Thursday, January 2, 2014

የወያኔን “አንድ ለአምስቶች” ወያኔን ለማዳከም እንጠቀምባቸው


ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመቆጣጠር እንዲያመቸው “አንድ ለአምስት” አደረጃጀትእያደራጀው ነው።  ይህ አደረጃጀት  ስታሊን ለሠላሳ ዓመታት ሶቭየት ኅብረትን፤ ኤንቨር ሆዣ ደግሞ ለአርባ ዓመታት አልባኒያን ጠፍረው የገዙበት ስልት ነው። በዚህ የአገዛዝ ስልት መሠረት እያንዳንዱ ሰው በመዋቅር ተይዞ አራቱ ለአንዱ መረጃ የሚያቀብሉበት ሥርዓት ይዘረጋል።   
ሕዝብን በድርጅት አባልነት ስም በመዋቅር ማስገባት ለአንባገነኖች የሚሰጠው ዋነኛ ጥቅም የማኅበረሰብን ስነልቦና መስበሩ ነው። ይህ አወቃቀር ዜጎች የአምባገነኑን መንግሥት ኃይል መጠን በላይ አግዝፈው፤ ራሳቸውን ደግሞ አንኳሰው እንዲመለከቱ ያደርጋቸዋል። ዜጎች፣ “መንግሥት እያንዳንዱን ነገር አብጠርጥሮ ያውቃል” በሚል የፍራቻ ቆፈን እንዲያዙ ያደርጋቸዋል። እያንዳንዱ ሰው ጓደኛውን እንዲጠረጥር በማድረግ አምባገነኖች የስለላ ተቋማቸዉ ጠንካራና ሁሉን-አዋቂ እንዲመስል ያደርጉታል።
ይሁን እንጂ የማኅበረሰብ ስነልቦና ካልተሰበረ፤ በፍራቻ ፋንታ በራስ መተማመን ከዳበረ ማንም ያደራጀው ማን ነፃ ህሊና ያላቸው አባላት ድርጅቱን ራሳቸውን ነፃ ለማውጣት ይጠቀሙበታል። አሁን በደረስንበት ሁኔታ ይህንን በአገራችን ተግባራዊ የማድረግ ሰፊ እድል አለን።  የኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ ፍራቻ እራሱን ነፃ እያወጣ ነው። ወያኔ ከስታሊንም ሆነ ከኤንቨር ሆዣ በተለየ መንገድየአመለካከትና የርዕዮተዓለም ጉዳይ የሚያሳስበዉ ሀይል አይደለም።ቢያሳስበውም የሕዝብን ቀልብ የሚይይዝበት ምንምነገር የለውም። ይህ ባህሪይዉ ነዉ ነው ወያኔ በእጅጉ የተጠላ ኃይል እንዲሆን ያደረገው። 
እንዲህ በግዴታ እንጂ በእምነት ያልተሰባሰቡ ሰዎች ባሉበት ሁኔታ ተመሳሳይ ፀረ-ወያኔ አቋም ያላቸው ሰዎች በአንድ “አንድ ለአምስት” ሕዋስ ውስጥ የመገኘታቸው አጋጣሚ የጎላ ነው።  እነዚህ አባላት በግልጽ ከተነጋገሩበት ሕዋሱን ለፀረ-ወያኔ ትግል ሊጠቀሙበት ይችላሉ።  በመሆኑም ወያኔን ለመጨቆኛ መሣሪያነት ያዋቀረውን “አንድ ለአምስት” ራሱ ወያኔን መታገያ ብሎም ማዳከሚያ መሣሪያ ማድረግ ይቻላል። “አንድ ለአምስትን” በሽፋንነት በመጠቀም ውስጥ ውስጡን መጀራጀት በስፋት  ልንይዘዉና ልንሰራበት የሚገባ ስትራቴጄ ነው።
የወያኔ “አንድ አምስት” የኑሯችን አካል እየሆነ መጥቷል። በአንዳንድ ቦታዎች አለመደራጀት ሥራ የሚያሳጣ እየሆነ ነው።  በማናቸውም ምክንያት ራሳቸውን ወያኔ ጉያ ውስጥ ያገኙ የሕዝብ ወገኖች ካሁን በኋላ መሥራት ያለባቸው ወያኔን ከውስጥ ሆኖ የማዳከምን ሥራ ማፋጠን ነው። ለዚህ ደግሞ እንደ “አንድ ለአምስት” አመቺ የሆነ መዋቅር አይገኝም።
በአሁኑ ሰዓት ግንቦት 7 ሕዋሳቶቹን በሁሉም ቦታ ለማዋቀር ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል፤በዚህም መሠረት  የግንቦት 7 ሕዋሶች በሁሉም የአገሪቱ አካባቢ ባልተማከለ መልኩ በብዛት እየተመሠረቱ ነው። ከዚህ ህዋሳቶችን ከመዘርጋት ሥራ ጎን ለጎን ህዝቡ በያለበት የወያኔንየራሱንመዋቅር በመጠቀም ወያኔንና ስርዐቱን መገዝገዝ አለበት።
ይህንን ለማድረግ የግንቦት 7ን መመሪያ መጠበቅ አያስፈልግም። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በራሱ መንገድተግባራዊ ሊያደርገው የ የሚችለዉ ነገር ነው።
በመሆኑም ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የወያኔ “አንድ ለአምስቶችን” ወያኔን ለማዳከም እንጠቀምባቸው የሚል ጥሪ ያቀርባል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

No comments:

Post a Comment