ምንሊክ ሳልሳዊ በተጭበረበረ ፖለቲካ ላይ ወያኔ እየገነባ ያለው ኢኮኖሚ እየተንኮታኮተ መሆኑ ይህንን ተከትሎ ከፍተኛ የሆኑ የገንዘብ ተቋማት ብሄራዊ ባንክን ጨምሮ ሙስናው በፈጠረው የኢኮኖሚ እብደት አጣብቂኝ ውስጥ መሆናቸው ተረጋግጧል::ተነሳሽነት ካለ በሃገሪቱ ውስጥ ያሉ ችግሮች የሚፈቱ እና አስቸጋሪ ያልሆኑ ናቸው:: ሆኖም ከፍተኛ የሆኑ የሕወሓት ባለስልጣናት በሙስና እና በፖለቲካ ማጭበርበር የህዝብ ችግሮች እንዳይፈቱ እያደረጉ ነው:: | |
የኢኮኖሚው መንኮታኮት እና የንግዱ እንቅስቃሴ ዝምታ ምንም አይነት ኤክስፐርት መቅጠር ወያንም በጉዳዩ ላይ ተቋም አዋቅሮ ምርምር እና ጥናት ማድረግ አያስፈለገውም በገሃድ እየታየ ያለ ነው:: የመንግስት ሚዲያዎች የሃሰት ፕሮፓጋንዳ እና የበለጸጉት ሃገራት ብሄራዊ ጥቅምን ተመርኩዞ የሚወጣ የእድገት ቁጥር ቁልል ይህንን ለመደበቅ አልቻሉም::በአደባባይ በይፋ እያየነው ነው::በሃገሪቷ ላይ የተፈጠረው ሙስናን መሰረቱ ያደረገው የዋጋ ግሽበት እና የውጪ ምንዛሪ አቅርቦት ባዶ መሆን ሌተር ኦፍ ክሬዲት ለመክፈትም አለመቻሉ የፋብሪካ ውጠቶችን ለማምረት የሃገር ውስጥ ማኑፋክቸሮች ለምርቶቻቸው የሚያስፈልጓቸውን በወቅቱ በቦታል አለማግኘት የውጪ ምንዛሬ አቅርቦት ባዶነት ለስራቸው መኮላሸት ምክንያት እየሆኑ ሲሆን የባንክ ብድሮች ሙስናን መሰረት አድርገው መስራታቸው የመንግስት ድርጅቶች አስፈላጊውን ክፍያዎች በገንዘብ እጥረት አለማድረጋቸው የንግዱን እንቅስቃሴ እያንኮታኮተው ሲሆን ይህ ደግሞ የሰራተኛ መፈናቀልን እና ሰርቶ የመኖር መብት ማጣትን ውጤታማ እያደረገ ነው::ገስት ሃውስ፣ ጫት ቤት፣ ሺሻ ቤት፣ማሳጅ ቤት፣… በየቦታው መስፋፋት የሃገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት ሳይሆን ውድቀት እና የትውልድን ዝቅጠት ያመለክታል:: | |
በወያኔ መንግስት ነጋዴውን እና ንግዱን እንመራለን በሚሉ ባለስልጣናት እና ሰራተኞቻቸው ዙሪአ እንዱም ከነጋዴው ጋር በመካከላቸው መተማመት የጠፋ ሲሆን የሙስናው ገመድ ሊያንቀኝ ይችላል በሚል ስልጣናቸው ሆኖ ያሉ ሰዎች ማንኛውንም ስራዎች ለመስራት የበላይና የበላይ ትእዛዝ የሚጠብቁበት በተጨማሪም ቀላል የሆኑ ፍቃድን የማውጣት እና የመመለስ ስራዎች ችግር እየፈጠሩ መሆኑ ሲታወቅ የግል ጥቅመኝነትን እንደ ዋነኛ መዘውር ማድረጋቸው ቢሮክራሲውን ተብትበውት ለኢኮኖሚው መንኮታኮት የፖለቲካው ድርሻ ጭነት ዋነኛው መሆኑን በገሃድ እየታየ እና ለሃገር እና ለህዝብ ደንታ የሌላቸው ከፍተኛ ባለስልጣናት ለራሳቸው ሙስና እና ማጭበርበር ያመቻቸው ዘንድ በፈጠሩት ሰንሰለት ኢኮኖሚውን በባዶ አስቀርተውታል:: | |
ፖለቲካው የወለደው ጭካኔ የፈጠረው የኢኮኖሚ መዛባት ህዝቦች የሚያገኙትን መረጃ በስራት እንዳያገኙ የህትመት ውጤቶችን እየጎዳ ነው::ይህ ከወያኔ ባለስልጣናት የሚተላለፉ መመሪያዎች ውጤት የሆነው እና ሀገሪቷን ለድቀት የዳረጋት የስልክ ትእዛዝ የህዝቦችን መረጃ የማግኘት መብት ከመጉዳቱም በላይ ወረቀት እና ቀለም የለም፣ ማሽን ተበላሽቷል፣ …በሚል ምክንያት ፕሬሱ የሕትመት ችግር እያጋጠመው ነው፡፡ ከምጣኔ ሃብት እንቅስቃሴ አኳያ ሲታይ እጅግ አስቸጋሪ ስለሆነ ኢኮኖሚውን አንገላቶት ገደል ጨምሮታል:: | |
ኢኮኖሚውን ያጠናክራሉ በሚባሉ የንግድ ተቋማት የሚሰማውን አቤቱታ እና ቅሬታ የሚያዳምጥ በመጥፋቱና ቅሬታ ሰምቶም መፍትሄ ና ውሳኔ የሚሰጥ አካል ባለመኖሩ መተማመኖች በመስፋታቸው መዋእለ ንዋዬን አፍስሼ በኋላ ቢያስቆሙኝስ ቢነጥቁኝስ በማለት የሚሰጋው ነጋዴ ጨምሯል ፡፡ ለችግሮቻችን መፍትሄ ስጡንየሚለው መብዛቱ አዳማጭ መንግስት በመጥፋቱ ሥራ ለማቆም የሚገደዱ እየበዙ ነው፡፡ በባንክ ዕዳ ተወጥረው የሠራተኛ ደመወዝ እየከፈሉ፣ ለቢሮ፣ ለመጋዘን፣ ለኤሌክትሪክና ለተለያዩ ወጪዎች በመዳረግ ገቢ የማያውቁ በርካታ የሥራ ዓይነቶች አሉ፡፡ ድርጅታቸው እንዳይዘጋ አንድ ቀን ችግሩ ይፈታል በሚል ተስፋ፣ እንዳይቀጥሉ ደግሞ የወጪ መብዛት እያስጨነቃቸው ጭንቅ ውስጥ የገቡ በርካታ ናቸው፡፡ ሥራቸውን ያቆሙም አሉ፡፡ | |
በሃገሪቱ የተፈጠረው ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግዥበት እና የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት ዜሮ መሆን የገንዘብ ምንጭ ይሆናሉ የተባሉትን ሁሉ በባዶ አባዝቶ ከየባንኩ ግድግዳ እያላጋቸው ነው::ወያኔ ምእራባውያንን ለማታለል ለፖለቲካው ፍጆታ ለመበልጸግ ሲል የጀመራቸው ስማቸው ልማት የተባሉት የሃገሪቷን የገቢ አቅም ያላመዛዘኑ እና የግሉን የገንዘብ ተቋማት የተፈታተኑ ከመሆኑም በላይ ባንኮች በየቦታው ያላቸውን አክሲዮኖች እስከመሸጥ እንዲደርሱ አድርጓቸዋል:: | |
ፖለቲካን ተገን አድርገው የተቋቋሙ የንግድ ድርጅቶች ሌላውን የንግድ ክፍል አላሰራ ከማለታቸውም አስፈላጊውን የግብር እና የቀረጥ ገቢዎች አላመክፈላቸው እና ትልልቅ የንግድ ገቢዎችን በሞኖፖል ገዢውን ፓርቲ ተንተርሰው ማንቀሳቀሳቸው ለሃገሪቱ የኢኮኖሚ መውደቅ ሌላው ምክንያት ነው:: | |
በአጠቃላይ ያለው የወያኔ ጁንታ በፖለቲካው ላይ ተመርኩዞ የፈጠረው ኢኮኖሚ ምንም ውጤት አለማምጣቱን መመልከት ስለተሳነው ኢትዮጵያውያን ሁሉ በጋራ ይህንን አጭበርባሪ ስርኣት ገርሲሰን መጣል የዜግነት ግዴታችን መሆኑን ለማሳሰብ እወዳለሁ:: | |
Monday, January 20, 2014
አሳሳቢና የወደቀ እንጂ አበረታች የኢኮኖሚ እድገት የለንም!!
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment