Thursday, July 31, 2014

Why is President Obama Hosting Some African Dictators?


July 29, 2014
by Dula
About to become a lame duck President, Obama is holding a roundtable discussion on Africa with African leaders. I guess better late than never. It is scheduled to be held on August 5-6 in Washington D.C. Many of the African leaders bring lots of baggage of crony capitalism, anti-Gay legislation, corruption, abuse of human rights, simply absolute lack of rule of law.
For example, Prime Minister Hailemariam Desalegn and his party have been in power for the last 23 years, and their legacy is dreadful, as Ethiopia is ranked the second poorest and second sickest country in the world, where over 70% of the population goes hungry on daily basis. The primary reason for the dreadful situation is government control of the economy.
A young boy waiting  in front of his tukul for his mother as she arrives with a body of his 4-year old dead sister  who died of malnutrition in Shashemene, Ethiopia: Source: NBC: & .Creeping famine-is-back-to-Ethiopia
A young boy waiting in front of his tukul for his mother as she arrives with a body of his 4-year old dead sister who died of malnutrition in Shashemene, Ethiopia: Source: NBC: & .Creeping famine-is-back-to-Ethiopia
Like North Korea, the regime controls everything, spies on everybody, at the village level as well as via the Internet, even though less than 1% of the people have Internet access. Like North Korea, the state controls all the land, telecommunication, Internet, mining, banking, and major industries directly or through cronies.
In Ethiopia, like in North Korea, there is no freedom of the press, freedom of assembly, no free or fair election, no property rights, and simply no rule of law when it comes to the majority of the citizens. The ruling party representing less than 6% of the population like the old Apartheid regime rules through its private and ethnic army and cronies.
African leaders democrats, and dictators like Mr. Desalegn are coming to the USA under the invitation of President Obama for a roundtable discussion on Africa. It would have been more natural to invite only those countries respecting and applying democratic principles. Furthermore, winning and dinning with African dictators will mean nothing unless President Obama has a concrete plan and he can make it stick.
For example, he can propose a Marshall Plan for Africa like the way Truman did for Europe. He can prompt African leaders to spend less on the military, because the armies are primarily used to keep the one party dictatorship, and spend more on education, technology, and economic development. Adopt a common language, privatize the economy, end corruption, respect human and property rights, rule of law, and form a stronger economic and political union.
Raging ethnic and religious tension are primarily fueled by lack of hope and oppression. The primary culprit for the hopeless situation, the dictators thrive and survive with U.S. support and largesse. Some will go by the wayside without massive Western aid. This gives President Obama tremendous leverage to promote democratic and economic reform in the continent. For example, the rabid anti-Muslim and anti-homosexual government of Ethiopia lead by Mr. Desalegn was forced last March by Washington to rescind an anti-homosexual legislation (Homosexuality-non pardonable) that he orchestrated through his rubber-stamped parliament.
The Ethiopian regime pretended for long for things that it is not in order to earn respect and foreign aid. The Ethiopian regime spends huge sums of money to make sure the West does not notice the cruel and evil system and to portray the regime incorrectly anti-terrorist and democratic.
Azusa Pacific University Board unanimously withdrew a plan to award an honorary degree to Mr. Desalegn on July 31 because of gross human rights violations by his regime (university-withdraws-honor). In 2003, Texas Southern University canceled a planned event with an Ethiopian government delegation for similar reason.
President Obama can rise to the challenge if he dared too. Pushing democratic values and free market economic development strategies are critical. President Truman provided a lifeline to a devastated Europe and created strong democratic allies for the U.S. The total cost for the Marshall Plan from 1948-1952 was $13.3 billion. President Obama has the option to embark on a similar, bold political and economic agenda for Africa, while opening a huge market three times that of Europe for American businesses.
By Dula Abdu, dula can be reached at dula06@gmail.com (article was adopted from previous articles from similar topics).

Tuesday, July 29, 2014

ሰበር ዜና አቶ በረከት ስምኦን.........



ሰበር ዜና አቶ በረከት ስምኦን ድፍት እንዳለ ምንጮች አመላከቱ!
ሳውዲ አረቢያ ጅዳ ከተማ ለህክምና የገቡት እኚህ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን በተለምዶ ብግሻን የሚባል አንድ ትልቅ ሆስፒታል 4 ፎቅ የልብ ቀዶ ጥገና በተሰካ ሁኔታ እንደተደረገላቸው የሚናገሩ ውስጥ፡ አውቂ ምንጮች ከቀዶ ጥገና ክፍሉ ከወጡ በሃላ የባለስልጣኑ የጤንነት ሁኔታ ወደ ነበረበት ሊመለስ ባለመቻሉ ወደሌላ ክፍል ተዘዋውረው የቀርብ ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ይህ በንዲህ እንዳለ አቶ በረከት ስምኦን ወደተኙበት ክፍል ዶክተሮች ባልተለመደ ሁኔታ እየተቻኳሉ ሲገቡ እና ሲወጡ ያዩ የአይን እማኞች የባለስልጣኑንን በህይወት መትረፍ ይጠራጠራሉ።
ከአንድ ቀን በፌት እዚህ ጅዳ ሳውዲ አረቢያ በሼክ አላሙዲን ማካኝነት አንድ ኢትዮጵያዊ ዶክተር አስከትለው ለህክምና እንደገቡ የሚነገረው አቶ በረከት ስምኦን እስካሁን ስላሉበት ሁኔታ በትክከል መናገር ባይቻለም አብረዋቸው ከመጡት የቀርብ ቤተሰቦቻቸው ውስጥ ሚስታቸው እና ሴት ልጃቸው ሆስፒታል ውስጥ ነጠላቸውን ወገባቸው ላይ አስረው ሲላቀሱ ያዩ ታዛቢዎች የባለስልጣኑን በህይወት መኖር ጥያቄ ምልክት ውስጥ እንደከተተው ይነገራል። ለአቶ በረከት አርቴፊሻል የፕላስቲክ ቧንቧ ከልባቸውጋር በድጋፍ የተገጠመ መሆኑን የሚገልጹት የሆስፒታሉ ምንጮችየባለስልጣኑን የልብ መት የሚለካ ግስቲር በተጓዳኝ መገጠሙን እና የልብ ቀዶ ጥገናው በተሳካ ሁኔታ መካሄዱን ያረጋግጣሉ።
አቶ በረከት ስሞኦን ቀደም በልው ድቡብ አፍሪካ ውስጥ ተመሳሳይ የሆነ የልብ ቀዶ ጥገናተደርጎላቸው እንደነበር የሚያሳዩ መረጃዎች ምናልባት በልብ ቀዶ ህክምናው ወቅት ስህተቶች ተፈጥረው በመንግስት ባላስልጣኑ ላይ አደገኛ ኢንፌክሸን ሳይፈጠር እናዳልቀር ይነገራል። አቶ በረከት ስሞን አሁን ስላሉበት የጤንነት ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግስት ምንም ያለው ነገር ባይኖረም ስለእህ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን የጤንነት ሁኔታ ተጨማሪመረጃ ለመስብሰብ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት የሚገኙ አንዳንድ ዲፕሎማቶችን ለማነጋገር ያደረኩት ሙከራ እስካሁን አልተሳካም ።
ምንጭ ታምራት ይደጎ

Sunday, July 27, 2014

ኦሮምኛ እንናገራለን፡፡ ግን ኢትዮጵያውያኖች ነን፡፡ በኢትዮጵያዊነት ማንም ከእኛ አይበልጥም፡፡( አቶ ቡልቻ ደመቅሳ )

ስለዚህ ነው እንገነጠላለን የሚሉ ሰዎች ያልተሳካላቸው፡፡

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ለረጂም ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ተሳትፏቸው ይታወቃሉ፤ በተለይም የኦሮሞን ህዝብ መብት እናስከብራለን ብለው የፖለቲካ ፓርቲ መስርተው ከታገሉት ሰዎች መካከል ከፊተኞቹ አንዱ ናቸው፡፡ አቶ ቡልቻ አሁን ስላሉበት የፖለቲካ ተሳትፏቸውና ስለተለያዩ አንኳር ሀገራዊ ጉዳዮች ከጋዜጠኛ በላይ ማናዬ ጋር ቆይታ አድርገዋል፤ እንዲህ ይቀርባል፡-
ነገረ ኢትዮጵያ፡- አቶ ቡልቻ በተለያዩ መድረኮች ላይ በፖለቲካ ተሳትፎዎ ነው የሚታወቁት፤ ነገር ግን አሁን ላይ ከፓርቲ ፖለቲካ ተሳትፎ የራቁ ይመስለኛል፡፡ በዚህ ወቅት ስላልዎት የፖለቲካ ተሳትፎዎ በአጭሩ ቢነግሩኝ?
አቶ ቡልቻ፡- እኔ ከመድረክ የገባሁት የኦፌኮ መሪ ሆኜ ነው፡፡ አሁን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) እስኪ ወጣቶቹ ይስሩ፣ እነሱ ሲሰሩ የሚቻለኝን እርዳታ አደርጋለሁ ብዬ በራሴ ፈቃድ ከፓርቲ ፖለቲካ ወጥቻለሁ፡፡   አድርጌያለሁ፡፡ እግዚአብሄር ይመስገን ጤናማ ነኝ፡፡ በእድሜየ በኩል 83 አመቴ ነው፡፡ በትምህርትም ሆነ በተፈጥሮ ስጦታ ትልቅ አቅም ያላቸው ልጆች ስላሉ እኔ በዚህ እድሜዬ መድከም የለብኝም ብዬ ነው የለቀቅኩት፡፡

ነገረ ኢትዮጵያ፡- ስለዚህ አሁን የቱንም የፖለቲካ ድርጅት አይወክሉም ማለት ነው?
አቶ ቡልቻ፡- ልክ ነው! በግሌ ነው የምንቀሳቀሰው፡፡ አሁን ምንም አልወክልም፡፡ አስተያየትም የምሰጠው፣ ንግግርም የማደርገው በግሌ ነው፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ፡- መድረክ በቅርቡ አዲስ አበባ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ ባደረገበት ወቅት ንግግር ሲያደርጉ በቦታው ነበርኩ፡፡ ‹‹በጋራ መምጣት ከፈለግን አንድ መሆን አለብን›› የሚል ንግግር አድርገው ነበር፡፡ ምን ለማለት ፈልገው እንደሆነ ሊያብራሩልኝ ይችላሉ?
አቶ ቡልቻ፡- እኔ ማለት የፈለኩት፤ የኢትዮጵያ ብሄሮች (ብሄሮች አሉ፡፡ የሉም ማለት አይቻልም፡፡ ብሄሮች እንደለሉ መናገር ችግር የለውም የሚሉ ቢኖሩም ተሳስተዋል፡፡ እኛ አይደለም የምንፈጥራቸው፡፡ እነሱ አሉ፡፡) መኖራቸውን አውቆ ከእነሱ ወኪሎች ጋር መነጋገር ነው፡፡ ኢትዮጵያ መነጋገሯ
አይደለም፡፡ የብሄሮች ወኪሎች ተነጋገሩ ማለት ኢትዮጵያ ተነጋገረች ማለት ነው በውስጧ፡፡ የተለያዩ የፖለቲካ መስመር የሚከተሉ ሰዎች አሉ፡፡ ይህ ማለት የአንድ ማህበረሰብ ሰዎች አንድ አይነት ፖለቲካ ይከተሉ ማለት አይደለም፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ፡- በጎሳ ወይም በብሄር የተደራጁት አካላት ትክክል አይደሉም የሚሉ ሰዎች አሉ፤ ብሄር ማለት ሀገር ማለት ነውና ከቃሉ ጀምሮ ትክክል አይደለም ይላሉ፡፡ እርስዎ ምን ይላሉ…ለእርስዎ ብሄር ማን ነው? ብሄረሰብስ የትኞቹ ናቸው?
አቶ ቡልቻ፡- እኔ ‹‹ብሄር›› የሚባለውን ቃል የሰማሁት የ19ና 20 አመት ሆኜ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁት፡፡ አንድ አራት ኪሎ ይገኝ የነበር ተስፋ ገብረስላሴ የተባለ ሰው ማተሚያ ቤት ነበር፡፡ ያ ማተሚያ ቤት ‹‹ተስፋ ገብረስላሴ ዘ ብሄረ ቡልጋ›› ይል ነበር፡፡ ይህ ምን ማለት እንደሆነ ጠይቄ አሁን የምረዳውን ተረዳሁ፡፡ ብሄር ማለት አሁንም እንደምንሰማው የአንድ ብዙ ወይንም አነስ ያለ ህዝብ አንድነት፣ ወይንም ማንነት ማለት ነው፡፡ ምንም አያስቸግረኝም፣ አስቸግሮኝ አያውቅም፡፡ ብሄር ማለት የህዝብ መገለጫ ማለት ነው፡፡

ነገረ ኢትዮጵያ፡- ህዝብ የተለያየና አንጻራዊ መገለጫዎች ይኖሩታል፡፡ በዚህ መሰረት እንደ ኢትዮጵያ የጋራ መገለጫ አይኖረንም? ‹ብሄር› የሚባሉት ቡድኖች መገለጫቸው ድንበር ሲያጣ ይታያል፡፡ ስለዚህ በጋራ የምንጋራቸውን ማንነቶችስ ምን ልንላቸው ነው?
አቶ ቡልቻ፡- ኢትዮጵያ ብቻ አይደለችም በዓለም ላይ ብዙ ሀገራት አሉ፡፡ በተባበሩት መንግስታት ላይ ያየኸው እንደሆነ 198 ነው ሀገራት አሉ፡፡ ኢትዮጵያ ከእነዚህ ሀገራት አንዷ ናት፡፡ እኔ ከእነዚያ መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ ዜጋ ነኝ፡፡ ልክ አንድ ቤተሰብ ብዙ ሰው እንደሚኖረው እኛም ሀገራችን ውስጥ ስንገባ ብዙ አይነት ኢትዮጵያውያን አሉ፡፡

ነገረ ኢትዮጵያ፡- እገሌ ብሄር፣ እገሌ ደግሞ ብሄረሰብ ነው ብለው በምሳሌ ሊያስረዱኝ ይችላሉ?
አቶ ቡልቻ፡- እኔ እንደሚገባኝ ነው የምሰጥህ፡፡ ኦሮሞ ማለት ኦሮምኛ የሚናገር፣ በምስራቅ፣ መካከለኛውና ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚኖር፣ አብዛኛውን ጊዜ ግብርና መኖሪያቸው የሆነ መልካቸው (ከሌላው ኢትዮጵያውያን ይለያል አልልም) ጥቁርም አይደሉም፣ ቀይም አይደሉም፡፡ ብዙው የኢትዮጵያ ህዝብ እንደዚህ ነው፡፡ ኦሮሞ እንዲህ አይነት ህዝብ ነው፡፡ ውስጥ የገባህ እንደሆነ ስነ ልቦና፣ የጋራ አመለካከት የመሳሰሉ የእያንዳንዱ ሰው ፍርድ አለ፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ፡- አንዳንድ ፖለቲከኞች ‹‹ብሄር›› የሚባሉትን ጎሳ፣ እንዲሁም ድርጅቶችን ‹‹የጎሳ ድርጅት›› ይሏቸዋል፡፡ እርስዎ ይስማማሉ?
አቶ ቡልቻ፡- አልስማማም! ጎሳ ሌላ ነው፡፡ እኔ የአማርኛ ሊቅ ባልሆንም መናገር እችላለሁ፡፡ ጎሳ የሚባል ቃል፤ እኔ እንጃ?! ኦሮሞ ጎሳ ነው እንዴ? ኦሮሞ ጎሳ አይደለም! አንድ ህዝብ ነው፣ ጎሳ አይደለም፡፡ ምን አልባት የሚዛመዱትን ከሆነ ኦሮሞ ውስጥ ብዙ እርስ በእርሳቸው የሚዛመዱ አሉ፡፡ እኔ በተወለድኩበት ወለጋ ውስጥ በራሱ ብዙ ብዙ ጎሳዎች አሉ፡፡ ጎሳ እንኳ ብዙም ትርጉም የለውም፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ፡- እንደ ሩዋንዳ ያሉ ሀገራት አንድን ህዝብ ቋንቋን ወይም ጎሳን መሰረት አድርጎ በፖለቲካ ማደራጀት በህግ ከልክለዋል፡፡ በጎሳ መደራጀት በተለይ በፖለቲካ ፓርቲ ደረጃ ምን ያህል ያስኬዳል? ለሀገር አንድነትስ ተጽዕኖ አይኖረውም?
አቶ ቡልቻ፡- እኔ እንደሚመስለኝ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ዘጠና ሚሊዮን ህዝብ ነው የሚኖረው፡፡ እግዚአብሄር ይመስገን መታወቂያ ስለሰጠን እንጂ ካለዚያማ ማን ምን እንደሆነም አይታወቅም፡፡ አሁን ግን አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ.. በጣም ደስ የሚል መግለጫ፡፡ እሱማ ባይኖር ማን ነበር የምንባለው? የትግሬ ህዝብ በራሱ መሪዎቹን መርጦ ወደ ዋናው ከተማ ይመጣል፡፡ ኦሮሞ በራሱ ክልል የራሱን መሪዎች መርጦ ወደ አዲስ አበባ ይመጣል፡፡ እነዚህ መሪዎች ኢትዮጵያን እንዴት እንምራት ብለው ሊስማሙ ይችላሉ፡፡ ሊነጋገሩ ይችላሉ፡፡ አንድ ህዝብ በስሙ መጠራቱ ምን ከፋ? ችግሩ እኛ ኢትዮጵያውያን አይደለንም ሲባል ነው፡፡ ህወሓት፣ ኦነግና አሁን ኢህአዴግ ውስጥ ያለው የአማራ ድርጅት ኢትዮጵያዊ አይደለንም ይሉ ነበር፡፡ ችግሩ የሚመጣው እንዲህ ሲሆን ነው፡፡ ይህ ሳይሆን በስሙ ተጠርቶ፣ ከሌሎች የኢትዮጵያ ዜጎች ጋር ተዋዶና ተፋቅሮ፣ እየተረዳዳ፣ እየሰራ ቢኖር ምን
ችግር አለው?
ነገረ ኢትዮጵያ፡- እርስዎ በፓርቲ ደረጃና በግል እንደሚታገሉለት የሚናገሩለት የኦሮሞ ህዝብ ሰፊ መሰረት ያለው መሆኑ ይታወቃል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ሰፊ መሰረት ያለው ሆኖ እያለ በቋንቋ በመደራጀት መብቱን አስከብራለሁ ማለት ለክብሩ የሚመጥን አይደለም የሚሉ አካላት አሉ፡፡ የኦሮሞ ህዝብ በቋንቋ ከመደራጀት ይልቅ በህብረ ብሄራዊነት ተደራጅቶ በኢትዮጵያ የተሻለ ለውጥ ማምጣት አይችልም? በአንድ ክልል፣ በአንድ ማዕቀፍ ብቻ ተወስኖ መደራጀት ለክብሩ የሚመጥን ነው ብለው ያስባሉ?
አቶ ቡልቻ፡- የኦሮሞ ህዝብ ከ37 እስከ 40 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ ነው፡፡ ግን አዋቂዎችና የተማሩት የሚሉትን ልንገርህ፡፡ እኛ የኢትዮጵያ አካል ነን፡፡ የትም መሄድ አንፈልግም፡፡ ኦሮምኛ እንናገራለን፡፡ ግን ኢትዮጵያውያኖች ነን፡፡ በኢትዮጵያዊነት ማንም ከእኛ አይበልጥም፡፡ እኩል ነን፡፡ እገዛችኋለሁ፣ እበልጣችኋለሁ፣ ቋንቋችሁን አፍናለሁ፣ የሚሉ ካሉ እንታገላቸዋለን፡፡ እንጂ የትም አንሄድም፡፡ አገራችንን ትተን የት እንሄዳለን? ዛፍ እንኳ ስታየው ቅርንጫፉ ነው የሚወድቀው፡፡ ዋናው ግንድ ይቆማል፡፡ ኦሮሞ ግንድ ነው፡፡ ማንም ሰው ለኦሮሞ አንተ እንዲህ ነህ፣ አንተ እንዲህ ነህ ብሎ ሊነግረው አይችልም፡፡ ኦሮሞ ምን እንደሆነ ራሱን ያውቃል፡፡ እንዲያውም ኦሮሞ ይህ ሀገር የእኔ ነው፣ ከሌሎች ጋር ተጋርቼ እኖራለሁ ብሎ ነው የሚያምነው፡፡ ስለዚህ ነው እንገነጠላለን የሚሉ ሰዎች ያልተሳካላቸው፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ፡- ታዲያ ኦሮሞ ግንድ ሆኖ እያለ እንደ ቅርንጫፍ ነጥሎና ጠበብ አድርጎ መደራጀት ለምን አስፈለገ?
አቶ ቡልቻ፡- ኦሮሞዎች፣ እኛ ኦርጅናል ኢትዮጵያውያን ነን፡፡ ኢትዮጵያውያን ሆነን ግን ለፖለቲካና ማህበራዊ ህይወት እንደራጃለን፡፡ ቋንቋችን ስንናገር ነው የምንግባባው፡፡ አማርኛም እንናገራለን፣ ነገር ግን አማርኛም የማያውቅ አለ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ለምን ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ አማራ፣ ጉራጌ ተብሎ ይጠራል
ብለው የሚከራከሩት አብዛኛውን ጊዜ የቀድሞ የሹማምንት ልጆች ናቸው፡፡ የግራአዝማቹ፣ የቀኝአዝማቹ፣ የራሱ የቀኝአዝማቹ ዝምድና ያላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ እነሱ የሚመኙት ወደ ድሮው፣ ወደመሪነት፣ ወደማዘዝ ቦታ ነው የሚመኙት፡፡ የፌደራል ጉዳይ ደግሞ ይነሳል፡፡ ለምንድን ነው ሁላችንም አንድ አዳራሽ ውስጥ የማንኖረው? ለምንድን ነው እያንዳንዱ ሰው ከሌላው ተወዳድሮ ቆንጆ ቤት ሰርቶ ለብቻው የሚኖረው? ፌደሬሽን የሚጠሉ ሰዎች ምንድን ነው የሚፈልጉት? በ1983 ዓ.ም ፌደራሊዝም ከመገንጠል ይሻላል ተብሎ እኮ ነው የመረጥነው፡፡ ያኔ ሁሉም፤ ኦነግም፣ ህወሓትም፣ አማራም፣ ሲዳማም… ሁሉም ብሄር ፌደራሊዝምን የመረጥነው እንገነጠላለን የሚሉትን ሰዎች ለማሸነፍ ነው፡፡ እኔ ኢትዮጵያ ከፌደራሊዝም ውጭ ተስፋ አላት ብዬ አላምንም፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ፡- አሁንም ቢሆን ከፌደራሊዝም ውጭ አማራጭ ይዞ የመጣ የፖለቲካ ፓርቲ ያለ አይመስለኝም፡፡ ልዩነቱ በቋንቋ/ጎሳ/ብሄር ከሚሆን ይልቅ አስተዳደራዊ አመችነትና ሌሎች መስፈርቶች መታየት አለባቸው የሚል ነው፡፡ እርስዎ አሁን እንደሚናገሩት ግን ኢህአዴግ የሚጠቀምበት ቋንቋን መሰረት ያደረገ አወቃቀር እንዲቀጥል የፈለጉ ይመስለኛል?
አቶ ቡልቻ፡- አዎ! አማራጭም የለውም፡፡ ታዲያ በምን የተመሰረተ ድርጅት ሊሆን ነው? በቋንቋው፣ በባህሉ፣ በሚኖርበት አካባቢ የፖለቲካ ድርጅት ቢያቋቁም ምን ይጎዳል? ለምንድን ነው የሚጠላው? አሁን እነሱ የሚሉት በዘር ሳይሆን በወንዝ፣ በተራራ፣ አንዳንድ ዳርቻዎችን በመጥቀስ ነው፡፡ ለምሳሌ በአጼ ኃይለስላሴ ጊዜ ሸዋ አማራም፣ ኦሮሞም ነበረበት፡፡ በዛን ጊዜ ሀገረ ገዥው ራስ መስፍን ነበሩ፡፡ እኔ አውቃቸዋለሁ፡፡ በጣም ጥሩ ሰው ነበሩ፡፡ በጣም ትሁት፣ ሩህሩህና ፍትህ የሚያውቁ ሰው ነበሩ፡፡ እሳቸው አማራ ነበሩ፡፡ ኦሮሞዎቹ እንደልባቸው ራስ መስፍን ጋር አይመሩም፣ ራስ መስፍንን አያማክሩም፡፡ አማራ የሆኑት የሸዋ ሰዎች ግን ራስ መስፍንን እንደራሳቸው መሪ፣ እንደራሳቸው ሀገረ ገዥ፣ እንደራሳቸው እንደራሴ አድርገው ነበር የሚያዩት፡፡ ይህ ራሴ በህይወቴ ያየሁት ገጠመኝ ነው፡፡ ህዝብ የሚፈልገውን ያውቃል፡፡ ከፌደራሊዝም ውጭ አማራጭ የለንም፡፡ ፌደራሊዝምን በደንብ መምራት የመንግስት ፋንታ ነው፡፡ ፌደራሊዝም በሚመራበት ወቅት የኦሮሞ ህዝብ ‹ራስ መስፍን የእኛ አይደሉም› እንዳሉት እንዳይሆን መደረግ አለበት፡፡ የአዲስ አበባ መንግስት ሁሉንም ሰው በእኩልነትና በፍርድ የያዘ እንደሆነ ፌደራሊዝም ጥሩ አማራጭ ይሆናል፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ፡- ፌደራሊዝሙ በቋንቋ መዋቀሩ እንደ ችግር ተብሎ የሚነሳው ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ‹‹ሀገራችሁ አይደለም ውጡ›› እንደሚባሉ በመጥቀስ ነው፡፡ በደቡብና ቤንሻንጉል እየታየ ያለውንም እንደማሳያ ይጠቅሳሉ፤ እና…
አቶ ቡልቻ፡- እሱን በጭራሽ አልደግፍም፡፡ እሱን በመመካከር፣ በአስተዳደር፣ በፖለቲካ፣ አንድም ነገር ሳይደበቅ መነጋገርና መወያየት ያስፈልጋል፡፡ ግልጹን ማውጣት ነው የሚጠቅመው፡፡ ለምሳሌ ከወለጋ አማራዎችን አንስተዋቸዋል ይባላል፡፡ ውሸት መሆኑን አውቃለሁ፡፡ ግድ የለም አስነሷቸው እንበል፡፡ ታዲያ ለምንድን ነው የምታስነሷቸው ብሎ መጠየቅ ነው? ኢትዮጵያውያን የትም ሄደው መስራትና መኖር አለባቸው፡፡ በመሆኑም ማፈናቀል ካለ ለወደፊት ወንጀል ተደርጎ መወሰድ አለበት፡፡ አንድ ብሄር ሌላኛውን ይህ ያንተ አይደለም፤ ከሌላ ነው የመጣኸው ብሎ ሲያፈናቅል የሚቀጣበትን አግባብ መፈለግ ነው ያለብን፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ፡- በአንቦና በሌሎች አካባቢዎች ግጭት ለመነሳቱ ቀዳሚው ምክንያት የኦሮሚያ መሬት ሊወስድ ነው፣ አርሶ አደሮች ሊፈናቀሉ ነው በሚል ነበር ይታወል፡፡ በአንድ በኩል አዲስ አበባ የኦሮሞ ነች እየተባለ በሌላ መልኩ ደግሞ የኦሮምያ መሬት ለአዲስ አበባ ሊሰጥ ነው ማለት እርስ በእርሱ አይጋጭም?
አቶ ቡልቻ፡- እንደ እኔ ይህንን ጣጣ ያመጡት በፌደራል መንግስቱ ውስጥ የሚሰሩ አንዳንድ ባለስልጣናት ናቸው፡፡ እርግጥ ነው ኦሮሞ መሬቱ በአዲስ አበባ እንዲወሰድ አይፈለግም፡፡ ምክንያቱም የጋራ ጥቅም ነው፡፡ አሜሪካም ውስጥ እንዲህ አይነት ጭቅጭቅ አለ፡፡ ትልልቅ የመንግስት ስራዎች ሲሰሩ አንዱ ስቴት ይመረጣል፡፡ ለመንግስት ስራ የተመረጠው ስቴት የስራ አጥነትና ሌሎች ችግሮች እንደሚፈጠሩ በመግለጽ ይከራከራሉ፡፡ ታዲያ ምን አለ የኦሮሞ ወጣቶች እኛ ሳንጠየቅ ይህን ያህል መሬት ለምን ይወሰድብናል? ቢሉ ምን ችግር አለው፡፡ አሜሪካ ዋና ከተማው ዋሽንግተን ዲሲ ነው፡፡ ዋሽንግተን የቨርጂኒያና የሜሪላንድን መሬት ዝም ብሎ ይከልላል? የማይታሰብና የማይደረግ ነገር ነው፡፡ ለማንም ሳይናገሩ ልዩ ዞኖችን እንደወሰዱት አይደለም፡፡ ይህ እኮ ሰውን መናቅ ነው፡፡ ከህዝቡ ጋር ተማክረዋል? መንግስት የህዝብ ወኪል ከሆነ ህዝብን መናቅ አይችልም፡፡ በሰለጠነ መንገድ ቢደረግ ኖሮ ማን ይቃወም ነበር?
ነገረ ኢትዮጵያ፡- በቅርቡ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ አይገባኝም!›› ማለትዎትን አንብቤያለሁ፡፡ ሰማያዊ አይገባኝም ሲሉ ምን ማለትዎት ነው?
አቶ ቡልቻ፡- አንድነትን አውቀዋለሁ፡፡ መኢአድን አውቀዋለሁ፡፡ ሰማያዊን ግን አላውቀው ማለቴ ነው፡፡ ይህ ግልጽ ነው አላውቃቸውም ማለት ነው፡፡ እነሱም አላማቸውን ለማሳወቅ ፓምፕሌት አይበትኑም፡፡ እኔ ለምሳሌ ኦፌኮ በነበርኩበት ጊዜ ስለ አላማችን በርካታ ፓምፕሌቶችን እያሳተምኩ እበትን ነበር፡፡ ህዝብ አላማችን እንዲያውቅ እናደርግ ነበር፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ይህንን ሲያደርግ አላየሁም፡፡ እና ሰማያዊ ከአንድነት ምን ያህል ልዩነት ኖሮት ነው ሰላማዊ ሰልፍ የተፈቀደለትና አንድነት ሰላማዊ ሰልፍ የተከለከለው? አይገባንም፡፡ እውነቴን ነው ፖለቲካም እውነት ሊሆን ይችላል አንዳንዴ፡፡ ይህን አላውቅም የምለው ከልቤ ነው፡፡ አንድነት ከኦሮሞ የሚለይበትን አንዳንድ ምክንያቶች አውቃለሁ፡፡ ይህ ከቅን ልቦና የማደርገው ንግግር ነው፡፡ ቢፈልጉ ፓምፕሌት ይላኩልኝ አንብቤ እረዳዋለሁ፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ፡- እርስዎስ በግልዎ ለማወቅ ጥረዋል?
አቶ ቡልቻ፡- አዎ! ጠየኩ! ቢሮ ውስጥ እባካችሁ የሰማያዊ ፓርቲ ፓምፕሌት፣ መግለጫ ካላችሁ ብዬ ጠይቄያለሁ፡፡ አሁንም እጠይቃለሁ፡፡ ለምሳሌ ከአንድነት ልዩነታቸው ምንድን ነው? አንድነት አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግራይ ሳይሆን ኢትዮጵያ መባል እንዳለበት እንደሚፈልጉ አውቃለሁ፡፡ የሰማያዊ ምን እንደሆነ አላውቅም፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ፡- ሰማያዊ አቋሞቹን፣ መግለጫዎቹንና ሌሎቹንም በዚህ ጋዜጣ ያሳውቃል፡፡ ለምሳሌ ነገረ ኢትዮጵያን አንብበው ያውቃሉ?
አቶ ቡልቻ፡- እስካሁን አላየሁም፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ፡- ለ2007 ሀገራዊ ምርጫ እየተቃረብን ነውና ከምርጫው ምን ይጠብቃሉ?
አቶ ቡልቻ፡- በአሁኑ ጊዜ የህዝቡን የኢኮኖሚ ችግር፣ የኑሮ ውድነት፣ የስራ አጥነት፣ በተለይም የምግብ ዋጋ መናር አለ፡፡ ይህን ሁሉ ህዝቡ ያውቃል፡፡ ታዲያ ህዝቡ ይህን እያወቀ ኢህአዴግን እንመርጣለን ይላል? እንግዲህ እያንዳንዱ ሰው መፍረድ አለበት፡፡ ይህ ሁሉ ችግር እያለ በማን አገር ነው አንድ ፓርቲ 20ና 30 አመት ስልጣን ላይ የሚቆየው? ቻይና ብቻ ነው አይደለም?! እንደ ቻይና ኮሚኒስት እንሁን ብሎ የኢትዮጵያ ፓርላማ ፈቅዷል? ያለ ፓርላማ ፈቃድ የኢትዮጵያ መንግስት እንደፈለገ የሚንቀሳቀስ፣ የፈለገውን ገንዘብ የሚያወጣ፣ የፈለገውን የሚገዛ፣ የፈለገውን የሚሸጥ፣ ዴሞክራሲ እንደሌለ አድረጎ ነው የሚያስተዳድረው፡፡ እንደ ፖለቲከኛ ሳይሆን እንደ ዜጋ ሳየው ተቃዋሚዎች በሚቀጥለው ምርጫ ትልቅ እድል አላቸው፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ፡- እርስዎ የሚገልጹት ብሶት መኖሩን ነው፡፡ ግን ተቃዋሚዎች የሚሉትን እድል ለመጠቀም የቤት ስራቸውን እየሰሩ ነው ብለው ያምናሉ?
አቶ ቡልቻ፡- ተቃዋሚዎች የማይፈታ ችግር አለባቸው፡፡ አሁን በቀደም በጋዜጣ ላይ ሳነብ ኢህአዴግ በደግነቱ ለተቃዋሚዎች ገንዘብ ሰጠ የሚል አይቼ በጣም ተደነኩ፡፡ ጋዜጣው ላይ ቃል በቃል ‹‹ለግሷል!›› ይላል፡፡ ይህ እኮ ድንቁርና ወይንም ክፋት ነው፡፡ በየትኛውም ሀገር ምርጫ ሲደርስ መንግስት ለተቃዋሚዎች ገንዘብ መስጠት ግዴታው ነው፡፡ ዋናው የመንግስት ስራ እኮ ነው፡፡ በጀት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ካለ በጀት ምንም ነገር አይሰሩም፡፡ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች አንድ ቦታ ላይ ለመድረስ የኢትዮጵያ በጀት እንዲደርሳቸው ያስፈልጋል፡፡ ይህ ደግነት አይደለም፡፡ የማንም ሀገር ተቃዋሚ በመንግስት በጀት ይንቀሳቀሳል፡፡ ተቃዋሚ አስተያየቱን በግልጽ በጋዜጣ፣ በቴሊቪዥንና በመሳሰሉት ካልገለጸ ማን ይመርጠዋል? እሱ እኮ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ የተዘጋው በር፡፡ በሩ ከተዘጋ ተቃዋሚዎች እንዴት ይንቀሳቀሳሉ? በሬድዮና ቴሌቪዥን አትናገሩ ከተባለ፣ ሰላማዊ ሰልፍን ለህዝብ በቴሌቪዥን እንዳይታይ ከተደረገ ተቃዋሚዎች እንዴት ይንቀሳቀሳሉ? እንደዛም ሆኖ ግን ተቃዋሚዎች አሁንም ትልቅ እድል አላቸው ባይ ነኝ፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ፡- በመጨረሻ መናገር እፈልጋለሁ የሚሉት መልዕክት ካለ?
አቶ ቡልቻ፡- እንዴት የኢትዮጵያ ህዝብ ዝም ብሎ አንድ ጥያቄ ሳይጠይቅ ይኖራል? ተቃዋሚዎችን በራዲዮና በቴሌቪዥን ያሰሙን ብሎ በሰልፍ አይጠይቅም? እንደዚሁም ደግሞ መንግስት መረጃ አልሰጥም እያለ ሲያስቸግር ህዝቡ አይጠይቅም? የመንግስትን ንብረት አጠቃለሁ፣ የሚገዙበት፣ የሚዙት የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ብቻ ናቸው፡፡ የመንግስት ኩባንያዎች ሁሉ በኢህአዴግ ስር ነው የሚተዳደሩት፡፡ ድሮ በአጼ ኃይለስላሴ ጊዜ እንደዚህ ነበር፡፡ ነገር ግን በእርሳቸው ጊዜ እንደዛ የሆነው የግል ባለሀብት ስለጠፋ ነው፡፡ ዛሬ የግል ባለሀብት እንደ ልብ ነው፡፡ ለምንድን ነው የኢትዮጵያ መንግስት ይህን ሁሉ ንብረት የሚቆጣጠረው? የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ቴሌ፣ አየር መንገድን ሁሉ ለምንድን ነው በስሩ ያደረገው? እኛ ኮሚኒስት ነን እንዴ? ፓርላማ ኢትዮጵያ ኮሚኒስት ነች ብሏል፡፡ ይህ የኢህአዴግ የራሱና የውስጥ አሰራር ነው፡፡ ይህን ለህዝብ መናገር እፈልጋለሁ፡፡
ምንጭ፡ ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ከአዲስ አበባ
 

 

Friday, July 25, 2014

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የአየር ሃይል ግቢ ውስጥበአንድ አነስተኛ ክፍል ውስጥ ታስረው ...........



ሐምሌ ፲፰ (አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከሰኔ 18 ቀን 2006 ዓም ጀምሮ ደብረዘይት በሚገኘው የአየር ሃይል ግቢ ውስጥበአንድ አነስተኛ ክፍል ውስጥ ታስረው ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
ኢሳት የተለያዩ ምንጮችን አነጋግሮ ባሰባሰበው መረጃ አቶ አንዳርጋቸው በመጀመሪያዎቹ 10 ቀናት ከፍተኛ ድብደባ ከተፈጸመባቸው በሁዋላ ድበደባው ቆሞ፣ የማሰቃያ መርፌዎችን እየተወጉና በኤልክትሪክ ሾክ እየተሰቃዩ መረጃ እንዲያወጡ እየተገደዱ ነው።
መርማሪዎች ከአቶ አንዳርጋቸው የሚፈልጉት መረጃ ከግንቦት7 ጋር በጋራ የሚሰሩ አሁን በስልጣን ላይ ያሉ የኢህአዴግን አመራሮችን እንዲሁም በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ያሉ አዛዦችን ስሞች ሲሆን፣ አቶ አንዳርጋቸው ግን እስካሁን ምንም አይነት መረጃ ባለመስጠታቸው ፣ መርማሪዎች ሲበሳጩ መታየታቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ለወትሮው አንድ መረጃ ሲያገኙ በታላቅ ደስታ የሚፈነጩት መርማሪዎች፣ ምርመራቸውን ጨርሰው ሲወጡ የሚያሳዩት ብስጭት፣ እስካሁን ድረስ የሚፈልጉትን እንዳላገኙ የሚያሳይ መሆኑን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ምንጮች ገልጸዋል።

Thursday, July 24, 2014

ትሩዝ ፋክት ስለ ኮ/ል መንግስቱ ሃይለማርያም

ኮ/ል መንግስቱ ሃይለማርያም የሰዎችን ህይወት እንዲጠፋ በማድረግ ከቀዳሚዎቹ አስር የሀገራት መሪዎች ውስጥ አንዱ ናቸው ተባለ
ትሩዝ ኮድ የተሰኘ ድረገጽ ሪፖርት በአለማችን በርከታ ሰዎችን በማስገደል ቀዳሚ የሆኑ 10 የሀገራት መሪዎችን ይፋ አድርጓል፡፡
በርካታ ዜጎቻቸውን በመግደል በቀዳሚነት የተቀመጡት የቻይናው ማኦ ሴዱንግ ሲሆኑ ከኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር ጋር የሚቀራረብ መጠን ያለው ህዝብ አስጨርሰዋል ይላል ሪፖርቱ 78 ሚሊዮን ሰዎችን በማስገደላቸው፡፡
ሁለተኛ የሶቤት ህብረቱ ጆሴፍ ስታሊን 23 ሚሊዮን ሰዎችን በማስገደል ደረጃውን ሲይዙ በሶስተኝነት የሚከተለው የጀርመኑ አዶልፍ ሂትለር ነው የ17 ሚሊዮን ሰዎችን ህይወት እዲጠፋ በማድረግ፡፡
ሪፖርቱ የሰዎችን ሂወት በማጥፋት ከዘረዘራቸው ሀገራት መሪዎች ውስጥ ኮ/ል መንግስቱ ሃይለማርያምም ለ1.5 ሚሊዮን ህዝብ ማለቅ ምክንያተ ናቸው በሚል የዘጠነኛነትን ቦታ ይዘዋል፡፡
ምንጭ ድሬ ትዩብ

Monday, July 21, 2014

ሰሜን ሸዋ የመርሃቤቴ ወረዳ ህዝብ ከወያኔ የፀጥታ ሃይሎችና ፌደራል ጋር ከባድ ውጊያ እያካሄደ ነው

 

ውጥረት በሰሜን ሸዋ መርሃቤቴ በርትቷል

ደብረብርሃን አከባቢ መግቢያና መውጪያ መንገዶች ተዘግተዋል።
ለወረዳው አለም ከተማና አካባቢዋ አገልግሎት ይውላል ተብሎ ከብዙ ጊዜ በሁአላ የገባውን መብራት የወያኔ መንግስት ህዝቡ የሚገለገልበትን መብራት አቁሞ ትራንስፎርሜሽኖቹን ነቅሎ ለአስቸኩአይ ጉዳይ ይፈለጋል ብሎ ወደ ትግራይ ለመውሰድ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የወረዳው 27ቱም ቀበሌ ተጠራርቶ ትራንፈርመሩን በቁጥጥር ስር በማድረግ ከላይ ከተጠቀሱት የወያኔ የፀጥታ ሃይሎች ጋር ኣሁን ድረስ ውጊኣ እያደረገ ሲሆን እስካሁን 7 የወያኔ ወታደሮች የሞቱ ሲሆን ከህዝብ ታጣቂ በኩል 1 ሞቷል። ባሁኑ ሰዓት ወረዳውን መሉ በሙሉ የህዝቡ ታጣቂ ተቆጣጥሮት ይገኛል። ወያኔ ከአዲስ አበባና ከተለያዩ አካባቢወች ተጨማሪ ሃይል ወደ አካባቢው እያንቀሳቀሰ መሆኑ ታውቁኣል።ሁኔታው የሚመለከታችሁ ወገኖች ሁሉ እየሆነ ያለውን ሁሉ በመከታተልና አስፈላጊውን ድጋፍ እንድታደርጉ ያስፈልጋል።
ቁስለኞች ሆስፒታሉን አጣብውታል ። ቁስለኞቹ የሚታከሙት በፖሊስ ታጅበው ሲሆን ህክምናውን እንደጨረሱ ውእደ እስርቤት ይወሰዳሉ ።ከቦታው የሚደርሱ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት እስከመቼ ተታለን እንኖራለን የሚሉ የሰሜን ሸዋ ነዋሪዎች ዱር ቤቴ ብለው ሸፍተዋል። ከዚህ በታች የምትመለከቱት ከአከባቤው ከሚገኘው ሆስፒታል የተላከ ምስል ነው።

source zehabesh

Sunday, July 20, 2014

የሰማያዊ ፓርቲዋ ወጣት ወይንሸት ሞላ ተፈንክታ፣ እጆቿ በፋሻ ጠቅልሎ፣ ሰውነቷ ዝሎ ፍርድ ቤት ቀረበች

  • 1781
    Share
(ፎቶው የተገኘው ከሰማያዊ ፓርቲ ነው)
(ዘ-ሐበሻ) በትናንትናው እለት የአንዋር መስጊድ አካባቢ የሕወሓት አስተዳደር በንጹሃን የእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ አሰቃቂ እርምጃ እየወሰደ በሚገኝበት ወቅት መርካቶ አካባቢ ለሥራ ጉዳይ ሄዳ የነበረችው የሰማያዊ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤትና የሴቶች ጉዳይ አባል ወጣት ወይንሸት ሞላ በደህነንቶች ታፍና ከተወሰደች በኋላ ከፍተኛ ድብደባ ሲፈጸምባት ቆይቶ በዝግ ችሎት ቀርባ 14 ቀን የምርመራ ቀጠሮ ተጠየቀባት።
(ፎቶው የተገኘው ከሰማያዊ ፓርቲ ነው)

















የነፃ አሳቢ ዜጎች መሰቃያ በሆነውና ከማዕከላዊ አጠገብ በሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እስር ቤት ውስጥ የምትገኘው ወጣት ወይንሸት ማንም ሰው እንዳይጠይቃት በፖሊሶቹ መከለከሉ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

ዛሬ ረፋዱ ላይ ሜክሲኮ አካባቢ ያለ ፍርድ ቤት የቀረብቸው ወጣት ወይንሸት ምንም እንኳ ችሎቱ በዝግ ቢደረግም ጭንቅላቷ ተፈንክቶ፣ ቀኝ እጇ በፋሻ ተጠቅልሎና አንገቷ ታስሮ የተመለከቷት ሲሆን የህግ አማካሪ እንዳታገኝም ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ መከልከሉን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አረጋግጠዋል።
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/32704

Saturday, July 19, 2014

አንዋር መስጊድ እና አካባቢው ላይ ውጥረት ነግሷል


ከጁመአ ሰላት ጋር በተያያዘ የተቃውሞ መርሃ ግብር ነበር በስፍራው የተለያዩ በራሪ ወረቀቶች እና መፈክሮች ነበሩ ::
ከነዚህ መካከል <<የታሰሩት ይፈቱ>> ፣ <<ድምፃችን ይሰማ >>፣ <<የሃይማኖት ነፃነትን ማክበር ግዴታ እንጂ መብት አይደለም >> የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮችም ነበሩ ፡፡
የጁመአ ሰላት ሁለት ረከአ (ሁለት ጊዜ) የሚሰገድ ሰላት ነው ፡፡ ነገር ግን ብትላንትናው እለት ተሰግዶ ሳይገባደድ ማለትም አንደኛው ረከአ ላይ ብጥብጥ ሊፈጠር ችሏል፡፡
 ውጥረቱ ቀጥሏል በስፍራው ከነበሩ እማኞች መረዳት የሚቻለውም በተደጋጋሚ የቶክስ ድምፅ ተሰምቷል ፡፡
በወርሃ ረመዳን ላይ ይገኛል የሙስሊሙ ማህበረሰብ (በእስልምና እምነት ውስጥ ትልቁ የጾም ወር ነው) እንዲህ አይነት ነገር ሲከሰት ለመጀመሪያ ጊዜ አልነበረም የዛሬ ሁለት አመት 2004 ክረምት ላይ በዚሁ የፆም ወቅት ተመሳሳይ ነገር ተፈጥሮ ነበር ፡፡
ባለፈው አመት ደግሞ በኢድ አልፈጥር በአል ቀን ከስግደት መልስ የተፈጠሩ ነገሮች እንደነበሩ ይታወሳል፡፡
በትላንትናው እለትም ጉዳት የደረሰባቸው የፖሊስ አአባላት እና እንዲሁም ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ በርከት ያሉ የእምነቱ ተከታዮች የደረሰባቸውን ጉዳት በአካባቢው ወደሚገኙ መካከለኛ ክሊኒኮች እና ሆስፒታሎች እርዳታ እንደተደረገላቸው ነው።
 

Wednesday, July 16, 2014

ጋዜጠኞቹና ጦማሪያኑ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ የምርመራ መዝገቡ መዘጋቱ ሕገወጥ አካሄድ መሆኑ ተገለጸ

June16/2014


‹አሁን ታስረው የሚገኙበት ሁኔታ ሕገወጥና አደገኛ ነው›› የተጠርጣሪዎች ጠበቃ
zone 9999በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው በክስ ላይ የሚገኙት ሦስት ጋዜጠኞችና ስድስት ጦማርያን ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ፖሊስ ‹‹ምርመራዬን ስለጨረስኩ መዝገቡ ይዘጋልኝ›› በማለት መዝገቡ እንዲዘጋ ማድረጉ ሕጉን ያልተከተለና አደገኛ መሆኑን ጠበቃቸው አስታወቁ፡፡
ተጠርጣሪ ጋዜጠኞች ተስፋለም ወልደየስ፣ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ኤዶም ካሳዬና ጦማሪያንና የሕግ መምህር ዘለዓለም ክብረት፣ ናትናኤል ፈለቀና አጥናፉ ብርሃኔ ሐምሌ 5 ቀን 2006 ዓ.ም. በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የሚቀርቡበት ዕለት ነበር፡፡ እንደወትሮው ሁሉ የተጠርጣሪዎች ቤተሰቦች፣ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ጋዜጠኞች፣ ጓደኞቻቸውና የተለያዩ የችሎት ታዳሚዎች በጠዋት ማልደው በፍርድ ቤት ግቢ የተገኙ ቢሆንም፣ እስከ ቀኑ 5፡30 ሰዓት ድረስ ፖሊስም ሆነ ተጠርጣሪዎቹ ወደ ችሎቱ አልመጡም፡፡ ከ5፡30 ሰዓት በኋላ ሌሎች ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ተጠርጣሪዎቹና ፖሊስ ችሎት ቆይተው ሲወጡ፣ የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ አቶ አመሐ መኮንን፣ ደንበኞቻቸው ፍርድ ቤት መቅረብ አለመቅረባቸውን ለማጣራት የዕለቱን ተረኛ ዳኛ ለማነጋገር ገቡ፡፡ ጠበቃው ስለደንበኞቻቸው ፍርድ ቤቱን ሲጠይቁ፣ ፖሊስ ምርመራውን መጨረሱን በማሳወቅ መዝገቡ እንዲዘጋለት ጠይቆ መዘጋቱን ሲያስረዳቸው፣ ‹‹እንዴትና በምን ሁኔታ?›› የሚል ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ ከመዘጋቱ ውጪ ምንም ምላሽ ሊያገኙ አለመቻላቸውን ተናግረዋል፡፡
እስረኛ ፍርድ ቤት ሳይቀርብ የምርመራ መዝገቡ ሊዘጋ እንደማይችል የሚናገሩት ጠበቃ አመሐ፣ ተጠርጣሪዎቹ ከሐምሌ 5 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ በእስር ላይ መሆናቸው፣ በሕግ አግባብ በፍርድ ቤት ምንም ትዕዛዝ ባልተሰጠበት ሁኔታ በመሆኑ ድርጊቱ ሕገወጥና አደገኛ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
ፖሊስ ምርመራውን ካጠናቀቀ ተጠርጣሪዎቹን ፍርድ ቤት ይዞ በመቅረብ ለፍርድ ቤቱ ማስረዳትና ክስ እስከሚመሠረትባቸው ድረስ በዋስ እንዲቆዩ ወይም የሕግ ሥርዓቱ በሚፈቅደው መሠረት ስለሚቆዩበት ሁኔታ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መስጠት እንደነበረበት አስረድተዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ባልሰጠበት ሁኔታ ተጠርጣሪዎቹ ባሁኑ ወቅት የት እንዳሉ እንደማይታወቅ የሚናገሩት ጠበቃው፣ በወንጀል ሕጉና በሕገ መንግሥቱ በተጠሰው አካልን ነፃ የማውጣት መብት (ሐቢየስ ኮርፐስ) ክስ ሊመሠርቱ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡
በሌላ የምርመራ መዝገብ የተካተቱት ጦማሪያን ማህሌት ፋንታሁን፣ አቤል ዋበላና በፈቃዱ ኃይሉ ደግሞ ፍርድ ቤት መቅረብ የነበረባቸው ሐምሌ 7 ቀን 2006 ዓ.ም. የነበረ ቢሆንም፣ ተጠርጣሪዎቹም ሆኑ መርማሪ ፖሊስ ሳይቀርቡ መቅረታቸውን ጠበቃው ጠቁመዋል፡፡
ዘጠኙም ተጠርጣሪዎች ‹‹የመብት ተሟጋች ነን›› ከሚሉ የውጭ ኃይሎች ጋር በሙሉ ሐሳብና ገንዘብ በመስማማት ሕዝብን የማተራመስ፣ አገርንና መንግሥትን የማፍረስ ዘገባ በኢንተርኔትና በተለያዩ ድረ ገጾች ያልሆነ መረጃ ሲያስተላልፉ ተገኝተዋል በሚል ፖሊስ ሚያዝያ 17 እና 18 ቀን 2006 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር እንዳዋላቸው መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ለሁለት ጊዜ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጠይቆ ከተፈቀደለት በኋላ፣ በሦስተኛው የፍርድ ቤት ቀጠሮ የተጠርጣሪዎቹ ጉዳይ ውስብስብና ድርጊቱም የሽብርተኝነት ድርጊት መሆኑን በመጥቀስ፣ ለተጨማሪ ምርመራ 28 ቀን እንዲፈቀድለት የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉን በመጥቀስ ተፈቅዶለት መመርመር ላይ መሆኑን መዘገባችን አይዘነጋም፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ 78 ቀናት ሞልቷቸዋል፡፡
 
 

Monday, July 14, 2014

በኖርዌ የምንኖር ኢትዮጵያውያኖች በእልህና በቁጣ የተሞላ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ አደረግን ።

ሰኞ ጁላይ 14, 2014 / ሓምሌ 7 ,2006

      የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ አዘጋጅነት በኖርዌ ኦስሎ በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ቁጥራቸው በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያኖች በአንድ ላይ በመሰብሰብ ከቀኑ 13፡00 ጀምሮ በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ በየመን የፀጥታ ኃይሎች ታፍነው በአምባገነኑ ወያኔ እስር ቤት መታሰራቸውን በመቃወም እና በተጨማሪም አቶ ኦኬሎ አኳይ የኖርዌይ ዜግነት ያላቸውና በኖርዌ ሃገር ይኖሩ የነበሩ የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዘዳንት ከሱዳን በወያኔ የደህንነት ኃይሎች በግፍ ታፍነው መወሰዳቸውንና በወያኔ እስርቤት ታስረው ለሞት ፍርድ መዳረጋቸውን በመቃወም ድምጻችንን  ስናሰማ  ዋልን።

እኛ መነሻቸውን በኖርዌጅያን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ያደረግን ሲሆን በዛው በኖርዌጅያን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በመገኘት የወያኔን ህገወጥ አፈና እና እስራት የሚቃወሙ የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝና በማሰማት የተቃውሞ ድምጻችንን አሰምተናል። በስፍራው የነበርን ሰልፈኞች ስናሰሟቸው ከነበሩት መፈክሮች መካከል በጥቂቱ ኦኬሎ አኳዮ ይፈታ፣ ኖርዌይ ዜጋሽ ኦኬሎ አኳዮ የት ነው ያለው?፣ ኦኬሎ አኳዮ አሸባሪ አይደለም የሚሉ የተለያዩ መፈክሮች ይገኙበታል ::

በማያያዝም እኛ የኖርዌ መንግስት ለአምባገነኑ የወያኔ መንግስት የምትሰጠውን እርዳታ እንድታቆምም ጠይቀናል:: በእለቱ የተዘጋጀውን ደብዳቤ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ዳንኤል አማካኝነት ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይ አስረክበዋል። ተወካይዋም ደብዳቤውን ከተቀበሉ በኋላ ጉዳዩ ን እንደሚያዩትና ችግሩ አሳሳቢ ከመሆኑም አኳያ በትኩረት እየተከታተሉት እንደሆነ አሣውቀዋል። 





በመቀጠልም እኛ በቀጥታ ጉዟችንን ወደ እንግሊዝ ኢምባሲ በማቅናት ታላቅ እልህና ቁጣ የተቀላቀለበት ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ ያደረግን ሲሆን በዛው በእንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት በመሆን የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ በታላቅ ጩህትና በስሜት ስናሰማቸው ከነበሩት መፈክሮች መካከል Britin were is you citizen, Free Andrgachew Tsige, where is your action, stop discrimination among citizens, we are all Andrgachew Tsige, Brtain dont support terrirost regim in Ethiopia የሚሉት ይገኙበታል:: እነዚሁ በኖርዌ የሚኖሩ ኢትዮጵያ ሰልፈኞች በዚሁ በእንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት ባለፈው ጁላይ 3, 2014 ሰልፍ ማድረጋቸው ይታወሳል::
የዛሬው ሰልፍ ከባለፈው ሰልፍ እጅግ በጣም ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር እኛ በጠቅላላ እኔም አንዳርጋቸው ፅጌ ነኝ የሚል የአንዳርጋቸውን ምስል የያዘ ቲሸርት የለበሱ ሲሆን ለሰልፉም ድምቀትን በመስጠት ለነጻነት ታጋዩ ለአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ያለንን  ፍቅር በአደባባይ ያስመሰከርን ሲሆን የተቃውሙ ሰልፉም በሰልፈኞቹ ቁጣና እልህ የተሞላበት እንደነበር ለማየት ተችሏል::
እኛም  የያዝነውን ደብዳቤ በሰልፉ አዘጋጅ ኮሚቴ ተወካይ በአቶ ዳዊት መኮንን በኩል ለእንግሊዝ ኢምባሲ ተወካይ ያስረከቡ ሲሆነ ተወካይዋም ጉዳዩ እንዳሳሰባቸው፣ በትኩረትና በቅርበት እየሰሩ መሆኑን እንዲሁም አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ነፃ እስኪወጡ ድረስ የተቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉና ክትትላቸውን እንደሚቀጥሉ ለሰልፈኛው አሳውቀዋል። በመጨረሻም ሰልፈኞቹ በአንድ ላይ በመሆን የግንቦት 7 ህዝባዊ ኃይል መዝሙር ላንቺ ነው ሐገሬ ላንቺ ነው ላንቺ ነው ኢትዮጵያ ላንቺ ነው የሚለውን ህዝባዊ መዝሙር በደማቅና በሀገራዊ ስሜት ዘምረው ዝግጅቱ በተሳካ ሁኔታ ከቀኑ 

15፡00 ተጠናቋል።
ሁላችንም አንዳርጋቸው ፅጌ ነን!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!




Thursday, July 10, 2014

ያማል ግን ይህን እመም ለመቻል ቁርጠኝነት ይጠይቃል፡፡

10494588_750671571658261_8784450188684809422_nhabtamu ayalew



የፓርላማ አባልና የአንድነት ከፍተኛ አመራር አባል አቶ ግርማ ሰይፉ የኢሕአዴግ   መንግስት በሰላም የሚታገሉ ወጣት ፖለቲከኞችን የማሰሩን ጉዳይ እብድነት ብለዉታል።
«እነዚህ ሰዎች አብደው መሆን ይኖርበታል፡፡ ሀብታሙ አያሌውን ፖሊሶች ይዘውት እንደሄዱ ሰማው፡፡ ስልኩ ይጠራል ግን አይመልስም፡፡ የእነርሱን ሃሳብ የሚቃወም ሁሉ አሸባሪ እየመሰላቸው በሽብር እራሳቸውን እያናወዛቸው ያለ ይመሰለኛል፡፡ ሀብታሙን ሊያስሩት ይችላሉ በህዝብ ውስጥ ያለውን የነፃነት መንፈስ ግን ማስረ አይቻላቸውም፡፡ እልፍ አህላፍ የነፃነት ሰዎች ይፈጠራሉ፡፡ ለነገሩ የሚታሰሩ ንፁሃን ታሳሪዎች ሳይሆን አሳሪዎ በከፍተኛ የህሊና ስቃይ ውስጥ መሆናቸውን መረዳት አሰቸጋሪ አይደለም፡፡» ሲሉ ነበር አቶ ግርማ በፌስ ቡክ አስተያየታቸውን የሰጡት።

«የዚህ ልጅ ነገር ሳያበሳጫቸው አይቀርም፡፡ ሰለማዊ ሰልፍ ላይ በባትሪ አንደሚሰራ ሳያርፍ ያጋልጣቸዋል፡፡ በየሳምንቱ ገበናቸውን በመፅኄት በጋዜጣ ያወጣል፡፡ በዓመት መጨረሻ ደግሞ ትምህርት ተምሮ በክብር በማዕረግ ይመረቃል፡፡ ኢዚህም እዚያም ያገኙታል ሁሉም ጋ ሲያወግዛቸው፤ በቃችሁ ሲላቸው ይሰማሉ፡፡ በቃቸው የሚላቸው ደግሞ እንደበቃቸው ስራቸው ሆኖ ያያቸው እርሱ መሆኑ ያበሳጫቸዋል፡፡ 

ሌላው በግምት አትችሉም ሲላቸው ሀብታሙ ግን አውቃችሀኋለሁ አትችሉም ይላቸዋል፡፡ በእውነት ነርቫቸውን ነው የነካው፡፡ የሚያጓጓው ግን ምን ብለው 28 ቀን የምርመራ ጊዜ ለመጠየቅ አሸባሪ እንደሚሉት ነው፡፡ ዛሬ ቄሱን አሸባሪ አሉ የሚለው ዜና አብርሃ ደሰታ ከመቀሌ ሹክ ብሎናል፡፡ ሀብታሙን ቢሉት አይገርምም፡፡ እንሰማለን፡፡ ተረኞች መዘጋጀት ነው፡፡» ብለው የጻፉት አቶ ግርማ የኢሕአዴግን የፖለቲክ ክስረትና የአቶ ሃብታሙን ታታሪነት የገለጹ ሲሆን፣ እርሳቸዉን ጨምሮ ሌሎች በሰላም የሚታገሉ ሁሉ፣ የሰላማዊ ትግል ለሚያስከፍለው እንዲዘጋጁ ጥሪ አቀርበዋል።

የሰላማዊ ትግል አልጋ በአልጋ እንደሆነ ለሚመስላቸውና በቀላሉ ተስፋ ለሚቆርጡ ወገኖች አቶ ግርማ ሰይፉን ጠንካራ ምክር ለግሰዋል። « ሰላማዊ ታጋዮች መንገላታት እና እስር አሰበውበት የገቡበት ነው፡፡ ምንም ጥርጥር የለውም ያማል ግን ይህን እመም ለመቻል ቁርጠኝነት ይጠይቃል፡፡ የሀብታሙ አያሌው ባለቤት ባለፈው ሳምንት አባቷን በድንገት በሞት ተነጥቃለች አሁን ደግሞ ባለቤቷ በግፍ ወህኒ ወርዶዋል ኮልታፋ ህፃን ልጅ ይዛ መከራዋን እንደምትገፋ ሀብታሙ ያውቀዋል፡፡ ሊያሞላቅቃቸው ቢፈልግ ግን ከኢህአዴ ደጅ ፍርፋሪ መልቀም የሚከለክለው አልነበረም፡፡ » ሲሉ ነበር በሰላምዊ ትግል ከአምባገነኖች ጋር ትንቅንቅ የየዙ ወገኖችን ጀግንነት ያስረዱት።

አቶ ግርማ ሲያጠቃልሉ « ውድ የትግል ጓዶች ከዞን ዘጠኝ ወደ ሌላ ዞን መሸጋገራችሁ ቢያሳዝነንም ፅናታችሁ ያበረታናል፡፡ ፅኑ፡፡ ለካ እነርሱ ይህን የማንበብ መብት የላቸው፡፡ በዞን ዘጠኝ የምትገኙ ሁሉ በርቱ ፅናቱን ይስጣችሁ ማለት የግድ ይላል» በማለት ትግሉን ከማፋፋም ዉጭ ሌላ አማራጭ እንደሌልም ለማሳየት ሞክረዋል።

መንግስታዊ ሽብርተኝነትን የሚሸከም ትከሻ አይኖረንም!!!


THURSDAY, JULY 10, 2014


ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
ሀምሌ 3/2006ዓ/ም

የህወሓት/ኢህአዲግ አገዛዝ በኢትዮጵያ ስልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ዜጎችን በማፈንና በማሰቃየት ብሎም በመግደል የአፈና አገዛዙን ለረጅም ጊዜ ሲያራምድ መቆየቱ ዓለም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡ በተለይም ባለፉት 10 ዓመታት የህዝብን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማፈን እስራትና ግድያውን ህጋዊ ለማስመሰል የተለያዩ አፋኝ አዋጆችን አውጥቷል፡፡ እነዚህን አዋጆችንም ተገን አድርጎ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና አባለትን፣ ጋዜጠኞችንና ጦማርያንን፣ እንዲሁም የእምነት ተቋማት መሪዎችን እና በአገዛዙ ላይ ጥያቄ የሚያነሱ ዜጎችን ማሰሩን፣ ማሰቃየቱንና ግድያውን ተያይዞታል፡፡ በህገ መንግስቱ የተካተቱ የሰብዓዊ መብቶችንና ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን በሙሉ የሚጥሰውና የአምባገነንነት ስልጣኑን ለማራዘም ሲል ያፀደቀው የፀረ-ሽብር አዋጅ ከፀደቀበት እለት አንስቶ ኢህአዴግ ለስልጣኔ ያሰጉኛል የሚላቸውን ፍፁም ሰላማዊ ታጋዮችንና ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው በድፍረት የፃፉ ጋዜጠኞችን ብሎም የእምነት ነፃነታችን ይከበር ብለው የጠየቁ የሀይማኖት መሪዎችን በጠራራ ፀሃይ ያለምንም ወንጀል በዚሁ ህገ ወጥ አዋጅ ‹‹የፀረ ሽብር ግብረ ሀይል›› በሚባል ማንነቱ በማይታወቅ የጨለማ ቡድን ወደ እስር ቤት እያጋዘ ይገኛል፡፡

ይህን የሚያጋልጡ ሚዲያዎችንም ለማፈን እስር ቤቶችን ጨምሮ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር እያፈሰሰ የአየር ሞገድ ያውካል፤ በዚህ ሳያበቃ በሀገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን የሚያሰሙ ፖለቲከኞችን ለማሸማቀቅ እንደ ኢሳት ያሉ ሚዲያዎችን የአሸባሪ ልሳን ብሎ በመፈረጅ ሚዲያውን የሚጠቀሙትን ደግሞ ከአሸባሪዎች ጋር ንክኪ እንዳላቸው አድርጎ መወንጀሉን ቀጥሎበታል፡፡ እንደሰማያዊ እምነት ማንም አካል መልእክት የሚያስተላለፍበትን የሚዲያ ተቋም ሊመርጥለት እንደማይችል መንግስት እንዲገነዘበው ከዚህ በፊት በግልፅ ያሳወቀ ሲሆን አሁንም ፓርቲው በዚሁ የፀና አቋሙ እንደሚቀጥል በድጋሚ ይገልፃል፡፡

ባጠቃለይ የዚህን ገዢ አካል የእውር ድንብር ሀገር የማስተዳደር ጉዞ ለመታገል በርካቶች በሰላማዊ መንገድ እየተንቀሳቀሱ ቢሆንም በህወሓት/ኢህአዲግ ግፍና መከራ ተገፍተው ስርዓቱን በሃይል እናስወግዳለን ብለው ሀገር ጥለው የተሰደዱ ዜጎችም እንዳሉ ይታወቃል፡፡ የህወሓት/ኢህአዲግ ማናለብኝነትና የስልጣን ጥመኝነትም በግለሰቦች ላይ ከሚያስከትለው ማህበራዊ ቀውስ በላይ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ አለመረጋጋትን አስከትሏል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም ይህ ገዢ ፓርቲ የፈጠረው ስርዓት የሀገሪቷን ሰላማዊ የፖለቲካ ምህዳር በማጥበብ ሀገራችንን ወደ አልተፈለገ አለመረጋጋትና ቀውስ እየመራት ይገኛል፡፡ፓርቲያችንም እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትና ሌሎችም በቅርቡ እየተፈፀሙ የሚገኙ ህገ ወጥ ድርጊቶች ስላሳሰበው ይህን መግለጫ ለማውጣት ተገዷል:-

1. ሰኔ 16 2006 ዓ.ም የየመን መንግስት የዓለም አቀፍ ስምምነቶችንና ድንጋጌዎችን በመጣስና በሰው ሀገር የውስጥ ጉዳይ በመግባት የአማፂ ቡድን ግንቦት ሰባት ዋና ፀሃፊ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን መያዟ ይታወሳል፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ ለህወሓት/ ኢህአዴግ ተላልፈው መሰጠታቸውን ከ16 ቀናት በኋላ መታወቁና ይህንንም ሁለቱ ሀይሎች ማመናቸው ተሰምቷል፡፡ ነፃነት በሌለበት ሀገር ዜጎች ሰብዓዊ ክብራቸውን ለማስጠበቅ የሚያደርጉት ጥረት የሌሎች ሀገር መንግስታት የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት በዓለም አቀፍ ስምምነቶችም ሆነ በተለይ በሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ጥላ የሚያጠላ መሆኑን ግንዛቤ አለመወሰዱ እጅግ የሚያሳዝን ድርጊት ነው፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከተያዙ በኋላ ላለፉት 16 ቀናት በምን አይነት ሁናቴ እንደቆዩ ህዝብና ቤተሰቦቻቸው እንዲያውቁት አለመደረጉ፤ ስለ አያያዛቸው ሁኔታም በማህበረሰቡና በፓርቲያችን ውስጥ ከፍተኛ ጥርጣሬ እንዲኖር አድርጓል፡፡ሰማያዊ ፓርቲ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሰብዓዊ አያያዝ እያሳሰበው ህወሓት መራሹ የኢህአዴግ አገዛዝ አያያዛቸውን ግልፅ እንዲያደርግ ሰብዓዊ ክብራቸውም እንዲጠበቅ በጥብቅ ያሳስባል፡፡
2. በዚሁ ሳምንት ገዢው ፓርቲ ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ የአምባገነኑን መንግስት ህወሓት/ኢህአዲግን ሲታገሉ የነበሩ ፖለቲከኞችን በስመ አሸባሪ ከያሉበት እየለቀመ ህገ-ወጥ እስራት መፈፀሙ ይታወቃል፡፡ ህወሓት/ኢህአዲግ ይህ ግብታዊ ተግባሩ ምንም እንኳን አዲስ ባይሆንም በአሁኑ ወቅት ለውጥን ለማምጣት በቆራጥነት እየታገሉ ያሉ ሰላማዊ ታጋዮችን ማሰሩ በሀገር ውስጥ በህጋዊ መንገድ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ፓርቲዎችን ከአማፂ ቡድኖች ጋር ግንኙነት ያላቸው በማስመሰል ሰላማዊ ትግሉን ለማዳከምና መጪውን 2007 ዓ/ም ምርጫ ያለ ተቀናቃኝ ለማለፍ የሚደረግ ህገ ወጥ እንቅስቃሴ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ የፓርቲያችን ብ/ም/ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነው አቶ የሺዋስ አሰፋ በሰላማዊ ትግሉ በቁርጠኝነት እየተሳተፈ ባለበት ሁኔታ ለእስር መዳረጉ፤ የአንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው፤ የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ምክትል ሀላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ከፍተኛ የህዝብ ንቅናቄን በመፍጠር ላይ ያለው የአረና /ትግራይ/ ፓርቲ አመራር አባል የሆኑትን አቶ አብረሃ ደስታ ለእስር መዳረጋቸው ህወኃት/ኢህአዴግ የመጨረሻው መጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱን ያረጋግጣል፡፡ በመሆኑም አገዛዙ እያካሄደ ያለውን መንግስታዊ ሽብር አቁሞ ለሀገርም ሆነ ለራሱ የሚበጀውን መንገድ እንዲከተል እያሳሰብን የታሰሩት የፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን፡፡

በመጨረሻም ፓርቲያችንን መንግስት እያደረገ ያለው ሽብርን የመንዛትና ህግን የመጣስ ተግባሩ መቼም ቢሆን ከሰላማዊ ትግሉ እንደማያቆመውና ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በአፅንኦት እየገለፀ እነዚህንና ከላይ የተጠቀሱትን የገዢውን ፓርቲ መርህ አልባነት፣ ህገ-ወጥነት እና የለየለት አምባገነንነትን አሁን ካለው ነባራዊ እውነታ ጋር አጣምሮ የትግል ስልቱን ደረጃ ከፍ ወዳለ ምዕራፍ ማሸጋገር እንዳለበት አምኗል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በኋላ ለምናደርጋቸው ሀገር አቀፍ ንቅናቄዎች መላው የሀገሪቱ ህብረተሰብ በንቃት ተዘጋጅቶ እንዲጠብቅ ጥሪውን እያስተላለፈ ለዚህም ቁርጠኛ አመራር ለመስጠት ዝግጁነቱን ለመግለፅ ይወዳል፡፡በዚህ አምባገነንነትን ለመታገል በሚደረገው ንቅናቄም በሀገር ውስጥ የሚገኙ ህጋዊና ሰላማዊ ፓርቲዎች፤አለም አቀፍ ተቋማት፤የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፤ሲቪክ ማህበራት፤መላው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከሰላማዊ ትግሉ ጎን በጋራ እንድንቆም እንጠይቃለን፡፡

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር
ሰማያዊ ፓርቲ
ሀምሌ 3/2006ዓ/ም

Sunday, July 6, 2014

ሚስስ አና ጎሜዝ፣ አቶ አንዳርጋቸው ለኢትዮጵያ ተላልፈው መሰጠታቸውን ማረጋገጣቸውን ለእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዊልያም ሔግ በጻፉት ደብዳቤ አስታውቀዋል፡፡




የአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ አባል የሆኑትና የኢትዮጵያን መንግሥት በመንቀፍ የሚታወቁት ሚስስ አና ጎሜዝ፣ አቶ አንዳርጋቸው ለኢትዮጵያ ተላልፈው መሰጠታቸውን ማረጋገጣቸውን ለእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዊልያም ሔግ በጻፉት ደብዳቤ አስታውቀዋል፡፡
ሚስስ ጎሜዝ በይፋዊ ድረ ገጻቸው ባሰፈሩት ደብዳቤ አቶ አንዳርጋቸው ለኢትዮጵያ መንግሥት ተላልፈው እንደተሰጡ መረጃ ማግኘቻቸውን ገልጸው፣ በዚህም መደንገጣቸውንና የእንግሊዝ መንግሥት ምንም ዓይነት ዕምርጃ ባለመውሰዱ መናደዳቸውንም አስረድተዋል፡፡
ሚስ ጎሜዝ በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የሕይወትና የአካል አደጋ ሊደርስባቸው እንደሚችል፣ እንዲሁም ባላመኑበትና ባልፈጸሙት ወንጀል ክስ ሊቀርብባቸው እንደማይገባ ገልጸው፣ በተቻለ መጠን ወደ እንግሊዝ የሚመለሱበት ሁኔታ እንዲመቻችም ጠይቀዋል፡፡
በ1997 ዓ.ም. ብሔራዊ ምርጫ የአውሮፓ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ የነበሩት ሚስስ ጎሜዝ፣ የእንግሊዝ መንግሥት የኢትዮጵያ ዋነኛው ለጋሽና የፖለቲካ ደጋፊ በመሆኑና ተፅዕኖውም ከማንም አገር የላቀ በመሆኑ፣ አቶ አንዳርጋቸውን ማስፈታት አለበት ሲሉ ለቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ፕሮግራም መናገራቸው ተዘግቧል፡፡
አቶ አንዳርጋቸው ለኢትዮጵያ መንግሥት ተላልፈው ተሰጥተዋል መባሉን በተመለከተ፣ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎችን ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡ የመንግሥት ባለሥልጣናትም ምንም ዓይነት መረጃ አልሰጡም፡፡ ነገር ግን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ፣ አቶ አንዳርጋቸው ኢትዮጵያ ውስጥ በሕግ የሚፈለጉ በመሆናቸው ተላልፈው መሰጠት እንዳለባቸው ለውጭ ሚዲያ መናገራቸው ተሰምቷል፡፡
ኢትዮጵያና የመን በ1991 ዓ.ም. በተፈራረሙት የፀጥታና የደኅንነት ስምምነት መሠረት፣ የመን አቶ አንዳርጋቸውን ለኢትዮጵያ አሳልፋ እንደምትሰጥ ይነገራል፡፡ በሌላ በኩል የእንግሊዝ ዜግነት ስላላቸው ለኢትዮጵያ ተላልፈው መሰጠት የለባቸውም የሚሉ ሲኖሩ፣ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እስከገቡ ድረስ ተጠያቂነት እንዳለባቸው የሚከራከሩ አሉ፡፡