የዋህነት አይጠቅምም፣ በስሜትና በአካኪ ዘራፍ ፖለቲካ የሚመጣ ለውጥ ይኖራል ብዬ አላስብም” ብለዋል። ስለ ስጋታቸውም ተናግረዋል።
“ወያኔ የሚባለውና ተዘጋጅቶ አገሪቱን የተቆጣጠረ ሃይል ለሰበሰበው ሃብትና ንብረት ሲል ፖለቲካውን በበላይነት ለመምራት ከቀን ወደ ቀን የሚፈጽመው ጥፋት ህዝብ እያማረረ መጨረሻው አገሪቱን ወደ ጥፋት እንዳይወስድ ነው። የከፋቸው በጨመሩ ቁጥር ችግሩ መከሰቱ አይቀርምና በጥበብ ታግሎ ካሰቡት ለመድረስ እነሱ ከሚያስቡት በተለየ በልጦ ማሰብና መታግል አስፈላጊ ነው። ለዚህም የልሂቃኑ ዳር ቆሞ መመልከት መቆም አለበት” ብለዋል። በማያያዝም ዲያስፖራው አገር ውስጥ ለሚታገሉ ድርጅቶች ልዩነት ሳያደርግ ድጋፍ ሊሰጥ እንደሚገባ አሳስበዋል። ድጋፉም ሆነ እገዛው ሰክኖ ለማሰብ እንደሚመነጭም ገልጸዋል። ዶ/ር በየነ ጴጥሮስ በተለይ ከጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ያደረጉትን ሙሉ ቃለ ምልልስ በቀጣይ ይዘን እንቀርባለን።

Saturday, January 11, 2014

ሻምበል ጉታ ዲንቃ፤ ጊዜውን ጠብቆ ይነጋል (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም )

በአሁኑ ጊዜ ወያኔ ሰውን እያፈረሰ፣ ማህበረሰብን እያፈረሰ ሰማይ-ጠቀስ ሕንጻዎችን በሚሠራበት ጊዜ፣ ከትናንት ወዲያ የሰዎችን ቤቶች አፍርሶ ትናንት የመኪና መንገድ ከሠራ በኋላ ዛሬ መንገዱን አፍርሶ የባቡር መንገድ እየተሠራ አዲስ አበባ በትራፊክ መጨናነቅ መኪና መንዳት አደገኛ በሆነበት ጊዜ፣ ዛሬ ባለሥልጣኖች የሚሠሩት ጠፍቶአቸው የጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ የሚባለውን በአማካሪዎች ከሞሉት በኋላ ለሚኒስትሮችም አማካሪ መሾም በተጀመረበት ጊዜ፣ ዛሬ በሳኡዲ አረብያ ኢትዮጵያውያን እንደአደገኛ አውሬ እየታደኑ በሚደበደቡበት፣ በሚታሰሩበት፣ በሚደፈሩበትና በሚገደሉበት ጊዜ፣ ዛሬ በኬንያና በዩጋንዳ እንዲሁም በእሥራኤል ኢትዮጵያውያንን የማንገላታት ዝንባሌዎች በሚታዩበት ጊዜ፣ ዛሬ ኢትዮጵያውያን ከስዊድን እስከአውስትራልያ እየተሰበሰቡ በመጮህ ለማይሰሟቸው ሁሉ አቤቱታቸውን በሚያቀርቡበት ጊዜ፣ ዛሬ በተለያዩ አገሮች በኢትዮጵያውያን ላይ በሚፈጸመው ጥቃትና በደል፣ አለሁላችሁ የሚል መንግሥት በሌለበት ጊዜ —- ዛሬ ታሪካዊትዋ ኢትዮጵያ፣ ራሳቸውን የሚያከብሩና ኩራት ራታችን የሚሉት ኢትዮጵያውያን አልቀው ለሆድ በየሰው አገር መሰደድ ባህል በሆነበት ጊዜ፣ ዛሬ ዶር. በድሉ ዋቅጅራ ስለኢትዮጵያና ስለኢትዮጵያውያን ውርደት ደጋግሞ የነፍሱን ኡኡታ ባሰማበት ጊዜ በድንገት አንገታችንን ቀና አድርጎ ኩራታችንን ሊያስጎነጨን የሞከረ ሰው ተገኘ! ኢትዮጵያ ሁሌም የተአምር አገር ነች።
በታላቁ ሰው በኔልሰን ማንዴላ እረፍት ምክንያት አንድ ተደብቆ የኖረ ክቡር ኢትዮጵያዊ ብቅ አለ፤ ማንዴላ ለሥልጠና በኢትዮጵያ በነበረበት ጊዜ ምናልባትም እንግሊዞች ማንዴላን ሊያስገድሉ ከጠባቂዎቹ አንዱ የነበረውን ወታደር በገንዘብ ገዝተው ዓላማቸውን ለመፈጸም አቅደው ነበር፤ ወታደሩ ገንዘቡን ከተቀበለ በኋላ ሀሳቡን ለውጦ ገንዘቡን ለአለቃው ሰጠ፤ ማንዴላ ከሞት ተረፈ፤ አንድ ተራ ኢትዮጵያዊ ራሱንና አገሩን የሚያስከብር ሥራ ሲሠራ የሚኮሰኩሳቸው ባለሥልጣኖች ለእነሱ የማይተላለፍ ክብር በመሆኑ ተዳፍኖ እንዲኖር አደረጉት፤ እነሱ ሞተው ወይም ተሰድደው ሲያልቁ የተዳፈነው ምሥጢር ብቅ አለ፤ ባለሥልጣኖቹ ሸልመውት ይሆናል፤ ግን አላከበሩትም፤ ሻምበል ጉታን ያከበረው የማንዴላ ሞት ነው፤ የሚያሳዝነው ማንዴላ ይህንን የሱን ሕይወት ለማትረፍ ሁለት ሺህ ፓውንድ ያጣውን ኢትዮጵያዊ ወታደር ሳያውቀው መሞቱ ነው።የኢትዮጵያ አርበኞች ታሪካቸው ተቀብሮ የቀረው እንዲህ እየሆነ ነው፤ ታዴዎስ ታንቱ ሥራዬ ብሎ የተረሱ አርበኞችን ከመቃብር እያወጣ ያስተዋውቀናል፤ በሌሎች አገሮች እንደዚህ ለአገር ትልቅ ፋይዳ ያለው ሥራ በአንድ ሰው በበጎ ፈቃድ የሚሠራ ሳይሆን ዋና የመንግሥት ተግባር ነው።
ሻምበል ጉታ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ባይሆንም ራሱን ችሎ ለኔልሰን ማንዴላ መቃብር ደርሶአል፤ በአገር ደረጃ በሥልጣን ወንበሮቹ ላይ ለአገር የሚያስቡ ሰዎች አለመኖራቸውን ለማወቅ ግሩም ማስረጃ ነው፤ ለቀብር የሄደው ባለሥልጣን ሻምበል ጉታን ይዞ ቢሄድ ኖሮ ለራሱም ሆነ ለአገሩ ክብርና ጌጥ ይሆንለት ነበር፤ ለደቡብ አፍሪካ ሕዝብም ሆነ ለዓለም በመላ አንድ ኢትዮጵያዊ ወታደር አልሸጥም-አልለወጥም ብሎ የኔልሰን ማንዴላን ሕይወት ማትረፉን በማስታወቅ አገሪቱን ያስከብር ነበር፤ የታፈነው ታሪክ አፈትልኮ ሲወጣ ከስደተኞች ጋር ተያይዞ መሆኑ ኢትዮጵያ የደረሰችበትን የአደባባይ መክሸፍ የሚያሳይ ነው፤ ባለቤት ያቀለለውን አሞሌ ባለዕዳ ተቀበለው፤ መንግሥት ያፈነውን ክብር ስደተኞች አጌጡበት!
ለእኔ አሁን አንድ ጥያቄ ይቀራል፤ ሻምበል ጉታ የአገሩን ክብር ከራሱ ጥቅም በላይ በማድረጉ፣ የተቀበለውን አደራ በመጠበቁ ቢያንስ ሁለት ሺህ ፓውንድ አጥቷል፤ እንዳጣ ሊቀር ነው? ቢያንስ የከፈለውን ሁለት ሺህ ፓውንድ ወይስ ያንን አሥር እጥፍ አድርገን እንከፍለዋለን? ሻምበል ጉታን የምናመሰግነው በርጥቡ ነው በደረቁ? እኛ ያለጥርጥር ኮርተንበታል፤ ሁላችንም በኢትዮጵያዊነታችን የሱን ክብር በመጋራት ራሳችንን አክብረናል፤ ሻምበል ጉታም በእኛ እንዲኮራና በእኛ እንዲከበር ማድረግ ያለብን ይመስለኛል፤ ስለዚህ ምን እናድርግ? ለራሱ ክብር፣ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ክብር ሲል የከፈለውን እስቲ ከወሬ ያለፈ ነገር እናስብና ለዚህ ጀግና የምንችለውን አድርገንለት እግዚአብሔር ዕድሜ ይስጥህ እንበለው።

Thursday, January 9, 2014

በጅዳ እና አካባቢው የኢትዮጵያውያን ክራሞ

saudi ethio j
ካሳለፍነው ወር ጀምሮ ወደ ሃገራቸው እንዲገቡ በተደረገው ጥሪ እጃቸውን የሰጡ መኖሪያና የስራ ፈቃድ የነበራቸው ዜጎች ባቀረቡት ቅሬታ “ወደ ሃገር እንዳንገባ ተደርገን እየተጉላላን ነው!” ብለውኛል። በቀን በሚሰጠው ደረቅ ብስኩትና ጥራቱ ባልተጠበቀ ሩዝ መጉዳታቸውን የገለጹልኝ ሲሆን መፍትሔ የሚሰጠን የኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ የሳውዲ መንግስት ተወካዮች አጥተው ቀን በጸሃይ ፣ ማታ በብርድና በቁር እንግልት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል። ወደ ሃገር እንግባ ብለው በተደረገው ጥሪ እጃቸውን የሰጡት መኖሪያና የስራ ፈቃድ የነበራቸው ዜጎች እዚህ በጅዳ ሽሜሲ ብቻ ሳይሆን በሪያድ እስር ቤቶች እንዳሉ እንግልት እየደረሰብን ያሉ ነዋሪዎች ምሬታቸውን ገልጸውልኛል።
ሁከት በጅዳ የንጉስ አብድልአዚአዚዝ አውሮፕላን ማረፊያ-
ከጅዳ መካው የሽሜሲ መጠለያ ተነስተው ወደ ሃገር ለመሳፈር  በጅዳ የንጉስ አብድልአዚአዚዝ አየር መንገድ ማረፊያ አውሮፕላን ማረፊያ የደረሱ ቁጥራቸው 1500 በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን “የያዛችሁት እቃ ከሚፈቀደው ኪሎ በላይ ነው!” በሚል የተፈጠረው አለመግባባት  ማክሰኞ ከቀትር በኋላ መጠነኛ ሁከት ተቀስቅሶ እንደነበር እና ከሰአታት በኋላ መረጋጋቱን ተደጋጋሚ መረጃ ደርሶኛል።  የማክሰኞው ሁከት መነሻ የተመላሾችን የተከማቸ እቃ ለማየት ወደ ቦታው የደረሱትን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሃላፊ በቦታው መድረሳቸውን ተከትሎ ሲሆን በእንግልቱ የተበሳጩት ዜጎች ሁከት መቀስቀሳቸው በአይን እማዘኞች ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ  ለመረዳት ችያለሁ። የአይን እማኞች አክለውም ዜጎች ከሃላፊው ጋር ሊጋጩ ሲሉ በጸጥታ አስከባሪዎች ብርታት መትረፋቸውን ከቦታው  በሰአቱ የደረሰኝ መረጃ ያስረዳል። ግርግሩ ለሰአት ያህል የቀጠለ ቢሆንም በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት አልደረሰም። ሁኔታውን ለማረጋጋት በቦታው የተገኙ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊሶች ማረጋጋት ከፈጠሩ እና ሁኔታው ከተረጋጋ በኋላ የአየር መንገዱን ሃላፊ ለጥያቄ ወስደዋቸው እንደነበርና ሃላፊውን ለማስለቀቅ የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች እና ጅዳ የመጡት የሪያዱ አንባሳደር ወደ ቦታው በመንቀሳቀስ ከሰአታት በኋላ ሃላፊውን ይዘው ምሽት ላይ መመለሳቸውን ተጨባጭ መረጃ ደርሶኛል።saudi ethio j1
የሃላፊውን ለጥያቄ መቅረብ ተከትሎ በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርኳቸው አንድ ውስጥ አዋቂ ሲናገሩ “  በአውሮፕላን አቅርቦት እጥረት እና እቃችን ሳንይዝ ወይም በአደራ ተቀብሎ ወደ ሃገር የሚያስተላልፍልን እስካላገኘን ወደ ሃገር አንገባም ያሉትን ዜጎች ጉዳይ እንዲመለከቱ በቆንስላው ጥያቄ ወደ አየር ማረፊያው ያቀኑት የአየር መንገዱ ሃላፊ ስለ ዜጎች መጉላላት መረጃ እንዳልነበራቸውና በቦታው ሲደርሱ ከሁከቱ ጋር ተያይዞ ግራ ተጋብተው ታይተዋል።” በማለት ሲያስረዱ በቆንሰሉና በአየር መንገዱ ሃላፊዎች መካከል የመረጃ ክፍተት መኖሩን ገላልጠው አጫውተውኛል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዚህ በፊት ከ40 ኪሎ በላይ እቃ መውሰድ አትችሉም የተባሉ ዜጎች እቃ ሃጅ ተርሚናል በሚባለው የአየር መንገዱ ማረፊያ ቦታ በብዛት ተዝረክርኮ እነወደሚገኝና የብዙዎች እቃ አድራሻ እንደሌለው የአይን እማኞች ገልጸውልኛል።  “አድራሻ ያለውን እቃም በሚመለከት የጅዳ ቆንስል ሰብስበን እንልከዋለን የሚል ቃል ከመስጠት ባለፈ ምንም አይነት ተጨባጭ እርምጃ እንዳልወሰዱም” በማለት እማኞች ገልጸውልኛል።
ከአስር ቀናት ያላነሰ እንግልታቸውን  በማስረዳት የተገፊ ድምጻቸውን እንዳሰማላቸው እንባቸውን እያዘሩና በብስጭት ያስረዱኝ ወገኖች በበኩላቸው “የአውሮፕላኑን ወጭ የሳውዲ መንግስት ከቻለ የኢትዮጵያ መንግስት እቃችን ይዘን እንድንገባ ለምን አላመቻቸልንም?  ሌላው ቢቀር መንግስት በሻንጣው መጫንና ለሳምታት ብስኩት እየተሰጠንና በውሃና ምግብ ግዠ የያዝነውን ገንዘብ ስናጠፋና ስንሰቃይ በዚህ ካልረዳን ወገኖቸ ማለቱ አልገባንም! ዜጎች አይደልንም?” ሲሉ በማጠየቅ በተጎዳ ሰሜት ገልጸውልኛል። ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወንድም እንደገለጹልኝ  ዜጎችን ማጓጓዙ እንደ በፊቱ በፍጥነት ባይከወንም አልፎ አልፎ መቶና ከመቶ በላይ ዜጎች በተገኘ የበረራ ክፍት ቦታ እየተላኩ መሆኑን በማስረዳት  ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ የመጣውን ይህንን ችግር የቆንስሉ ሰራተኞች በተደጋጋሚ ለቆንስል ሃላፊዎች ማሰማታቸውን በመግለጽ መፍትሔ ግን እስካሁን አለመሰጠቱን አክለው ገልጸውልኛል።
የካርጎ መዘጋት መዘዝና የነዋሪዎች ሮሮ-saudi ethio j2
የአየር መንገድ የካርጎ አገልግሎት ለወራት መሰናከል ተከትሎ በኢትዮጵያ አየር መንገድና በእቃ አቅራቢ የካርጎ ኤጀንቶች በደል ደረሰብን የሚሉ ዜጎች  ቅሬታ እያሰሙ ነው። ይህ ችግርም በነዋሪዎችና በካርጎ ኤጀንሲ ሰራተኞች መካከል ውዝግብ ማስከተሉ አልቀረም። የአየር መንገድ ወደ ኢትዮጵያ የሚደረገው ጉዞ ከስድስት ወራት በላይ ምክንያቱ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ከተዘጋ በኋላ ሰሞኑን ስራ መጀመሩ እየተሰማ ነው። ያም ሆኖ በጅዳ ዙሪያ ያሉ የካርጎ ኤጀንሲዎች “ወደ ኢትዮጵያ የካርጎ ግልጋሎት በተለያዩ አቅጣጫዎች እንሰጣለን!” በሚል ከፍተኛ ገንዘብ ለእቃው ማስጫኛ እየተቀበሉ እቃውን ቢረከቡም ከስድስት እሰከ አስር ወራት ለሚቆይ ጊዜ እቃውን በመጋዘ ቃላቸውን ጠብቀው እንዳላደረሱላቸው የመጫኛ ማስረጃቸውን እያሳዩ ቅሬታቸውን የገለጹልኝ በርካታ ዎች ናቸው። የሳውዲ ውጡ ህግ ከተነገረ ጀምሮና ከዚያም ወዲህ በተሰጠው የሰባት ወር የምህረት ጊዜ ጠቃሚ የሚሏቸውን ጥሪት እቃቸውን ለካርጎ ቢያስረክቡም አንድም በካርጎው መዘጋት በተጓዳኝ በካርጎ ኤጀንሲዎች ለአንድ ኪሎ እስከ 10 ሪያል በመክፈል እቃቸውን ቢያስገቡም እቃቸውን ደህንነት በማያውቁበት ደረጃ በንብረታቸው ላይ ብክነት እንዳስከተለባቸው እያዘኑ ሮሯቸውን አጫውተውኛል።
በጀዛን የዜጎች እንቢታ እና የህግ ታሳሪዎች ሮሮ -
በጀዛን “ወደ ሃገር እንግባ!” የሚሉ ነዋሪዎችን ጥሪ ተከትሎ የመጓጓዣ ሰነድ ለመስራት የጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት ተወካይ ዲፕሎማት ወደ ቦታው ያቀኑ ቢሆንም “ድረሱልን!” ሲሉ የነበሩ ዜጎች የውሃ ሽታ መሆናቸውን የኮሚቴውን በፊስ ቡክ መኖሩን የሚያሳውቀን የወገን ለወገንsaudi ethio j3የህዝብ ግንኙነት ፊስ ቡክ ጠቁሞናል።  በጀዛን የሚገኙ የህግ እስረኞችም በህግ ተይዘው ፍርድ ከተሰጣቸው በኋላ ለአመታት የሚጉላሉ እና በጥርጣሬ ተይዘው ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ዜጎች የድረሱልን ጥሪ ዛሬም አላቆመም። “ትኩረቱ ሁሉ ወደ ሃገር ተመላሾች መሆኑ ብቻ ሳይሆን ድሮም ተረስተናል አሁንም ተረስተናል!” እያሉ ነው!  በጀዛን ዙሪያ ባሳለፍነው ሳምንት መረጃ ያቀበለን የወገን ለወገን ደራሽ የህዝብ ግንኙነቱ ገጽ ባስተላለፈው መረጃ ወደ ሃገር ቤት ለመሄድ ሰላላሳዩት ዜጎች ትኩረት በመስጠት የዜጎችን ወደ ሃላፊዎች ለመቅረብ እና ለመሸኘት ፍላጎት አለማሳየታቸውን ሲገልጽም “እነሆ ግዜው ደረሰና የሁለቱም ሃገር መንግስታት ሁኔታዎችን አስተካክለው በሰማት (አሻራ) የሚሰጡበት ቦታ ተበጅቶላቸው ከቆንስላ ፅ/ቤት ተወካይ በቆንስል አህመድ የሚመራ ቡድን ለዜጎቻችን እዚያው እንዲሰራላቸው በማሰብ ወደ ጂዛን ተጓዙ። አሁንም እዚያው ናቸው። ነገር ግን ነገሮች እንደታሰቡ እየሄዱ አይደለም። ታስቦላቸው የተሄደላቸው ወገኖች እየወጡ አይደለም የሚል አሳሳቢ ዜና ሰማን። አሁን ባለው ሁኔታ ወደ ማቆያ የሚገቡት ሰዎች በቀን መቶም እንደማይደርሱ ተገለፀልን። ከጂዳ ለዚህ ጉዳይ የተንቀሳቀሰው ልኡካን አሁንም ለማገልገል ይጠብቃል፡ ምንም የሚታይ ነገር ግን የለም። በጂዛን አጎራባች ወደ ሆኑ ከተሞችም ከአካባቢው ማህበረሰብ አምስት አምስት ሰዎች ለቅስቀሳ ተልከዋል። ቢሆንም ወገናችን ዜጎቻችን የሚወጡ አይነት አይደለም። በጣም ሚገርም ነው።” ይላል።  የህግ ታሳሪዎች በበኩላቸው የቆንስል ሃላፊዎችን አነጋግረዋቸው “ለእናንተ ጉዳይ አልመጣንም!” እንዳሏቸው ገልጸውልኛል። የህዝብ ግንኙነቱ ዜጎች ወደ ኋላ ስላፈገፈጉበት ጉዳይም ሆነ በደል ደረሰብን ስለሚሉ ህጋዊ ታራሚዎች የሰጠው መረጃ የለም ። በወገን ለወገን ደራሽ ኮሚቴ ለአንድ ወር በስራ አስፈጻሚነት የሰራሁ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ለቆንስል ሃላፊዎች ያቀረብኩት የዜጎች አቤቱታ እንዲታረም በተደጋጋሚ አሳስቤ የነዋሪውን አቤቱታ በጀርመን ራዲዮ በማቅረቤ በተወሰደ የ “በዲሲፕሊን!” እርምጃ ከኮሚቴው አባልነት በተጽዕኖ መነሳቴ ይታወሳል!
የውጭ ጉዳይ ልዑካን በጅዳ:-
በሳውዲ አረቢያ የሪያድ ኢንባሲ አምባሳደርን ጨምሮ ሶስት አባላትን የያዘው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቡድን ከሶስት ቀናት በፊት ጅዳ ገብተዋል። ልዑካኑ በእስካሁኑ ቆይታቸው የኢህአዴግ የድርጅት አባላትንና የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎችን በዝግ ያነጋገሩ ሲሆን የውይይታቸው ትኩረት በመጡበት የዜጎችን ወደ ሃገር መግባት ጉዳይ የማፋጠን ስራ ይሁን በሌላ ተዛማጅ ጉዳይ የሚታወቅ ነገር የለም። የልዑካን ቡድኑsaudi ethio j4 አባላት በእስካሁን ቆይታቸው አደጋውን ለመከላከል በጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች የተቋቋመውን የወገን ለወገን ደራሽ ጊዜያዊ ኮሚቴ እስካሁን ያላነጋገሩ መሆኑ ታውቋል። የልዑካኑ ቡድንን ኮሚቴውን አለማነጋገሩ ቅያሞት የገባቸው አንዳንድ አባላት በበኩላቸው የዜጎች እንግልት በቅንጅት ጉድለት እየተበራከተ በሄደበት በዚህ አጋጣሚ ኮሚቴው ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ላልቻለበት ሁኔታ የቆንስሉ እና የአመራሩ ድክመት እንደሆነ በማስረዳት እያደር ለይስሙላ የተቋቋመ እንጅ ወገንን ለመርዳት ከመካዝን ያለውን ውሃ ለማደል እንኳ አቅም አጥቷል በሚል ከማህበረሰቡ ወቀሳ እየቀረበበት መሆኑን በግልጽ አጫውተውኛል።
በሳውዲ አረቢያ የሪያድ ኢንባሲ አምባሳደርን ጨምሮ ሶስት አባላትን የያዘው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑክ በጅዳ ቆንስል የመንግስታችን ተወካዮች ለተጠቀሱትና በከባቢው ላሉ ችግሮች አፋጣኝ እርምጃ ካልወሰዱ አደጋውን መታደግ ከማንችልበት ደረጃ እንዳይደረስ የብዙ ነዋሪዎች ስጋት ሆኗል። የሳውዲ መንግስትን እና የኢትዮጵያ ኢንባሲና ቆንስል በማስታወቂያ ብቻ የተደገፈ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ተከትሎ “ሰነድ የሌላችሁ ዜጎቸወ ከሳውዲ ውጡ!” በሚል ማስተላለፋቸው አይዘነጋም። ያም ሆኖ ነዋሪው በርካታ ያልተሟሉ ቅድመ ሁኔታዎችን በማቅረብ ለመውጣቱ ጥሪ “አሻፈረኝ!”  ያሉትን በሽዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ሮሮ እና ጥያቄ ለመስማትና አፋጣኝ የመፍየትሔ እርምጃ ለመውሰድም የመንግስት ሃላፊዎች ህዝባዊ አስቸኳይ ጥሪ በመጥራት መፍትሔ ያመላክቱ ዘንድ ደግሜ ደጋግሜ እመክራለሁ!
ዛሬም የመረጃ ክፍተቱ ይዘጋ፣ የምንናገረው ተጨባጭ መረጃ መሆኑን አጣርታችሁ መፍትሔ አፈላልጉ ስል ደጋግሜ “ጀሮ ያለው ይስማ!” እላለሁ !
ቸር ያሰማን!

Thursday, January 2, 2014

የመንግስት ባለስልጣናት በቀጥታ እጃቸውን አስገብተዋል::



የሕወሓት ታማኝ እና ታዛዥ ሰዎችን የሰበሰበው እና ራሱን የኦሮሞ ህዝብ ወኪል አድርጎ በሕወሓት የጦር እልቅና ሕዝቡን እየጨቆነ የሚገኘው ኦሕዴድ/ኢሕኣዴግ በበዴሌ ቢራ በኩል የሚደረገውን የቴዲ አፍሮ የፍቅር ጉዞ እንዲቋረጥ አስፈላጊውን ጥረት እያደረገ ሲሆን ከፍተኛ አመራሩ ወደ ፋብሪካው ከመደውል እና ውጥረት ከመንዛት ጀምሮ እስከ ደብዳቤ መጻፍ ድረስ የደረሰ መሆኑን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመዋል::እንዲሁም በተጨማሪ ኢሕኣዴግ በኦሮምኛ ቋንቋ በሚተላለፉ የመንግስት ሚዲያዎች ሁሉ ጸረ ምንሊክ የጥላቻ ዘገባዎችን በተከታታይ በወጣ ገባ እያቀረብ የሚገኝ ሲሆን ይህም እንዲቀጥል ተደርጓል:: በኦሮሚያ ክልል ከተሞች የታቀዱ መንግስት ሰራሽ ተቃውሞ ሰልፎች ይካሄዱ አይካሄዱ በኦሕዴዶች መካከል ጭቅጭቅ ፈጥረዋል::
የበደሌ ቢራ ፋብሪካ ባለቤት የሆነው የአውሮፓው ሄንከንስ ቢራ ከቴዲ አፍሮ ጋር ባደረገው ውል የመጀመሪያው ክፍያውን 1.5 ሚሊዮን ብር በቴዲ አፍሮ ስም በቼክ ቢሰጥም ለጊዜው ብሩ እንዳይገባ የተደረገ ሲሆን ኮንሰርቱ ባይካሄድም ገንዘቡ መከፈሉ አይቀሬ ነው::የሄይከን በደለ ቢራ ኮንሰርቱ እንዳይቋረጥ እስካሁን ከመንግስት ባለስልታናት ጋር ግብግብ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን የፋብሪካው ማናጀር አማካሪ የሆነው የኦሮሞ ብሄር ተወላጁ ለኦሮሞ ህዝብ የበደለ ቢራ ካሳ መክፈል አለበት የሚል ሃሳብ በማቅረቡ አለመግባባት ስለተከሰተ ከስራው የለቀቀ መሆኑ ታውቋል::
ይህን ሰሞን ኦሕዴድ ለትምህርት አሜሪካን አገር የላከውና በዲሲ የወያኔ ኤምባሲ መኖሪያው አድርጎ ከሕወሓት ዲፕሎማቶች ጋር ሳይስማማ ከኤምባሲው ቅጥር ግቢ የተባረረው ጽንፈኛው ኦቦ ሜንጫ የተባለው ግለሰብ በቴዲ አፍሮ እና በበደሌ ቢራ ላይ እና በሃገር ኢኮኖሚ ላይ የጠባበኝነት እና የጥላቻ ዘመቻ በመክፈት ሕወሓት የሆኑ የቀበሮ ለምድ ለብሰው ለኦሮሞ የቆሙ አስመሳዮች ለስልታን እድሜ ማስረዘሚያ ይረዳቸው ዘንድ ሲያሟሙቁ እንደነበር ይታወሳል::ይህ አጀንዳ ያገናኛቸው ኦቦ ሜንጫ እና ኦሕዴድ በሕወሓት አበረታችነት በጋራ ዘመቻውን በመምራት ክንሰርቱን ለማስቆም አስፈላጊውን ወደ ተግባር በመግባት ስራቸውን ጀምረዋል::
የበዴሌ አምራች የሆነው አውሮፓዊው ካምፓኒ የፍቅር ጉዞ የተባለው የቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ኮንሰርትን ለማቆም ምንም አይነት ችግሮች አለመኖራቸውና ኮንሰርቱ በታቀደለት ቀን እንደሚካሄድ ደጋግሞ ቢናገርም የኦሕዴድ አመራሮች እና ጠባብ ዲያስፖራዎች በጋራ ከተጻፈው ደብዳቤ በተጨማሪ በተየቡት መሰረት ኮንሰርቱ ቢካሄድ በሚነሳው የሕዝብ ቁጣ ሊከተል የሚችል አደጋ በማለት በማስፈራራት እንዲሁም የተለመደው የጸጥታ ሃይሎች እጥረት በሚል ለማስተጓጎል ጥረቱ ውስጥ ውስጡን እንደቀጠለም ይገኛል::ከዚህ ክንሰርቱን ከማስቆም ጀርባ የዲያስፖራ ኦሮሞ ጽንፈኞችን ዘመቻ አለመሳካቱ ያንገበገባቸው የሕወሃት ባለስልጣናት ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል::

የወያኔን “አንድ ለአምስቶች” ወያኔን ለማዳከም እንጠቀምባቸው


ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመቆጣጠር እንዲያመቸው “አንድ ለአምስት” አደረጃጀትእያደራጀው ነው።  ይህ አደረጃጀት  ስታሊን ለሠላሳ ዓመታት ሶቭየት ኅብረትን፤ ኤንቨር ሆዣ ደግሞ ለአርባ ዓመታት አልባኒያን ጠፍረው የገዙበት ስልት ነው። በዚህ የአገዛዝ ስልት መሠረት እያንዳንዱ ሰው በመዋቅር ተይዞ አራቱ ለአንዱ መረጃ የሚያቀብሉበት ሥርዓት ይዘረጋል።   
ሕዝብን በድርጅት አባልነት ስም በመዋቅር ማስገባት ለአንባገነኖች የሚሰጠው ዋነኛ ጥቅም የማኅበረሰብን ስነልቦና መስበሩ ነው። ይህ አወቃቀር ዜጎች የአምባገነኑን መንግሥት ኃይል መጠን በላይ አግዝፈው፤ ራሳቸውን ደግሞ አንኳሰው እንዲመለከቱ ያደርጋቸዋል። ዜጎች፣ “መንግሥት እያንዳንዱን ነገር አብጠርጥሮ ያውቃል” በሚል የፍራቻ ቆፈን እንዲያዙ ያደርጋቸዋል። እያንዳንዱ ሰው ጓደኛውን እንዲጠረጥር በማድረግ አምባገነኖች የስለላ ተቋማቸዉ ጠንካራና ሁሉን-አዋቂ እንዲመስል ያደርጉታል።
ይሁን እንጂ የማኅበረሰብ ስነልቦና ካልተሰበረ፤ በፍራቻ ፋንታ በራስ መተማመን ከዳበረ ማንም ያደራጀው ማን ነፃ ህሊና ያላቸው አባላት ድርጅቱን ራሳቸውን ነፃ ለማውጣት ይጠቀሙበታል። አሁን በደረስንበት ሁኔታ ይህንን በአገራችን ተግባራዊ የማድረግ ሰፊ እድል አለን።  የኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ ፍራቻ እራሱን ነፃ እያወጣ ነው። ወያኔ ከስታሊንም ሆነ ከኤንቨር ሆዣ በተለየ መንገድየአመለካከትና የርዕዮተዓለም ጉዳይ የሚያሳስበዉ ሀይል አይደለም።ቢያሳስበውም የሕዝብን ቀልብ የሚይይዝበት ምንምነገር የለውም። ይህ ባህሪይዉ ነዉ ነው ወያኔ በእጅጉ የተጠላ ኃይል እንዲሆን ያደረገው። 
እንዲህ በግዴታ እንጂ በእምነት ያልተሰባሰቡ ሰዎች ባሉበት ሁኔታ ተመሳሳይ ፀረ-ወያኔ አቋም ያላቸው ሰዎች በአንድ “አንድ ለአምስት” ሕዋስ ውስጥ የመገኘታቸው አጋጣሚ የጎላ ነው።  እነዚህ አባላት በግልጽ ከተነጋገሩበት ሕዋሱን ለፀረ-ወያኔ ትግል ሊጠቀሙበት ይችላሉ።  በመሆኑም ወያኔን ለመጨቆኛ መሣሪያነት ያዋቀረውን “አንድ ለአምስት” ራሱ ወያኔን መታገያ ብሎም ማዳከሚያ መሣሪያ ማድረግ ይቻላል። “አንድ ለአምስትን” በሽፋንነት በመጠቀም ውስጥ ውስጡን መጀራጀት በስፋት  ልንይዘዉና ልንሰራበት የሚገባ ስትራቴጄ ነው።
የወያኔ “አንድ አምስት” የኑሯችን አካል እየሆነ መጥቷል። በአንዳንድ ቦታዎች አለመደራጀት ሥራ የሚያሳጣ እየሆነ ነው።  በማናቸውም ምክንያት ራሳቸውን ወያኔ ጉያ ውስጥ ያገኙ የሕዝብ ወገኖች ካሁን በኋላ መሥራት ያለባቸው ወያኔን ከውስጥ ሆኖ የማዳከምን ሥራ ማፋጠን ነው። ለዚህ ደግሞ እንደ “አንድ ለአምስት” አመቺ የሆነ መዋቅር አይገኝም።
በአሁኑ ሰዓት ግንቦት 7 ሕዋሳቶቹን በሁሉም ቦታ ለማዋቀር ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል፤በዚህም መሠረት  የግንቦት 7 ሕዋሶች በሁሉም የአገሪቱ አካባቢ ባልተማከለ መልኩ በብዛት እየተመሠረቱ ነው። ከዚህ ህዋሳቶችን ከመዘርጋት ሥራ ጎን ለጎን ህዝቡ በያለበት የወያኔንየራሱንመዋቅር በመጠቀም ወያኔንና ስርዐቱን መገዝገዝ አለበት።
ይህንን ለማድረግ የግንቦት 7ን መመሪያ መጠበቅ አያስፈልግም። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በራሱ መንገድተግባራዊ ሊያደርገው የ የሚችለዉ ነገር ነው።
በመሆኑም ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የወያኔ “አንድ ለአምስቶችን” ወያኔን ለማዳከም እንጠቀምባቸው የሚል ጥሪ ያቀርባል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!